የማህበረ ቅዱሳን አባላት በአንድ ጉዳይ ለሁለት መከፈላቸው ተሰማ
ማህበረ ቅዱሳን ተሃድሶዎችን ለማሳደድ 100000 ብር ያስፈልጋኛል ብሎ ገቢ ለማሰባሰብ እየተዘጋጀ ባለበት ባሁኑ ወቅት ጊዜያችንን እና ገንዘባችንን በማይጠቅም ነገር ላይ ማጥፋት የለብንም የሚሉ አባላት ከውስጥ ተቃውሟቸውን እያነሱ ነው። እነዚህ ተቃዋሚዎች ምክንያታቸውን ሲያቃርቡ በቅርቡ የያዙት ተሃድሶን የማሳደድ ፕሮግራም በሕዝቡ ዘንድ ተቀባይነት ማጣቱና ወጤት ካለማስገኝቱም በላይ በተቃራኒው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤ/ ክርስቲያንን ሕዝብ ለሁለት እየከፈለ ከፍተኛ አለመተማመንን ፈጥሯል ይላሉ።
ብዛት ያላቸው ምዕመናን ደግሞ ቄሶችና ሰባኪዎች ተሃድሶ ከሆኑ እኛስ ከነርሱ በምን እንበልጣለን? ይህ ጉዳይ የካህናቱ ስለሆነ ያናንተን አልባልታ መስማት አንፈልግም በማለት ከፍተኛ ተቃውሞአቸውን በማህብረ ቅዱሳን ላይ አሰምተዋል እያሰሙም ነው።
በዋናነት ግን ማህበረ ቅዱሳንን ለሁለት ለመከፈል ያበቃው የገረገራ ጊዮርጊስ ጉዳይ ነው። ባለፈው እንደ ዘገብነው የሰሜን ወሎ ስራ አስኪአጅን ጨምሮ አራቱ የማህበረ ቅዱሳን አባላት ኢየሱስ ክርስቶስን ሲያሳድዱ ሰንብተው ሲመለሱ የጌታ ቁጣ እንዳገኛቸውና አጥንታቸው ተለቅሞ እስኪቀበር ድረስ እንደተቀጡ ይታወቃል። በዚህ የመቂት ወረዳ የማሳደድ ፕሮግራማቸው ወንጌልን እንሰብካለን ብለው ሕዝብን በማታለል ወንጌልን ሲቃወሙ ሰንበተዋል። ሦስት ዲያቆናትን ሁለት ቄሶችን፤ አንድ የቅዳሴ መምህርና የመምሪያ ኃላፊን ከሥራቸው አፈናቅለዋል ሕዝብ በድንጋይ እንዲወግራቸው ቅሥቀሣ አድርገዋል በዚህም ምክንያት እነዚህ አገልጋዮች በገንዛ ሐገራቸው እንዳይወጡ እንዳይገቡ በመንገድ ላይ እንኳ እንዳይታዩ ተደርገዋል. ዘመድ እና ወገን እንዲአይገላቸው ማህበረ ቅዱሳን በመቀስቀሱ ከፍተኛ ስደት ደርሶባቸው ዛሬ በሥጋት ላይ ይገኛሉ።
ጌታ ግን የመውጊያውን ብረት ብትቃወመው ባንተ ይብስብሃል እንዳለው የመውጊያውን ብረት የተቃወሙት አራት የማህበረ ቅዱሳን ባላት በመውጊያው ተወግተው ወደ ማይመለሱበት ዓለም ሄደዋል። ይህ ነገር ግን የገረገራን ሕዝብና ማህብረ ቅዱሳንን ለሁለት ከፈለ። ግማሹ የገረገራ ሕዝብ የማህበረ ቅዱሳን አባላት ኃጢአተኛ ናቸው ቅዱሳንን ስላሳደዱ ወዲያው ፍርዳቸውን አገኙ እነዚህ ቄሶች እውነተኛ የኢየሱስ ክርስቶስ አገልጋዮች ነበሩ እናም ወደ ቦታቸው መመለስ አለባቸው በማለት በመከራከር ላይ ይገኛል።
ግማሹ የድጋይ ልብ የያዘው የገረገራ ሕዝብ ግን በነዚህ ሰዎች ምክንያት ነው ወንድሞቻችን አደጋ የደረሰባቸውና እነዚህን ቄሶች መበቀል አለብን ብሎ ቄሶችን ለመግደል በፈለግ ላይ ነው። ለንስሐ መዘጋጀት ይቅርታ መጠየቅ ሲገባ እንደገና ቄሶችን ከተሰደዱበት ፈልጎ ለመግደል መሞከር በጣም የሚያሳዝን ነው። ጌታ የሚገላችሁ ሁሉ እግዚአብሔርን እንደሚያገለግል የሚመስልበት ጊዜ ይመጣል ያለው ቃል እየተፈጸመ ነው። ነገሩን ላስተዋለው ግን ይህ ጉዳይ ለማህበረ ቅዱሳን የንስሐ ጥሪ መሆኑን ነው። ኢየሱስን በማሳደድ አንድም ሰው አልተጠቀመም።
የገረገራ ሕዝብ የመከፋፈሉን ያህል የማህበረ ቅዱሳን አባላትም ጥቂቶቹ የወንድሞቻቸው በአደጋ መሞት በጥሞና ሥራቸውን እንዲመረምሩ አድርጓቸዋል። ማንን እያገለገልን ይሆን? የሚሉ አባላት በዝተዋል እነዚህ እግዚአብሔር የድንጋዩን ልብ አውጥቶ የሥጋና የመንፈስ ልብ የሰጣቸው ናቸው በሃይማኖት ብትኖሩ ራሳችሁን መርምሩ እንደተባለው ራሳቸውን የሚመረምሩ እየበዙ ናቸው
አንዳዶች ይህ ቅጣት ከእግዚአብሔር የተላከልን ማስጠንቀቂያ ነው እና ነገሮችን እንደገና ማጤን አለብን፤ ሰው ኢየሱስ ክርስቶስን ካመነ በቂው ነው የሚሉ ሐሳቦች በማህበረ ቅዱሳን ዋና ቢሮ እና ንኡስ ማዕከላት ተጧጡፏል።
እነዳንኤል ክብረትና መሰሎቹ ደግሞ እንደ ፈሮን ዓይነት የድንጋይ ልብ እንደተሰጣቸው እንዲያውም ያሁኑ ፕሮግራማችን ካልተሳካ ድብደባ እና ግድያ እንጀምራለን በማለት እየፎከሩ ነው። በተለይም ዳንኤል ክብረት የታባለው የክርስቶስ ጠላት "አባ ሕርያቆስ ከሌሉበት መንግሥተ ሰማያት አባ ሕርያቆስ ያሉበት ሲኦል እንደሚሻለው" ሲናገር ተደምጧል።
አባ ሕርያቆስ የአባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ ጓደኛ ሲሆኑ የዋልባ መነኩሴ በነበሩበት ወቅት ቅዳሴ ማርያምን የደረሱ ሰው እንደነበሩ ድርሳነ ኡራኤል ይናገራል። ነገር ግን ድርሰቱ ከግብጽ የመጣ ለማስመሰል አባ ሕርያቆስ ዘብሕንሳ ተብለው ይጠራሉ የግብጽ ቤተ ክርስቲያን ግን ሰውየውን አታውቃቸውም የኢትዮጵያው የአባ ሕርያቆስ ቅዳሴም ግብጽ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ አይገኝም። እንደ ድርሳነ ኡራኤል ዘገባ ከሆነ ግን ሰውየው ኢትዮጵያዊ ናቸው። ሰውየው የትም ይሁኑ የት ግን ዳንኤል ክብረት ሰውየውን ካላገኘኋቸው ወደ መንግሥተ ሰማያት አልገባም ብሎ እምቢ ያለበት ምክንያት ግልጽ አይደለም። ሰውየው ገና ቅዳሴ ማርያምን ደርሰዋል ብለን አድራሻቸውን ልናውቅ እንችላለንን? ሲኦል ይሁኑ ገነት እንዴት ማረጋገጥ ይቻላል? ብዙ የማያምኑ ሰዎች ጠንቋዮችም ታላላቅ ድርሰት እንዳላቸው የታወቀ ነው። ግሩም ድንቅ የሆኑ ምሥጢራዊ ቅኔዎችን የሚቀኙ ሰዎች ጠንቋይ ሆነው አግኝተናቸዋል። ስለዚህ ያንድ ሰው እውቀታዊ ችሎታ ሲኦል ወይም ገነት ለመግባቱ ማረጋገጫ አይሆንም ይህን ጉዳይ የሚያውቀው እግዚአብሔር ብቻ ነው።
ዳንኤል የሚሻለውን ራሱ ያውቃል ምርጫው የራሱ ነው እኛ ግን ማንም እዚያ ባይገኝ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ያለበትን መርጠናል። በእርግጥም የዳንኤሉ አባ ሕርያቆስ ጌታ ባለበት ከተገኙ እኛም እዚያ እናገኛቸዋለን ምን አልባት ከሌሉ ግን እርሳቸውን ተከትለን ሲኦል መግባት አንፈልግም። ለዳንኤል ይመቸው። ይህ ትምህርቱን በሲዲ አሳትሞ ለሕዝብ ማሰራጨቱ ጉዙው ወዴት እንደሆነ ከወዲሁ ማወቅ ይችላል።
ዳንኤል እና መሰሎቹ የሰሜን ወሎው አደጋ የጌታ ቅጣት መሆኑ አልተዋጠላቸውም ይልቁንም የጌታ ቅጣት ነው ብለው ያመኑትን እና ለንስሐ የተዘጋጁትን እናንተም ከሐተሃድሶዎች ጎራ ልትመደቡ ትችላላችሁ የሚለውን የተለመደ ማስፈራሪያ እያስተጋቡ ነው።
ለቤተክርስቲያናችን መሻሻል የምንጥር የቤተ ክርስቲያኒቱ ልጆች ግን የወንድሞቻችንን ክፉ ነገር አንመኝም እግዚአብሔር ይቅር እንዲላቸውም እንጸልያለን ክፉውን በክፉ አትቃወም ይላልና ቃሉ ማህበረ ቅዱሳንን በክፉ አናስበውም እርሱ ሊገለን ሊያስድደን በሕዝባችን ፊት ሊያዋርደን ስማችንን ቢያጠፋም ስለ ስሜ ክፉውን ያደርጉባችኋል፣ ስለስሜ የተጠላችሁ ትሆናላችሁ የሚለው የጌታ ቃል ትዝ ስለሚለን በደስታ ተሞልተናል ወንድሞቻችን በያዙት የተሣሳተ አቋም ግን እጅግ አዝነናል ያዝነውም ስለምንወዳቸው እንጂ ሥራው ተጓጎለ ብለን አይደልም ሥራውን ጌታ እኛ እንደማንሠራው ጠንቅቀን እናውቃለን። እኛ ስለስሙ መነቀፋችን ደስ አሰኝቶናል ሥራው የጌታ ነው ሁሉም በጊዜው ይከናወናል ተሐድሶ የጌታ ሐሳብ ከሆነ ያብባል ይስፋፋል የጌታ ካልሆነ ግን ይጠፋል እኛ ብንሰደድ ኢየሱስ ክርስቶስ ሌሎች የተቀቡ አገልጋዮችን ያስነሳል። እግዚአብሔርን ማሸነፍ አይቻልም፤ ለወንድሞቻችን ለማህበረ ቅዱሳን አባላት የምንመክረው ግን ከማትችሉት ጌታ ጋር ነውና የገጠማችሁት ተጠንቀቁ ነው፤ እኛም ቢያንስ በሀገራችን የመኖር መብት አለን በቤተ ክርስቲያናችንም ጥያቄ የማንሳት መብት አለን መልሱን ግን ከዚያው ከሲኖዶሱ እንጂ ከናንተ አንጠብቅም። እናም እኛን በመግደል ደም ማፍሰስ እንጂ ሌላ ምን ትርፍ ታገኛላችሁ? ፖለቲካ ከሆነ አላማችሁ ለምን ፓርቲ ሆናችሁ አትወዳደሩም? በኛ ደም ለመበልጸግ እኛን በማርከስ ልትቀደሱ አስባችሁ ነው? ለምን አታስተውሉም? ሰውን በማሳደድ የጸደቀ ማን ነው? የሃማኖት ችግር አላባችሁ ካላችሁ ሊቃውንት ጉባኤው መድረክ ያዘጋጅልንና ማን እንደተሣተ እንንወያይ ስንላችሁ እምቢ ከተሐድሶዎች ጋር አብረን አንቀመጥም በማለት ትሸሻላችሁ ፡ ለምን ትሸሻላችሁ? አላውቂነታችሁ እንዳይገለጥ አይደለምን? መወያየት አንፈልግም ካላችሁ ለምን ታሳድዱናላችህ? በእውነት በእግዚአብሔር መንፈስ የምትመሩ ከሆነ አልቧልታ በየመንደሩ ከመንዛት ቃሉን ሰብካችሁ ለምን አታሳምኑንም?
አሁን የያዛችሁት ፕሮግራም ግን ከምር አደገኛ ነው ሕዝቡን ግራ ያጋባና እርስ በርሱ እንዳይተማመን የሚያደርግ ለወንጌልም ልቡን እንዲዘጋ ንስሐ ገብቶ እንዳይፈወስ እያረጋችሁ ነው በዚህ ተንኮላችሁ ምክንያት በቤተ ክርስቲያን ላይ የሚመጣው የእግዚአብሔር ቁጣ ያስፈራል ቁጣውን ብትንቁ እንኳ ለትውልድ አይብጅምና አስቡበት የጓደኞቻችሁን ሐሳብ ለማዳመጥ ጆሮአችሁን ክፈቱ፤ እኛ ተከፋፍላችሁ እንድትጋደሉ አንፈልግም ግን ተለውጣችሁ ለውጥ እንድታመጡ እንፈልጋለን ይህ ለኛም ለሀገርም ለቤተ ክርስቲያንም ለናንተም ለጌታም ይጠቅማል አሜን
የለውጥ ያለህ?
ታዛቢው ነኝ