Friday, August 19, 2011

ፓትርያርኩ ከቤተ ክርስቲያኒቱ ቀኖና ውጪ ለሚንቀሳቀሱ ማስጠንቀቂያ ሰጡ "abaselama"

Wednesday, June 8, 2011

በማኅበረ ቅዱሳን ላይ ከየአቅጣጫው ተቃውሞዎች እየተሰነዘሩ ነው== dejesemay.org

  • የቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ ተማሪዎች ታሪካዊ የተባለ የአቋም መግለጫ በማኅበረ ቅዱሳን ላይ አወጡ፤ ለቅዱስ ፓትርያርኩም አቀረቡ
  • ማኅበረ ቅዱሳን ከነጥሎ መምታት ወደ ጅምላ የስም ማጥፋት ስልት መሸጋገሩ ያስከተላቸው መዘዞች
  • በሐዋሳው ጉዳይ ላይ ቋሚ ሲኖዶስ ማኅበረ ቅዱሳንን አንገት ያስደፋ ውሳኔዎችን አሳለፈ 
ማኅበረ ቅዱሳን በለኮሰው እሳት መለብለብ መጀመሩን ከየአቅጣጫው እየተነሡ ያሉ ፀረ ማኅበረ ቅዱሳን እንቅስቃሴዎች እያረጋገጡ መሆኑን ምንጮቻችን ገለጹ፡፡ ማኅበሩ የስም ማጥፋት ዘመቻ ከከፈተባቸው መንፈሳውያን ኮሌጆቻችን መካከል አንዱ የሆነው የቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ ተማሪዎች በ5/8/2003 ዓ.ም. በማኅበረ ቅዱሳን ላይ የተቃውሞ ሰልፍ በማድረግ ወደመንበረ ፓትያርክ ጽ/ቤት ቀርበው የአቋም መግለጫቸውን ለብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ አቅርበዋል፡፡ የወንድሞች ከሳሽ የሆነውና ጥቂት ዘመን እንደቀረው ዐውቆ በታላቅ ቁጣ እንደ ወጣው እንደ ግብር አባቱ እንደ ዲያብሎስ፣ ማኅበረ ቅዱሳንም ዘመኑ እንደ ተፈጸመና ጥቂት እንደቀረው ተረድቶ በቤተ ክርስቲያን ልጆች ላይ የስም ማጥፋት ዘመቻውን አጠናክሮ በቀጠለበት በዚህ የዐቢይ ጾም ወቅት፣ የመንፈሳዊ ተቋማትን (የኮሌጆችን) ተማሪዎች ነጥሎ ከመምታት ስልቱ ወደጅምላ የስም ማጥፋት ዘመቻ መሸጋገሩ የኮሌጁን ተማሪዎች በእጅጉ እንዳስቆጣና ለተቃውሞ ሰልፍ እንዳንቀሳቀሳቸው ምንጮቻችን ጠቅሰው፣ በማኅበሩ ላይ ከኮሌጁ ተማሪዎች በኩል እንዲህ ያለና የአንድ እጅ ጣት የማይሞሉ ጥቂት የማኅበረ ቅዱሳን ደጋፊ ተማሪዎች ሲቀሩ፣ አብዛኛው ተማሪ ቀፎው እንደ ተነካ ንብ አንድ ሆኖ ለተቃውሞ መውጣቱ በኮሌጁ ታሪክ የመጀመሪያ መሆኑ ይነገራል፡፡
“የቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ ተማሪዎች ወቅታዊ በሆኑ የቤተ ክርስቲያቱ ችግሮች ዙሪያ የተሰጠ የዐቋም መግለጫ” በሚል ርእስ የወጣው የዐቋም መግለጫ 6 ነጥቦች ያሉት ሲሆን፣ በቅድሚያ ማኅበረ ቅዱሳን እየሠራ ያለውን መሠሪ ተግባር በዝርዝር አስቀምጧል፡፡ በዚሁ መሠረት ማኅበረ ቅዱሳን፡-
  • ቤተ ክርስቲያኒቱ አምናባቸው የከፈተቻቸውንና የምትቆጣጠራቸውን፣ ለቤተ ክርስቲያኒቱም ከፍተኛ አገልግሎት እያበረከቱ ያሉትን ኮሌጆች የሃይማኖት ችግር አለባቸው የሚል የስም ማጥፋት ዘመቻ መክፈቱ፤
  • የቤተ ክርስቲያኒቱን የአስተዳደር መዋቅር በመናቅና እንደሌለ በመቁጠር ከቤተ ክርስቲያን ዕውቅና ውጪ በየሆቴሉ በየአዳራሹ ስብሰባ በመጥራት በፈጠራ ወሬና አሉባልታ፣ የቤተ ክርስቲያን አባቶችንንና ምእመናንን ግራ የማጋባትና ረብሻና ብጥብጥ ሰፍኖ ቤተ ክርስቲያቱ ብሎም አገሪቱ በብጥብጥ የምትተራመስበትን መንገድ መቀየሱ፣
  • በቅዱስ ፓትርያርኩ ዘመነ ፕትርክና ቤተ ክርስቲያናችን በዓለም አብያተ ክርስቲያናት ያገኘችውን ስፍራ በማጣጣልና ለዚህ ከፍተኛ ጥረት ያደረጉትን የቅዱስ ፓትርያርኩን ስም በየሚዲያው ሲያጠፋና ሲያስጠፋ የኖረ መሆኑና አሁን ግን የፕሬስ ሕጉ ሕገወጦችን ተጠያቂ የሚያደርግበት ሁኔታ ስለተፈጠረ፣ ሌላውን ካልወነጀለ፣ ካልተሳደበና ስም ካላጠፋ የሠራ የማይመስለው ማኅበረ ቅዱሳን “ደጀ ሰላም” የተባለ የወሬ ድረ ገጽ ከፍቶ በዓለም አቀፍ ደረጃ የስድብ አፉን ማላቀቅ ከጀመረ ውሎ ማደሩ ተመልክቷል፡፡ የሚከተለው ስልትም “መንጋውን ለመበተን እረኛውን መምታት” የሚል ነው ይላል መግለጫው፡፡ ስልቱ ፓትርያርኩን በማስወገድ ቤተ ክርስቲያቱን መቆጣጠር የሚል አንድምታ ያለው ሲሆን፣ እርሳቸውን አስወግዶ እርሱ የቀረጸውን ፖለቲካዊ የሃይማኖት ሥርዐት ማስፈን የመጨረሻ ግቡ መሆኑም የአደባባይ ምስጢር ነው፡፡
6 ነጥቦች ያሉት የቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ ተማሪዎች ያወጡት የአቋም መግለጫ የሚከተለው ነው፡፡
1- “የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ለዘመናት ዶግማዋን፣ ቀኖናዋንና ትውፊቷን ጠብቃ የኖረችው ባላት ጠንካራ አስተዳደራዊ መዋቅርና በመንፈስ ቅዱስ የሚመራ ቅዱስ ሲኖዶስ ያላት ያለ ምንም እንከን የኖረች ስለሆነች፣ አሁንም ይህ ሥርዐቷንና የቅዱስ ሲኖዶስ መመሪያ ተጠብቆ በተገቢው የቤተ ክርስቲያን አስተዳደራዊ ሰንሰለት የቅዱስ ሲኖዶስ ክብርና ሥልጣን እንዲጠበቅ፣
2- “ማኅበረ ቅዱሳን የሚባለው ማኅበር አሁን የቤተ ክርስቲያናችንን የአስተዳደራዊ መዋቅር እና የቅዱስ ሲኖዶስ አመራርን ወደ ጎን በመተውና በመናቅ የቤተ ክርስቲያኒቱን አባቶች ከምእመናን፣ ከመንፈሳዊ ኮሌጆች የሚወጡ ደቀ መዛሙርትን ከአባቶችና ከምእመናን ጋር በማጋጨት የኮሌጆቹን ስም በማጥፋት እያደረጉት ካለው ሕገወጥ ተግባር ቅዱስ አባታችን እና ጉዳዩ የሚመለከታቸው የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት በዚህ ማኅበር እንቅስቃሴ ላይ አስተዳደራዊ እርምጃ እንዲወስዱ እንጠይቃለን፡፡
3- “ይህን የስም ማጥፋት ዘመቻ በማስፋፋት ላይ ያለውና የፈጠራ ወሬውን የፈጠረው አቶ ያረጋል አበጋዝ የሚባል በማኅበረ ቅዱሳን የሐመር መጽሔት ዝግጅት ክፍል ምክትል ኀላፊ እና አባል ግለሰቡም ፍጹም የሆነ ሃይማኖታዊና ቤተ ክርስቲያናዊ ዐላማን የማያራምድ ሲሆን፣ በተቃራኒው ሽብርና ሁከትን በቤተ ክርስቲያኒቱ ብሎም በአገር ለመፍጠር በጥናታዊ ጽሑፍ መልክ በመላው ሀገሪቱ በመዘዋወር የቤተ ክርስቲያቱን መንፈሳዊ ኮሌጆችን የተሐድሶ እና የመናፍቃን መፍለቂያ ወይም መፈልፈያ ናቸው በማለት ችግር እየፈጠረ ያለ በመሆኑ፣ ይህ ሁኔታ የቤተ ክርስቲያኒቱንም ሆነ የሀገሪቱን ሰላም የሚያናጋ  በመሆኑ ግለሰቡ በቤተ ክርስቲያኗ የበላይ አመራር እና ኀላፊዎች ተጣርቶ ከዚህ ተግባር እንዲቆጠብና ከዚህ ቀደም ላደረጋቸው ድርጊቶች ሕጋዊ እርምጃ እንዲወሰድበት እንጠይቃለን፡፡
4- “የዚህ የስም ማጥፋት ዘመቻ ተባባሪ የሆኑ በቤተክርስቲያን መዋቅር ውስጥ የመሸጉ ለዚህ መሠረተ ቢስ ውንጀላ እና ሽብር የተሳሳተ መረጃ አቀባይ እና የተሰጣቸውን ኀላፊነት ወደ ጎን በመተው ቤተ ክርስቲያንን ማገልገል ሲገባቸው፣ ለዚህ እኩይ ተግባር ተባባሪ በመሆን ለማኅበሩ ፈቃድ የሰጠውን የቅዱስ ሲኖዶስን ስም በማጥፋት ራሳቸውን የዚህ ማኅበር አባል ያደረጉ በኮሌጆቻችን እና በጠቅላይ ቤተ ክህነት በየመምሪያው ያሉ የቤተ ክርስቲያኗ አገልጋዮች ከዚህ ሥራ እንዲቆጠቡና ሁኔታው ተጣርቶ አስፈላጊው አስተዳደራዊ እርምጃ እንዲወሰድባቸው በጥብቅ እንጠይቃለን፡፡
5- “ባለቤትነቱ ለጊዜው ያልጠረጋገጠ ነገር ግን በጽሕፈቱ ሐሳብ ደረጃ ማንነቱ የሚታወቅ ማኅበር በቅዱስነትዎ እና በብፁዓን አባቶች ላይ እንዲሁም በመምሪያ ኀላፊዎች በመንፈሳዊ ኮሌጅ ደቀ መዛሙርት ላይ የስም ማጥፋት ዘመቻ በደጀ ሰላም ብሎግ (በደጀሰላም ዌብ ሳይት) እየተደረገ ያለውን፣ ቤተ ክርስቲያናችንን የማይወክልና በቅዱስ ሲኖዶስ የማይታወቅ ድርጊት በመሆኑ፣ ለምእመናን እና ለቤተ ክርስቲያን አገልጋዮች እንዲሁም ለመንግሥት በማሳወቅ ጉዳዩን የሚያከናውኑ ግለሰቦችም ሆኑ ማኅበሩ ላይ እርምጃ እንዲወሰድ ስንል አቋማችንን እንገልጻለን፡፡
6- “በመጨረሻም ለዚህ ስም የማጥፋት ዘመቻ እንደ ምሽግ የሚጠቀሙበት የቤተ ክርስቲያኒቱ ዐውደ ምሕረት ነው፡፡ ነገር ግን ቅዱስ አባታችን ደጋግመው እንደሚያዙትና ቤተ ክርስቲያኗም እንደምታምንበት የዐውደ ምሕረት ጉባኤ በተማረው ክፍል ወይም ቤተ ክርስቲያኒቱ መምህራን ብላ በመንፈሳዊ ኮሌጆች በአብነት ትምህርት ቤቶች በምታስመርቃቸው መምህራን እንዲሆን ከዚህ በፊት የተጻፈ ቢሆንም፣ ተፈጻሚ እንዲሆን በአጽንኦት ከከፍተኛ መንፈሳዊ ኮሌጆች እንዲሁም ከሚታወቁ የአብነት ትምህርት ቤቶች መምህራን ውጪ በቤተ ክርስቲያን ዐውደ ምሕረት ማስተማር የማይቻል መሆኑ ተገልጾ ለእየአህጉረ ስብከትና ለወረዳ ቤተ ክህነቶች እንዲሁም ለእያንዳንዱ አጥቢያ ቤተ ክርስቲያን ሰርኩላር በድጋሚ እንዲተላለፍልን እና ለመምህራኑም ሕጋዊ የሆነ የሚታደስ መታወቂያ እንዲሰጣቸው በጥብቅ እንጠይቃለን፡፡”
ከዚህ የአቋም መግለጫ በመነሳት እናንተም ሆናችሁ ሌሎቹ ሁላችሁም ልጆቼ ናችሁ በማለት ንግግራቸውን የጀመሩት ቅዱስ ፓትርያርኩ መቼም ሳትበደሉ ገፍታችሁ እንዲህ በቁጭት አትመጡም‹‹ውሸት ሲደጋገም እውነት ስለሚመስል›› ያለውን ችግር ለሚመለከተው አካል ለማሳወቅ መነሳታችሁ ‹‹ለእኔም ሆነ ለብፁዓን አባቶቼ ትልቅ የቤት ሥራ ነው›› ብለዋል፡፡ ‹‹ያገለገልነው ሕዝብ ድንጋይ እንዲወረውርብን በገዛ ቤታችን የባይተዋርነት ስሜት እንዲያድርብን እየተገደድን ነው›› ላሉት የደቀ መዛሙርቱ ተወካይ ቅዱስነታቸው አክለው ሲመልሱ ‹‹የሠራ ሁሉ ይነቀፋል ሥራ ስለ ሰራችሁ አገልግሎታችሁ ትርጉም ስላለው ነው የተነቀፋችሁት፤ ሕይወት ስለሌላቸው በድኖች ማን ምን ይላል? አይዟችሁ ስለ ሰሙ ነቀፋን መሸከም የደጋጎቹ አባቶቻችሁ መንገድ ነው በርቱ!  እኛ ይኼ ነው ብለን ዛሬ ምንም ባንላችሁም አሁን እናንተ ባነሳችኋቸው ጉዳዮች ዙሪያ እየሰራን ስለ ሆነ በቅርቡ ተግባራዊ ምላሽ ታገኛላችሁ፡፡ ቤተ ክርስቲያንን እንዲያገለግሉ አደራ ተጥሎባቸው መንፈሳዊ ተቋሙን ለጥፋት እያዘጋጁት ያሉት የኮሌጁም አስተዳዳሪዎች ለእውነትና ለቅድስት ቤተ ክርስቲያን እንደሰሩ መደረጉ የማይቀር ነው በማለት የዕርምት እርምጃ እንደሚወሰድ ተገልጾላቸዋል የሚል ምላሽ መሰጠቱን ምንጮቻችን አክለው ገልጸዋል፡፡
አስገራሚው ነገር የፈጠራው “ጥናታዊ ጽሑፍ” ደራሲ አቶ ያረጋል በአንድ በኩል ኮሌጁን የመናፍቃን መፈልፈያ እያለ ሲሳደብ፣ እርሱ ለስም ማጥፋት ዘመቻው በተገኘባቸው አዳራሾች የመድረክ መሪዎች የነበሩት የማኅበሩ አባላት ሲያስተዋውቁት ስሙን “የቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ ደቀ መዝሙር” ከሚል ቅጽል ጋር መጥራታቸው፣ የሌላውን በግ ለመውስድ ከጅሎ ባለቤቱን የተሸከምኸው ውሻ ነው እያለ ለማስጣል የሞከረውን ቀሳጢ ታሪክ ያስታውሳል ሲሉ ምንጮቻችን ትዝብታቸውን ያስቀምጣሉ፡፡ 
በመግቢያው ላይ እንደተገለጸው ማኅበረ ቅዱሳን፣ ወደ ጅምላ የስም ማጥፋት ዘመቻ ከመሸጋገሩ በፊት የቀደመው ስልቱ ነጥሎ መምታት የነበረ መሆኑን ብዙዎች ይናገራሉ፡፡ አንበሳ ከዱር እንስሳት መንጋ መካከል ለመንጠቅ ሲፈልግ፣ በአንዱ ላይ አተኩሮ እስኪይዘው ድረስ እንደሚያሳድደው ሁሉ፣ የሚውጠውን ፈልጎ እንደሚያገሣ አንበሳ በዙሪያችሁ ይዞራል ለተባለው ባላጋራችን ዲያብሎስ፣ የግብር ልጆች የሆኑት ማኅበረ ቅዱሳንም በቅጥረኞቹ በኩል ነጥሎ በመምታት ስልቱ ብዙዎችን ግዳይ እየጣለ መሆኑ የማይረሳ ሲሆን፣ አሁንም እንደ አስፈላጊነቱ ይህን ስልት እየተጠቀመበት ቢሆንም፣ ለመብቱ የሚታገልና ማኅበረ ቅዱሳን በቤተ ክርስቲያናችን ዕድል ፈንታ እንዳይኖረው የሚቃወም ትውልድ እየተነሣ መሆኑ ስልቱን ጊዜ ያለፈበት (Out dated) እያደረገው መጥቷል፡፡ በዚህ በኩል በመምህር አሰግድ ሣህሉ ላይ የከፈተው ነጥሎ የመምታት ስልቱ እንዳልያዘለትና ነውራችሁን ይፋ አደርጋለሁ እያለ ያሻውን የሚያስፈጽማቸውን ቅጥረኛ ጳጳሳቱን ሁሉ በሕግ ፊት እያዋረዳቸው መምጣቱ ተመልክቷል፡፡ ማኅበረ ቅዱሳን በመምህር አሰግድ ሣህሉ ላይ የሸረበውና እስከ ኮሌጁ ዲን አቡነ ጢሞቲዎስ ድረስ ባደራጃቸው ጀሌዎቹ በኩል የሞከረው ነጥሎ የመምታት ስልቱ በሕግ ፊት ጭምር መክሸፉን የሚገልጽ ዘገባ በቀጣይ እንደምናስነብብ ከወዲሁ መግለጽ እንወዳለን፡፡
ይህ በእንዲህ እንዳለ የቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ ተማሪዎች ያሰሙትን ተቃውሞና በማኅበረ ቅዱሳን ላይ ያወጡትን ጠንካራ የአቋም መግለጫ በማግሥቱ የወጡ የግል ጋዜጦች አለመዘገባቸው የጋዜጦቹን ማንነት ያጋለጠ ተግባር ነው ሲሉ አንዳንድ የቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ ተማሪዎች መናገራቸውን ምንጮቻችን ገልጸዋል፡፡ ተማሪዎቹ ለአብነት የሚጠቅሱት በየሳምንቱ ዐርብ የሚታተመውንና “ፍትሕ” የተባለውን አፍቃሬ ማኅበረ ቅዱሳን የሆነውን ጋዜጣ ነው፡፡ ጋዜጣው በሚያዝያ 7 ዕትሙ በፊት ገጹ “የሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ ተማሪዎች ቅሬታቸውን ለፓትርያርኩ አቀረቡ” በሚል ርእሰ ዜና የሠራ ቢሆንም፣ በዜናው ሐተታ ውስጥ ግን ተማሪዎቹ በዋናነት የአቋም መግለጫ ያወጡበት የማኅበረ ቅዱሳን ጉዳይ ፈጽሞ ሳይጠቀስና ከዚህ ቀደም የተቃውሞ ድምፅ ያሰሙባቸውን የከረሙ ጉዳዮች ፈጽሞ ባልተነሡበት ሁኔታ እንዳዲስ በማቅረብ ዋናውን ጉዳይ አቅጣጫ ለማስለወጥ ሆነ ብሎ የተዘጋጀ አስመስሎታል፡፡ ከምንም በላይ ደግሞ ጋዜጠኛው ሳይጋደል አክሊለ ሰማዕትን ለመቀዳጀት የከጀለ ይመስል፣ የዘራውን ማጨዱን “እንግልት” አድርጎ መዘብዘቡ ትልቅ ትዝብት ላይ እንደጣለውና “ፍትሕ ጋዜጣ ሆይ! ከማን ወገን ነህ?” የሚል ጥያቄ እንዳሰነዘረበት ተጠቁሟል፡፡ ጋዜጠኛው “ምንጮቻችን” ያላቸውና “ፓትርያርኩም የተማሪዎቹን ቅሬታ አድምጠው ‘ይህ በአስቸኳይ ትእዛዝ የማስተላልፍበት ጉዳይ ነው’” ሲሉ ምላሽ እንደሰጡ የነገሩት ክፍሎች፣ የመግለጫውን ፍሬ ነገር ለምን ቀየሩት? ወይስ ጋዜጠኛው ይሆን የለወጠው? ሲሉ ታዛቢዎች ይጠይቃሉ፡፡ በብዙዎቹ የግል ጋዜጦች ውስጥ በአንድም በሌላም መንገድ የማኅበረ ቅዱሳን እጅ መኖሩን የሚናገሩት እነዚሁ ምንጮች፣ ጋዜጦቹ ማኅበረ ቅዱሳን የሚፈልጋቸውን ጉዳዮች ብቻ እያነፈነፉ ለማኅበረ ቅዱሳን ወግነው ከመዘገብ ውጪና የማኅበሩን “በጎ ገጽታ” ከመገንባት በቀር አንድም ጊዜ እንኳ የእርሱን ድክመትና መሠሪነት ሲዘግቡ እንደማይስተዋሉ ይናገራሉ፡፡ ይህም ጋዜጦቹ የቆሙት የማኅበረ ቅዱሳንን ፖለቲካዊ አጀንዳ ለማስፈጸም እንጂ፣ በገለልተኛነትና በነጻነት የሁሉንም ሐሳብ ሚዛናዊ ሆነው ለማስተናገድ አለመሆኑን የሚጠቁም ምስክር ነው፡፡    
ይህ በእንዲህ እንዳለ የተማሪዎቹ የአቋም መግለጫ በቀረበበት በዚሁ ዕለት፣ ቋሚ ሲኖዶሱ በሐዋሳ ለግጭቶች መንሥኤ የሆነውን በማኅበረ ቅዱሳንና ሐዋሳ ላይ በሚገኘው የማኅበረ ተስፋ ኪዳነ ምሕረት መካከል የተፈጠረውን ችግር ለመፍታት ባደረገው ስብሰባ በግጭቶቹ ዙሪያ ውሳኔዎችን አሳልፏል፡፡ በዚሁ መሠረት፡-
1.      አዲስ ተሹመው በሀገረ ስብከቱ የተመደቡትና ለማኅበረ ቅዱሳን ሽፋን ሲሰጡ የነበሩት ሊቀጳጳስ አቡነ ገብርኤል እስከ ግንቦቱ የሲኖዶስ ስብሰባ ወደ ሀገረ ስብከቱ እንዳይሄዱና ለጊዜው ሀገረ ስብከቱን ቅዱስ ፓትርያርኩ በሞግዚትነት እንዲያስተዳድሩ፣
2.     ማኅበረ ቅዱሳንና ማኅበረ ተስፋ ኪዳነ ምሕረት በሀገረ ስብከቱ ውስጥ በሚከናወኑ ማናቸውም የቤተ ክርስቲያኒቱ ጉዳዮች ውስጥ ምንም ዐይነት ጣልቃ ገብነት እንዳያካሂዱ፣
3.     በማኅበረ ቅዱሳን ኀይለኛ ውንጀላ በሐዋሳ ከተማ የሚገኙ የገብርኤል፣ የሥላሴ፣ የጊዮርጊስና የተክለ ሃይማኖት አድባራት አስተዳዳሪዎች የማኅበረ ተስፋ ኪዳነ ምሕረት ደጋፊዎች ናቸው የሚለውን ክስ ቋሚ ሲኖዶሱ ውድቅ በማድረግ በየተመደቡበት ቦታ አገልግሎታቸውን እንዲቀጥሉ ውሳኔዎችን አሳልፏል፡፡
ውሳኔው ማኅበረ ቅዱሳንን አንገት ያስደፋና ተሰሚነቱና ጫና መፍጠሩ እየተሸረሸረ መምጣቱን የሚያሳይ መሆኑን ምንጮቻችን ይገልጻሉ፡፡
ይህ በእንዲህ እያለ የቅዱስ ሲኖዶሱን ውሳኔ ተከትሎ በአንዳንድ የሀገራችን ክፍሎች የተቀሰቀሰው አንባጓሮ ማኅበሩ ለእግዚአብሔር፣ ለቅድስት ቤተክርስቲያንና ለመንግሥት አስተዳደር ስፍራ በሌላቸው ጨካኞች የሚመራ በለስ ቢቀናው ማንንም አጋድሞ ከማረድ የማይመለስ ቡድን መሆኑን የማያሳይ ሆኗል፡፡ በተለይም በሆሳዕና በአል ዋዜማ ቅዳሜ በ8/8/2003 ዓ.ም ቅዱስ ሲኖዶስ ባሉበት እንዲቆዩ ከወሰነላቸው አስተዳዳሪዎች መካከል የቅዱስ ገብርኤልን  ቤተ ክርስቲያን አስተዳዳሪ የማህበሩ መናጆ የሆኑ ሁለት መሪጌቶች በጋቢ አፍነው ለመግደል ሲታገሉ ድንገት በደረሰች አንዲት የሰንበት ተማሪ ጩኸት አስተዳዳሪው ከሞት ተርፈዋል፡፡ የወጠኑት ያልሆነላቸው መሪጌቶች በደመነፍስ ባነሱት ቆንጨራ ጩኸቱን ሰምተውና ተሯሩጠው ከመጡ የሰ/ት/ቤቱ አገልጋዮች መካከል አለማየሁ የተባለውን የሰንበት ት/ቤት አገልጋይ እጁን ሲዘነጥሉ፤ አሸናፊ የተባለውን የሰንበት ት/ቤቱን ምክትል ሊቀመንበር ደግሞ በያዙት ቆንጨራ አናቱ ላይ የከፋ ጉዳት አድርሰዋል፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘ አቶ ዘለቀ ሶርሳ የሚባለው ግለሰብ በመኪና ጭኖ ባቀረበው ድንጋይ ልጅ አዋቂ ሳይለይ በተፈፀመው ጥቃት ደግሞ ወ/ሮ እናኑ መኩሪያ የተባሉ እናት ቀኝ እጃቸው ከመሰበሩም ሌላ በቅጥቀጣው ሰውነታቸው ክፉኛ ተጎድቷል፡፡ እኒህን እናት ጨምሮ በርካታ ሰዎች ላይ ከፍተኛ ጉዳት ያደረሰው የማኅበረ ቅዱሳን ወጀብ ፈጥኖ በደረሰው የሰላም አስከባሪ ተኩስ ባይገታ ኖሮ ሊደርስ የሚችለው እልቂት ከዚህ ይከፋ እንደነበር በስፍራው የነበሩ የዐይን እማኞች መስክረዋል፡፡
የመቀደሻ አልባሳት መገበሪያና ጧፍ የሌላቸው ገዳማትን ለመርዳት እያለ በተዘጉ አብያተ ክርስቲያናት ስም ገንዘብ ሲያካብት የኖረው ማኅበረ ቅዱሳን፤  ባከማቸው ገንዘብ ለወንጌል የተከፈቱ ደጆችን ለማዘጋት መትጋቱ፣ ከሀይማኖት ውጪ ለሆነ አላማው ስኬት አብረውት ያልተሰለፉትን መጉዳቱ፣ በተለይም አበይት በዓላትን አስታኮ የሚለኩሰው እሳትና የሚያደርሰው ጥፋት በየትኛውም መመዘኛ ኦርቶዶክሳዊ ወይም ክርስቲያናዊ ባልሆነ ሸፍጥ ውስጥ እንዳለ ጠቋሚ ነው፡፡ በተለይ ለተከታታይ አመታት አብይ ጾምን ተከትሎ በሚፈጥረው ውዥንብር የበረከቱን ወቅት የመርገምና የመከራ እንዳደረገው የታዘቡ አንድ አረጋዊ ዓብይ ጾም ለማኅበረ ቅዱሳን ‹‹ረመዳኑ ነው እንዴ?›› ብለው መጠየቃቸው ተሰምቷል፡፡ የያዛቸው አባዜ እስከዚያ አያደርሳቸውም እንጂ ለከርሞ አብሮን ከዘለቁ የከዚ በፊቱን ልብ ብሎ ያላየ የዚህ ጽሑፍ አንባቢ መጪውን የ2004 ዓብይ ጾም ‹‹ረመዳን›› አርገውት በሌላ በከፋ መከራና ሀዘን እንደሚያያቸው ስንጠቁም ‹‹አንባቢው ያስተውል›› የሚለውን የመጽሐፍ ቃል እንዲያስታውሰው በማስገንዘብ ነው፡፡
በሌላ በኩል ደግሞ የማኅበረ ቅዱሳን አባል በመምሰል ሙሴ ነኝ በማለት ለብፁዕ አቡነ ገብርኤል ስልክ ደውለው የነበሩ የገፈቱ ቀማሽ ወጣቶች ሲናገሩ፤ አቡነ ገብርኤል ‹‹አይዟችሁ በርቱ የወያኔ ካድሬ የሆኑት ፓትርያርክ ትንሽ እንቅፋት ሆነውብኛል፡፡ እናንተ በርቱ ምንም የሚመጣ የለም፤ እኛ እናሸንፋለን ›› ሲሉ የማበረታቻ ቃል መናገራቸውን  በሞባይል ከተቀረጸው ድምፃቸው ማረጋገጥ ችለናል፡፡
በሌላም በኩል  መንፈሳዊ ተቋም ነኝ ካለው ማኅበር በእጅጉ ተሽለው የተገኙት የጥበቃ ሰራተኞችና፣ የክልሉ ባለስልጣናት እንደከዚህ ቀደሙ የቤተ ክርስቲያኑ በር እንዳይዘጋ ‹‹ነገ ህፃን አዛውንቱ የዘንባባ ዝንጣፊ ይዞ የሚያከብረው የሆሳዕና በዓል ነው፤ ደጁ መቆለፍ የለበትም፤›› በማለት ሀዘኑ እጥፍ ድርብ እንዳይሆንና ዝንት ዓለም የሆሳዕና በዓል በመጣ ቁጥር የሚታወስ ጠባሳ እንዳይኖር ስለ አደረጉት ማስተዋል የተመላበት ውሳኔ በቅድስት ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን እንዲሁም የቤተ ክርስቲያን ራስ በሆነው መድኃኔ ዓለም ኢየሱስ ክርስቶስ ስም ሳናመሰግንናቸው አናልፍም፡፡ ይህንንም ተከትሎ የሆሳዕና በዓል የከተማው ወጣቶች ለጥምቀት በዓል በገዙት ምንጣፍ ግቢው አጊጦ ሀዘኑን በሚያስረሳ ድምቀት ‹‹ሆሳዕና ለዳዊት ልጅ ሆሳዕና አቤቱ አድን አቤቱ አቅና›› በሚሉ ዝማሬዎች ደምቆ ተከብሯል፡፡
EBS የቴሌቪዥን መንፈሳዊ አገልግሎት እየተጠናከረ መሄዱ ተመለከተ
በዐረብ ሳት እየተላለፈ ባለው EBS የቴሌቪዥን መርሐ ግብር ላይ በመጋቤ ሐዲስ በጋሻው ደሳለኝ፣ በመምህር በሪሁን ወንድወሰን፣ በመምህር ያሬድ አደመ እና በዘማሪ ዲያቆን ትዝታው ሳሙኤል የተጀመረው በየሳምንቱ እሑድ ከ4፡30-5፡00 ሰዓት የሚተላለፈው የግማሽ ሰዓት የቴሌቪዥን መንፈሳዊ አገልግሎት፣ ወቅታዊ በሆነ የቤተ ክርስቲያን ጉዳይ ላይ መልእክት አስተላለፈ፡፡
ለመልካም ነገር ባልታደሉ አሉባልተኞች ብዙ ሲነቀፉ የነበሩት የየEBS መንፈሳዊ አገልግሎት ጀማሪ አገልጋዮች የሆኑት እነመጋቤ ሐዲስ በጋሻው፥‹‹
ይሁን እንጂ ለግብር አባታቸው ለዲያብሎስ እንጂ ለቅድስት ቤተ ክርስቲያንም ሆነ የእናት ቤተ ክርስቲያንን ጉዳት ማየትም ሆነ መስማት ለሚሰቃቸው የቤተ ክርስቲያን ልጆች ቦታ በሌላቸው የማቅ ቅጥረኞች ጉዳዩ ለጠላት ደስታ ለምዕመናንና ምዕመናት የልብ ስብራት መሆኑን ያስተዋሉ፣ ‹‹እነሱ በክፋት እናንተ ደግሞ ለበጎ በሆነ ቅንዓት ብትገለጡ ምናለ? ለምን ዝም አላችሁ? የእናንተ ዝምታ ለእነርሱ የልብልብ ሰጥቷቸዋል፡፡ ጉዳዩን ዓለም በተዛባ ሁኔታ እየሰማው ነው፣›› የሚል ግፊት በማሣደራቸው፤ ጉዳዩን ይፋ ለማድረግ የተገደዱት የስርጭቱ ባለቤቶች በውሸት ግራ ለተጋባው ሕዝብ እረፍት፣ ጉዳዩን በዚህ መልኩ ላላየው ፣ማስተዋል፣ ለቤተ ክርስቲያን ልጆች ተስፋ ሰጪ የሆነ መልዕክትን አስተላልፈዋል፡፡ እንደ ቀድሞ ማህበረ ቅዱሳን በምላሱ የነደፋቸው የሚመረዙበት እርሱ ቤታችሁ አይደለም ያላቸው ሁሉ ልባቸው እያወቀ እንደርሱ በሀይልና በተንኮል መገዳደር ስላልቻሉ እያለቀሱ ከቤታቸው እየወጡ በማያምኑበት መስመር ለመጓዝ የተገደዱበት ዘመን አብቅቷል፡፡ ዛሬ ከቤቱ ንቅንቅ የሚል አይኖርም ያሉት የፕሮግራሙ መሪዎች ሕዝቡም ቢሆን እንደአለፈው ዘመን እነሱ ጣት በቀሰሩበት ላይ ድንጋይ ለመወርወር ሆን ብሎ እንደማይነሳ ከዓለምና ከሞት ማጀት ጎትቶ ያወጣን የእነዚህ ተነቃፊዎች ዝማሬና ስብከት አይደለም እንዴ? እያለ ከነሱ ውንጃላ ይልቅ ተነቃፊቹ የሰበኩለት ወንጌል እንዳተረፋቸው መናገራቸውን ጠቆም አድ
በተለይም በተለያየ ጊዜ የሚነሳበትን የፓለቲካ ጥያቄ የትኩረት አቅጣጫ ለማስቀየር የአባይን ወንዝ ጉዳይ እያቀነቀነ ሕዝቡን በሚፈልገው መንገድ ሲነዳ እንደነበረው የግብጽ አስተዳደርዛሬም ሕዝባችን ለቅዱሳን ያለውን ከንጹህ ልብ የሚወጣ ፍቅር በመረዳት በቅዱሳን በተለይም አምላክን በወለደች በእመቤታችን የሚመጣበትን እንደማይወድ በመረዳት የጠሉዋቸውን ለማስጠላት በተሐድሶና በሌላ ውንጀል ማኅበሩ አገልጋዩን ከተገልጋዩ ለማጋጨት የሚያደርገው ጥረት እንዳለፈው ዘመን እንደማይሳካለት አስገንዝበዋል፡፡
አገልግሎቱ የቤተክርስቲያንን በጎ ነገር በሚናፍቁ በቅንነት በገባቸው መንገድ ያለውን እድልና ቴክኖሎጂ ለሰይጣን ውርደት፣ ለሕዝብ ጥቅምና ለእግዚአብሔር ክብር ለማዋል አቅምና እድሜያቸው ከሚፈቅደው አልፈው እየሰሩ ያሉትን ያደለው ‹‹እጁን ለበጎ በማበርታት በገንዘብ፣ በዕውቀት(በሀሳብ) በጉልበትና በልዩ ልዩ አስተዋጽኦ ሲደግፍ ያልታደሉት ደግሞ አለመተባበራቸው አንድም በጎ አስተዋፅኦ አለማድረጋቸው ሲያስገርም እንደ እነ ጦቢያና ሰንባላጥ ዳር ቆመው ‹‹ቤተክርስቲያን የማታውቀው›› እያሉ የአለማውያን መጽሔት ማጣፈጫ መሆናቸው አይ ቤተ ክርስቲያን ስንቱን ተሸክመሻል አሰኝቷል፡፡
እንደ እነ ነህምያ እንደ አንድ ልብ መካሪ እንደ አንድ ቃል ተናጋሪ በመሆን ‹‹የሰማዩ አምላክ ያከናውንልናል እኛም ባሪያዎቹ ተነስተን እንሰራለን›› ያሉት አገልጋዮች ከየኪሳቸው በማውጣት ለ4ት የጀመሩት አገልግሎት ሰምሮላቸው አገልግሎታቸውን የሚያስፋፉበት ድጋፍ በቅርብ ከሚያውቋቸውና ትጋትና ድካማቸውን በመልካም ከተረዱላቸው ጥቂት ሰዎች በተደረገላቸው ድጋፍ አገልግሎቱን ከ30 ደቂቃ ወደ አንድ ሰዓት ለማሳደግ ቆርጠው ተነስተዋል፡፡
ይህ በእንዲህ እንዳለ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ፓትርያርክ ሰሞኑን (በ2003 ዓ.ም) ባከበርነው የትንሳኤ በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት በመላው ዓለም ለሚተላለፈው ታኦሎጎስ የEBS ፕሮግራም ቡራኬና ቃለ ምዕዳን ሰጥተዋል፡፡ የአገልግሎቱን በረከት ለቴክኖሎጂው ቅርብ በሆነ ማስተዋል ከሌሎች ቀድመው የሚገነዘቡት ቅዱስ ፓትሪያርኩ ‹‹አይዟችሁ በርቱ! እደጉ! ልጆቼ›› ከሚለው የዘወትር ተስፋና ማበረታቻ ባሻገር በመንበረ ፓትርያርክ የስብከተ ወንጌል አደራሽ ተገኝተው ለ EBS ፕሮግራም አዘጋጆችና አቅራቢዎች እንዲሁም በመላው ዓለም ለሚገኙ ሕዝበ ክርስቲያን ባስተላለፉት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት፥ ‹‹የክርስትና አስኳሉ ፍቅር ነውና በሩቅም በቅርብም ያለን ሁላችን በፍቅር እንኑር›› በማለት አባታዊ ምክርና መመሪያ አስተላልፈዋል፡፡ ይህን ቡራኬና የፍቅር መልዕክት በEBS ሲተላላፍ ያዩና የሰሙ ፕሮግራሙ ወይንም ስለEBS አገልግሎት ከዚህ በኋላ ምን ይሉ ይሆን? እነርሱ የሚሉትን ባያጡም እኛም ያምንለውን ብለናል፡፡ አምላክ በነገር ሁሉ ማስተዋልን ይስጥልን፡፡
ወግ ማዕርግ ለሆናችሁን በቃለ ወንጌልና በጥኡም ዝማሬ የቅድስት ቤተክርስቲያን ፈርጥ የሆናችሁን የEBS አዘጋጆችንም ብዙ፤ እልፍ አዕላፍም ሁኑልን፡፡ ዘወትር በመልካም እንድናያችሁ አምላክ ከናንተ ጋር ይሁን እንላለን፡፡

‹‹የባርነት ልጆች››(ገላ. 4፥21-31) "DejeSemay.org

የገላትያ መልእክት ዐቢይ ዓላማ በክርስቶስ አምነው ከጸጋው ቃል ወደ ኋላ በመመለስ እውነትን ይቃወሙ ለነበሩ ምዕመናን የተጻፈ ነው፡፡ ሐዋርያው በዚህ መልእክት ላይ የተለያዩ ምሳሌዎችን በመጠቀም እንዲሁም በቀደመው ኪዳን ስለበነሩ ነገሮች በመጥቀስ የገላትያ ምዕመናን አስቀድሞ ከተሰበከላቸው የክርስቶስ ወንጌል የተለየ ወንጌልን የሚሰብክ ሰውም ይሁን መልአክ የተረገመ ይሁን!›› በማለት በሐዋርያዊ ሥልጣኑ ይገዝታል (ገላ. 18)፡፡
በገበሬ እርሻ ላይ ምርጥ ዘር ከተዘራ በኋላ ዘሩ መብቀል ሲጀምር ቀድሞ ያልነበረ ነገር መታየቱ አይቀርም፡፡ ይህም የሚሆነው መልካም ነገር ሁሉ ተቃዋሚ ስላለበት ነው፡፡ ከዚህም የተነሣ መልካም ነገር ኃላፊነት ነው፡፡ ጥበቃና እንክብካቤም ይፈልጋል፡፡ ያለበለዚያ ለፍሬ አይበቃም፡፡ ጌታም በእርሻው ላይ ስለተዘራው መልካም ዘር ከተናገረ በኋላ ሰዎቹ ሲተኙ ጠላት መጥቶ እንክርዳድ እንደዘራና እንደሄደ ለደቀ መዛሙርቱ ሲናገር እናያለን፡፡ (ማቴ. 1324-30)
በዚህ ዘመንም በእውነተኛው የወንጌል አገልግሎት ላይ እንክርዳድ ለመዝራት የተሠማሩ፣ ሕዝብ የክርስቶስን ወንጌል እንዳይሰማ በተረትና በወግ እንዲሁም የራሳቸውን የጥቅም ፍላጎት ለማሳካት በሚያመች ሁኔታ ተብትበው ሕዝብን ለባርነት የሚወልዱ ብዙ ናቸው፡፡
እነዚህ ወገኖች ቀድሞውንም የጽድቅ አገልጋዮች አይደሉም፡፡ መቼም ሰው ሁሉ ባለበት መንፈሳዊ ደረጃና ኑሮ ከታመነ፣ ይህ ሰው ለእግዚአብሔር መንግሥት ቅርብ ነው፡፡ ነገር ግን መንፈሳዊውን አገልግሎት አንድ የትርፍ መንገድ አድርጐ መያዝና ለማይኖሩበት እውነት መሟገትን የመሰለ የድፍረት ኃጢአት የለም፡፡
የክርስቶስ ወንጌልን የሚሰብኩትን ስም እየሰጡ እንዳያገለግሉ በማድረግ፣ ለክርስቶስ ክብር የሚቀርበውን የምሥጋና መሥዋዕት /ዝማሬ/ ሁሉ የሚያወግዙ፣ ይህ የእኛ አይደለም በሚል ፈሊጥ የሁሉም ነገር ጀማሪዎች እኛ እንደሆንን እንድናስብና ከእውነተኛው አምላክ እንድንለይ የሚያደርጉ፣ የክርስቶስ ስም የተጠራበት ዝማሬም ሆነ ስብከት የማይጥማቸው እነዚህ የመስቀሉ እንቅፋትና የባርነት ልጆች ናቸው፡፡
ወገኖቼ ! በወንጌል አምነናል እያልን ክርስቶስን የሚስጠላ ማንነት ካለን ስሙ ሲጠራም የምንደነግጥ ከሆንን ራሳችንን መፈተሽ ይኖርብናል፡፡ የማን ስም ይሰበክ? የማን ማዳን ይነገር? የማንስ ስም ይመስገን? በስሙ እየተጠራን እርሱን ከመቃወም ያድነን!
ሳይማሩ አውቃለሁ እንደማለት ያለ ድንቁርና የለም፡፡ የብዙዎች ችግር ይህ ነው፡፡ የሚማር መንፈስ የሌላቸውና ለመቃወም ብቻ የሚኖሩ፣ ግመል እየዋጡ ትንኝ የሚያጠሩ፣ ተረፈ ፈሪሳውያን ዛሬም ሞልተዋል፡፡ እነዚህ ወገኖች በገበያ ግርግር ተንጠላጥለው የቤተ-ክርስቲያንን ዓውደ ምሕረትና ልዩ ልዩ የአገልግሎት ሥፍራ የተቆጣጠሩ ሲሆን የጽዋ ማኅበራቸው አባል ያልሆነ ‹‹ኦርቶዶክሳዊ አይደለም›› በማለት ሰውን ሁሉ የአሳባቸው አገልጋይ (ባሪያ) ለማድረግ የሚተጉ ናቸው፡፡
እንደሚታወቀው የሽሽግር ወቅት /Transition Period / ተብሎ የሚጠራው ጊዜ ሲከሰት ይልቁንም የመንግሥት ለውጥ ሲደረግ የሚሞቱና ትንሣኤ የሚያገኙ ወገኖች ይኖራሉ፡፡ አንዳንዶች ወደ ድህነት ቀጠና ይወርዳሉ፡፡ ሌሎች በግርግሩ ዘርፈው ከባለጠጎች ጎራ ይቀላቀላሉ፣ አንዳንዶችም ሕይወታቸውን በማጣት ወደሞት ይሻገራሉ፡፡ በአንድም በሌላም የመጣው ለውጥ ብዙ ለውጦችን ይወልዳል፡፡
በአገራችን ታሪክም የደርግ መንግሥት ሲወድቅና አሁን በሥልጣን ላይ ያለው መንግሥት ሲተካ ይህ ሁኔታ ታይቷል፡፡ ራሱን ‹‹የቅዱሳን ማኅበር›› እያለ የሚጠራው ይህ የጽዋ ማኅበር ዛሬ ለደረሰበት ደረጃ የበቃው በዚህ ግርግር ነው፡፡ እየቆየ ሲሄድ ግን ራሱን እንደ አንድ ‹‹ሲኖዶስ›› መቍጠር ጀመረ፡፡ ብዙዎችም ለባርነት ወለደ፡፡ የመጣበትን ስለረሳው የሚሄድበት ቢጠፋው አያስደንቅም፡፡ ይሁን እንጂ ዛሬም በንስሓ ለመመለስ በሩ ክፍት ነው፡፡
የእግዚአብሔር ቃል፡- ‹‹በነጻነት ልንኖር ክርስቶስ ነጻነት አወጣን›› (ገላ. 5፥1) ይላል፡፡ ነጻነት ሁለንተናዊ ነው፡፡ ሰው ለተገዛለት ለዚያ ባሪያ እንደሆነም መጽሐፍ ቅዱስ ይነግረናል፡፡ ሰው ነጻ ግዛት ባለመሆኑ ለአንድ ጌታ መገዛቱ የግድ ነው፡፡ በክርስቶስ ያገኘነው መዳንም ከብዙ ባርነት ነጻ የወጣንበት ሲሆን ክርስትናም ራሳችንን ለዚህ ጌታ ባሪያ አድርገን የሰጠንበት የፍቅር ግዛት ነው፡፡ ቀድሞ የማይገዛንና በእኛ ላይ ያልሠለጠነ አልነበረም፡፡ ከመዳን በፊት የነበረን መታወቂያ ሁሉ የሚያሳፍር ታሪክ መዝገብ ነው፡፡ ኢየሱስ ክርስቶስ ግን የጽድቅ ባሪያዎች አድርጐናል፡፡
ወገኖቼ! አገልግሎታችንን መፈተሽ ይገባል፡፡ ሆዳችን አምላካችን ሆኖ ዛሬም ጥቅም የሚገዛንና በመንፈሳዊ አገልግሎት ስም የራሳችንን ፍላጎት ለማሳካት የቆምን ከሆንን የባርነት ልጆች መገለጫ ይህ ነው፡፡ መንፈሳዊ አገልግሎት የጸጋና የጥሪ ጉዳይ እንጂ የትምህርት ማስረጃ (የዲፕሎምና የዲግሪ ወዘተ…) ጉዳይ አይደለም፡፡ እውቀት እንጀራ ለመብላት ይጠቅም ይሆናል፡፡ ለመንፈሳዊ አገልግሎት ግን ጥሪና ጸጋ ያስፈልጋል፡፡ ሰዎችን ከተለያዩ የትምህርት ተቋማት በመመልመል የቤተ-ክርስቲያን አገልጋዮች ለማድረግ ማቀድና በዚህም ቤተ ክርስቲያንን ሙሉ በሙሉ ለመቆጣጠር ማሰብ፣ በገንዘብ ኃይል በመደራጀትም ተከታይ ለማብዛት ማቀድ፣ ለጊዜው አሸናፊ ሊያስመስል ይችላል፡፡ ኢየሱስ ክርስቶስ ግን በትንሣኤው ሞትን ሳይቀር የረታ በመሆኑ የወንጌሉን የምሥራች የሚገታው የለም፡፡ የወንጌል አገልጋዮችንም በማሳደድ እውነትን ማስቀረት አይቻልም፡፡
የአብርሃም ልጆች ብዙ ቢሆኑም በዋነኛነት ግን የሚታወቁት ሁለቱ እስማኤልና ይስሐቅ ናቸው፡፡ እነዚህ ሁለት ልጆች የአብርሃም ልጆች ቢሆኑም የተለያየ ማንነት አላቸው፡፡ እስማኤል ከእግዚአብሔር የተስፋ ቃል ውጪ የተወለደና በሥጋ ልደት የተገኘ ነው፡፡ ይስሐቅ ደግሞ አስቀድሞ የተስፋ ቃል የተነገረለትና በእግዚአብሔር የተስፋ ቃል የተወለደ እውነተኛ የአብርሃም ወራሽና የተስፋው ቃል ፍጻሜ ነው፡፡
በእነዚህ ሁለት ልጆች መካከል ትልቅ ልዩነት አለ፡፡ ይኸውም የእግዚአብሔር የተስፋ ቃል የሚፈጸመው እንደ ቃሉ በተወለደው በኩል በመሆኑ እንደ ሥጋ ፈቃድ የተወለደው እስማኤል ይስሐቅን የሚጠላና የሚያሳድድ እንደነበር ተገልጧል፡፡ ‹‹ነገር ግን እንደ ሥጋ የተወለደው እንደ መንፈስ የተወለደውን በዚያን ጊዜ እንዳሳደደው ዛሬም እንዲሁ ነው›› (ገላ. 429)፡፡
እንደ ሥጋ የተወለደ በማለት የገለጠው እስማኤልን ነው፡፡ ይኸውም እስማኤል የተወለደው አብርሃም መውለድ በሚችልበት ወቅት በአብርሃምና በሣራ ምክር ከባሪያይቱ ከአጋር ነው፡፡
በዚህ አሳብና ምክር እንዲሁም ሥራ ውስጥ እግዚአብሔር የለም፡፡ እስማኤል ቢወለድም የጠብና የሁከት ምክንያት እንጂ የቤቱ ደስታ አልሆነም፡፡ ዛሬም በእግዚአብሔር ቤት ውስጥ እንደ እስማኤል የተወለዱ አሉ፡፡ እነዚህ ወገኖች በእግዚአብሔር ቃል የተወለዱ ሳይሆኑ በሥጋዊ እውቀትና በራስ ችሎታ እንዲሁም በሥጋ ምክር የልጅነት እውቅና የተሰጣቸው ናቸው፡፡ ሌላው ቀርቶ ብዙዎቹ የአገልግሎት መሥፈርትን እንኳ ሳያሟሉ የአገልግሎት ሥፍራዎችን የተቆጣጠሩ ጨዋዎች ናቸው፡፡ (ጨዋ የሚለው ቃል በቤተ ክርስቲያን ቋንቋ ያልተማረ ማለት ነው)፡፡
እንደ እነዚህ ያሉ በመወለዳቸው ዛሬ ቤተ-ክርስቲያን ትታመሳለች፡፡ ሌላው ቀርቶ ገደባቸውን እንኳ ባለማወቃቸው ‹‹ቅዱስ ሲኖዶስ›› እያለ ተክተው ለመሥራት የሚያስቡና የሚያወግዙ እንዲሁም የራሳቸውን አሳብ ለማስፈጸም የሚሯሯጡ ናቸው፡፡ እስማኤል ይስሐቅን እንደ ጠላው፣ አጋርም ሣራን እንደናቀች እነዚህም ወገኖች ከእነርሱ ውጪ ያለውን እንዲሁ የሚመለከቱ ናቸው፡፡ እንደ መንፈስ ፈቃድ የተወለደው ይስሐቅ ነው፡፡ ይስሐቅ የተወለደው በእግዚአብሔር ፈቃድና ችሎታ ነው፡፡ አብርሃምም ሣራም ምንም ማድረግ በማይችሉበት ወራት የተወለደ የእግዚአብሔር ስጦታ ነው፡፡ ይህም የእግዚአብሔር ልጆች ተብለን ለመጠራት የሚያበቃን ከእርሱ የሆነልን ነገር ብቻ መሆኑን ይገልጣል፡፡ ክርስትና የዘር ውርስ አይደለም፡፡ ከእግዚአብሔር ቃል ጋር በመስማማት የተሰጠን የመዳን ጸጋ ነው፡፡ ቃሉም እንዲህ ይላል ‹‹ጸጋው በእምነት አድኖአችኋልና፤ ይህም የእግዚአብሔር ስጦታ ነው እንጂ ከእናንተ አይደለም፤ ማንም እንዳይመካ ከሥራ አይደለም›› (ኤፌ. 2፥8)፡፡ እንግዲህ በልጅነት ለመጠራት፣ ለማገልገልና ለመውረስ የእግዚአብሔር ጸጋ ያስፈልጋል፡፡ ቃሉም ‹‹የእግዚአብሔር ስጦታ ነው እንጂ ከእናንተ አይደለም›› ይላልና፡፡
ሐዋርያው እነዚህን ሁለት ልጆች በምሳሌነት ያነሣው ‹‹ዛሬም እንዲሁ ነው›› የሚለውን ለመግለጥ ነው፡፡ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክሳዊት ቤተክርስቲያንም ያለውን ሁኔታ ስንመለከት ዛሬም እስማኤላውያን እንደ ተስፋ ቃሉ የተወለዱትን ሲቃወሙና ሲያሳድዱ እናያለን፡፡ ከየዓውደ ምሕረቱ፣ ከየአድባራቱ፣ ከየገዳማቱ ወዘተ፡፡ በእርግጥም እውነተኛ ኦርቶዶክሳውያን የቤተ-ክርስቲያን ልጆች ዛሬም እንደሚሰደዱ ቃሉ ያረጋግጣል፡፡ ይሁን እንጂ እንደ ተስፋ ቃሉ ወራሾች እነርሱ ናቸው፡፡ ቃሉም እንዲህ ይላል፡- ‹‹የባሪያይቱ ልጅ ከጨዋይቱ ልጅ ጋር አይወርስም ባሪያይቱን ከልጅዋ ጋር አውጣት፤ ስለዚህ ወንድሞች ሆይ የጨዋይቱ ልጆች ነን እንጂ የባሪያይቱ አይደለንም›› (ገላ. 430-31)፡፡
ከላይ እንደተገለጠውና ‹‹ባሪያይቱን ከልጅዋ ጋር አውጣት›› እንደተባለ ዛሬም የእግዚአብሔር ፍርድ ሲገለጥ አሳዳጆች ይወጣሉ፡፡ ልጆች ይወርሳሉ፡፡ ለውርስ የሚያበቃው ከጨዋይቱ መወለድ ነው፡፡ የሚሰደዱ እንጂ የሚያሳድዱ የክርስቶስ አይደሉም፡፡
ወስብሐት ለእግዚአብሔር !

Thursday, April 28, 2011

የማህበረ ቅዱሳን አባላት በአንድ ጉዳይ ለሁለት መከፈላቸው ተሰማ(abaselama)

የማህበረ ቅዱሳን አባላት በአንድ ጉዳይ ለሁለት መከፈላቸው ተሰማ

ማህበረ ቅዱሳን ተሃድሶዎችን ለማሳደድ 100000 ብር ያስፈልጋኛል ብሎ ገቢ ለማሰባሰብ እየተዘጋጀ ባለበት ባሁኑ ወቅት ጊዜያችንን እና ገንዘባችንን በማይጠቅም ነገር ላይ ማጥፋት የለብንም የሚሉ አባላት ከውስጥ ተቃውሟቸውን እያነሱ ነው። እነዚህ ተቃዋሚዎች ምክንያታቸውን ሲያቃርቡ በቅርቡ የያዙት ተሃድሶን የማሳደድ ፕሮግራም በሕዝቡ ዘንድ ተቀባይነት ማጣቱና ወጤት ካለማስገኝቱም በላይ በተቃራኒው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤ/ ክርስቲያንን ሕዝብ ለሁለት እየከፈለ ከፍተኛ አለመተማመንን ፈጥሯል ይላሉ።

ብዛት ያላቸው ምዕመናን ደግሞ ቄሶችና ሰባኪዎች ተሃድሶ ከሆኑ እኛስ ከነርሱ በምን እንበልጣለን? ይህ ጉዳይ የካህናቱ ስለሆነ ያናንተን አልባልታ መስማት አንፈልግም በማለት ከፍተኛ ተቃውሞአቸውን በማህብረ ቅዱሳን ላይ አሰምተዋል እያሰሙም ነው።
በዋናነት ግን ማህበረ ቅዱሳንን ለሁለት ለመከፈል ያበቃው የገረገራ ጊዮርጊስ ጉዳይ ነው። ባለፈው እንደ ዘገብነው የሰሜን ወሎ ስራ አስኪአጅን ጨምሮ አራቱ የማህበረ ቅዱሳን አባላት ኢየሱስ ክርስቶስን ሲያሳድዱ ሰንብተው ሲመለሱ የጌታ ቁጣ እንዳገኛቸውና አጥንታቸው ተለቅሞ እስኪቀበር ድረስ እንደተቀጡ ይታወቃል። በዚህ የመቂት ወረዳ የማሳደድ ፕሮግራማቸው ወንጌልን እንሰብካለን ብለው ሕዝብን በማታለል ወንጌልን ሲቃወሙ ሰንበተዋል። ሦስት ዲያቆናትን ሁለት ቄሶችን፤ አንድ የቅዳሴ መምህርና የመምሪያ ኃላፊን ከሥራቸው አፈናቅለዋል ሕዝብ በድንጋይ እንዲወግራቸው ቅሥቀሣ አድርገዋል በዚህም ምክንያት እነዚህ አገልጋዮች በገንዛ ሐገራቸው እንዳይወጡ እንዳይገቡ በመንገድ ላይ እንኳ እንዳይታዩ ተደርገዋል. ዘመድ እና ወገን እንዲአይገላቸው ማህበረ ቅዱሳን በመቀስቀሱ ከፍተኛ ስደት ደርሶባቸው ዛሬ በሥጋት ላይ ይገኛሉ።
ጌታ ግን የመውጊያውን ብረት ብትቃወመው ባንተ ይብስብሃል እንዳለው የመውጊያውን ብረት የተቃወሙት አራት የማህበረ ቅዱሳን ባላት በመውጊያው ተወግተው ወደ ማይመለሱበት ዓለም ሄደዋል። ይህ ነገር ግን የገረገራን ሕዝብና ማህብረ ቅዱሳንን ለሁለት ከፈለ። ግማሹ የገረገራ ሕዝብ የማህበረ ቅዱሳን አባላት ኃጢአተኛ ናቸው ቅዱሳንን ስላሳደዱ ወዲያው ፍርዳቸውን አገኙ እነዚህ ቄሶች እውነተኛ የኢየሱስ ክርስቶስ አገልጋዮች ነበሩ እናም ወደ ቦታቸው መመለስ አለባቸው በማለት በመከራከር ላይ ይገኛል።
ግማሹ የድጋይ ልብ የያዘው የገረገራ ሕዝብ ግን በነዚህ ሰዎች ምክንያት ነው ወንድሞቻችን አደጋ የደረሰባቸውና እነዚህን ቄሶች መበቀል አለብን ብሎ ቄሶችን ለመግደል በፈለግ ላይ ነው። ለንስሐ መዘጋጀት ይቅርታ መጠየቅ ሲገባ እንደገና ቄሶችን ከተሰደዱበት ፈልጎ ለመግደል መሞከር በጣም የሚያሳዝን ነው። ጌታ የሚገላችሁ ሁሉ እግዚአብሔርን እንደሚያገለግል የሚመስልበት ጊዜ ይመጣል ያለው ቃል እየተፈጸመ ነው። ነገሩን ላስተዋለው ግን ይህ ጉዳይ ለማህበረ ቅዱሳን የንስሐ ጥሪ መሆኑን ነው። ኢየሱስን በማሳደድ አንድም ሰው አልተጠቀመም።
የገረገራ ሕዝብ የመከፋፈሉን ያህል የማህበረ ቅዱሳን አባላትም ጥቂቶቹ የወንድሞቻቸው በአደጋ መሞት በጥሞና ሥራቸውን እንዲመረምሩ አድርጓቸዋል። ማንን እያገለገልን ይሆን? የሚሉ አባላት በዝተዋል እነዚህ እግዚአብሔር የድንጋዩን ልብ አውጥቶ የሥጋና የመንፈስ ልብ የሰጣቸው ናቸው በሃይማኖት ብትኖሩ ራሳችሁን መርምሩ እንደተባለው ራሳቸውን የሚመረምሩ እየበዙ ናቸው
አንዳዶች ይህ ቅጣት ከእግዚአብሔር የተላከልን ማስጠንቀቂያ ነው እና ነገሮችን እንደገና ማጤን አለብን፤ ሰው ኢየሱስ ክርስቶስን ካመነ በቂው ነው የሚሉ ሐሳቦች በማህበረ ቅዱሳን ዋና ቢሮ እና ንኡስ ማዕከላት ተጧጡፏል።
እነዳንኤል ክብረትና መሰሎቹ ደግሞ እንደ ፈሮን ዓይነት የድንጋይ ልብ እንደተሰጣቸው እንዲያውም ያሁኑ ፕሮግራማችን ካልተሳካ ድብደባ እና ግድያ እንጀምራለን በማለት እየፎከሩ ነው። በተለይም ዳንኤል ክብረት የታባለው የክርስቶስ ጠላት "አባ ሕርያቆስ ከሌሉበት መንግሥተ ሰማያት አባ ሕርያቆስ ያሉበት ሲኦል እንደሚሻለው" ሲናገር ተደምጧል።
አባ ሕርያቆስ የአባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ ጓደኛ ሲሆኑ የዋልባ መነኩሴ በነበሩበት ወቅት ቅዳሴ ማርያምን የደረሱ ሰው እንደነበሩ ድርሳነ ኡራኤል ይናገራል። ነገር ግን ድርሰቱ ከግብጽ የመጣ ለማስመሰል አባ ሕርያቆስ ዘብሕንሳ ተብለው ይጠራሉ የግብጽ ቤተ ክርስቲያን ግን ሰውየውን አታውቃቸውም  የኢትዮጵያው የአባ ሕርያቆስ ቅዳሴም ግብጽ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ አይገኝም። እንደ ድርሳነ ኡራኤል ዘገባ ከሆነ ግን ሰውየው ኢትዮጵያዊ ናቸው። ሰውየው የትም ይሁኑ የት ግን ዳንኤል ክብረት ሰውየውን ካላገኘኋቸው ወደ መንግሥተ ሰማያት አልገባም ብሎ እምቢ ያለበት ምክንያት ግልጽ አይደለም። ሰውየው ገና ቅዳሴ ማርያምን ደርሰዋል ብለን አድራሻቸውን ልናውቅ እንችላለንን? ሲኦል ይሁኑ ገነት እንዴት ማረጋገጥ ይቻላል? ብዙ የማያምኑ ሰዎች ጠንቋዮችም ታላላቅ ድርሰት እንዳላቸው የታወቀ ነው። ግሩም ድንቅ የሆኑ ምሥጢራዊ ቅኔዎችን የሚቀኙ ሰዎች ጠንቋይ ሆነው አግኝተናቸዋል። ስለዚህ ያንድ ሰው እውቀታዊ ችሎታ ሲኦል ወይም ገነት ለመግባቱ ማረጋገጫ አይሆንም ይህን ጉዳይ የሚያውቀው እግዚአብሔር ብቻ ነው።
ዳንኤል የሚሻለውን ራሱ ያውቃል ምርጫው የራሱ ነው እኛ ግን ማንም እዚያ ባይገኝ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ያለበትን መርጠናል። በእርግጥም የዳንኤሉ አባ ሕርያቆስ ጌታ ባለበት ከተገኙ እኛም እዚያ እናገኛቸዋለን ምን አልባት ከሌሉ ግን እርሳቸውን ተከትለን ሲኦል መግባት አንፈልግም። ለዳንኤል ይመቸው። ይህ ትምህርቱን በሲዲ አሳትሞ ለሕዝብ ማሰራጨቱ ጉዙው ወዴት እንደሆነ ከወዲሁ ማወቅ ይችላል።
ዳንኤል እና መሰሎቹ የሰሜን ወሎው አደጋ የጌታ ቅጣት መሆኑ አልተዋጠላቸውም ይልቁንም የጌታ ቅጣት ነው ብለው ያመኑትን እና ለንስሐ የተዘጋጁትን እናንተም ከሐተሃድሶዎች ጎራ ልትመደቡ ትችላላችሁ የሚለውን የተለመደ ማስፈራሪያ እያስተጋቡ ነው።
ለቤተክርስቲያናችን መሻሻል የምንጥር የቤተ ክርስቲያኒቱ ልጆች ግን የወንድሞቻችንን ክፉ ነገር አንመኝም እግዚአብሔር ይቅር እንዲላቸውም እንጸልያለን ክፉውን በክፉ አትቃወም ይላልና ቃሉ ማህበረ ቅዱሳንን በክፉ አናስበውም እርሱ ሊገለን ሊያስድደን በሕዝባችን ፊት ሊያዋርደን ስማችንን ቢያጠፋም ስለ ስሜ ክፉውን ያደርጉባችኋል፣ ስለስሜ የተጠላችሁ ትሆናላችሁ የሚለው የጌታ ቃል ትዝ ስለሚለን በደስታ ተሞልተናል ወንድሞቻችን በያዙት የተሣሳተ አቋም ግን እጅግ አዝነናል ያዝነውም ስለምንወዳቸው እንጂ ሥራው ተጓጎለ ብለን አይደልም ሥራውን ጌታ እኛ እንደማንሠራው ጠንቅቀን እናውቃለን። እኛ ስለስሙ መነቀፋችን ደስ አሰኝቶናል ሥራው የጌታ ነው ሁሉም በጊዜው ይከናወናል ተሐድሶ የጌታ ሐሳብ ከሆነ ያብባል ይስፋፋል የጌታ ካልሆነ ግን ይጠፋል እኛ ብንሰደድ ኢየሱስ ክርስቶስ ሌሎች የተቀቡ አገልጋዮችን ያስነሳል። እግዚአብሔርን ማሸነፍ አይቻልም፤ ለወንድሞቻችን ለማህበረ ቅዱሳን አባላት የምንመክረው ግን ከማትችሉት ጌታ ጋር ነውና የገጠማችሁት ተጠንቀቁ ነው፤ እኛም ቢያንስ በሀገራችን የመኖር መብት አለን በቤተ ክርስቲያናችንም ጥያቄ የማንሳት መብት አለን መልሱን ግን ከዚያው ከሲኖዶሱ እንጂ ከናንተ አንጠብቅም። እናም እኛን በመግደል ደም ማፍሰስ እንጂ ሌላ ምን ትርፍ ታገኛላችሁ? ፖለቲካ ከሆነ አላማችሁ ለምን ፓርቲ ሆናችሁ አትወዳደሩም? በኛ ደም ለመበልጸግ እኛን በማርከስ ልትቀደሱ አስባችሁ ነው? ለምን አታስተውሉም? ሰውን በማሳደድ የጸደቀ ማን ነው? የሃማኖት ችግር አላባችሁ ካላችሁ ሊቃውንት ጉባኤው መድረክ ያዘጋጅልንና ማን እንደተሣተ እንንወያይ ስንላችሁ እምቢ ከተሐድሶዎች ጋር አብረን አንቀመጥም በማለት ትሸሻላችሁ ፡ ለምን ትሸሻላችሁ? አላውቂነታችሁ እንዳይገለጥ አይደለምን? መወያየት አንፈልግም ካላችሁ ለምን ታሳድዱናላችህ? በእውነት በእግዚአብሔር መንፈስ የምትመሩ ከሆነ አልቧልታ በየመንደሩ ከመንዛት ቃሉን ሰብካችሁ ለምን አታሳምኑንም?
አሁን የያዛችሁት ፕሮግራም ግን ከምር አደገኛ ነው ሕዝቡን ግራ ያጋባና እርስ በርሱ እንዳይተማመን የሚያደርግ ለወንጌልም ልቡን እንዲዘጋ ንስሐ ገብቶ እንዳይፈወስ እያረጋችሁ ነው በዚህ ተንኮላችሁ ምክንያት በቤተ ክርስቲያን ላይ የሚመጣው የእግዚአብሔር ቁጣ ያስፈራል ቁጣውን ብትንቁ እንኳ ለትውልድ አይብጅምና አስቡበት የጓደኞቻችሁን ሐሳብ ለማዳመጥ ጆሮአችሁን ክፈቱ፤ እኛ ተከፋፍላችሁ እንድትጋደሉ አንፈልግም ግን ተለውጣችሁ ለውጥ እንድታመጡ እንፈልጋለን ይህ ለኛም ለሀገርም ለቤተ ክርስቲያንም ለናንተም ለጌታም ይጠቅማል አሜን
የለውጥ ያለህ?
ታዛቢው ነኝ

እኛም አውቀናል …! ዲ/ን ሙሉጌታ ወልደገብርኤል

እኛም አውቀናል …! ዲ/ን ሙሉጌታ ወልደገብርኤል

ዲ/ን ሙሉጌታ ወልደገብርኤል

 
ለተከበራችሁ በሀገር ውስጥና ከሀገር ውጭ ለምትገኙ ሴቶችም ወንዶችም ኢትዮጵያውያን!!
በዛሬው ዕለት እጅግ አጠር ባለ መልኩ የዓባይን ጉዳይ በተመለከተ ማናችንም ብንሆን ልንስተው የማይገባ እውነት ላወሳችሁ እወዳለሁ። ይኸውም ኢትዮጵያዊ ሆኖ የኢትዮጵያ ሕዝብ አሁን ካለበት የደከረተና የከረፋ የባርነት፣ የውርደት፣ የሰደት፣ የረሀብ፣ የጉስቁልና እንዲሁም ከማያባራ የቅሶና የዋይታ ኑሮ ወጥቶ የሰላምና የዕረፍት ሕይወት ይመራ ዘንድ የሚጠላ፤ የኢትዮጵያ ምድር ትንሣኤ የማይዋጥለትና እንደ ኮሶ መድኃኒት የሚከነክነው ፍጥረት አይኖርም! ሊኖርም አይችልም። ሀገራችን ኢትዮጵያ ከ80% በላይ ባለቤት የሆነውን ፈሳሽ ተገድቦ የኢትዮጵያ ሕዝብ ተጠቃሚ ቢሆንና ለውጥ በምድራችንና ብልጽግና በኢትዮጵያ ሕዝብ ቢመጡ የማይዋጥለት ሌላ ማንም ሳይሆን የኢህአዴግ መንግሥት ራሱ ብቻ ነው።
የዚህ ያለ ሕዝብ ይሁንታ በጠመንጃ በሥልጣን ላይ የሚገኘውን መንግሥት የሚደንቅና የሚያሳዝነው ደንባራ ገጽታ አንዱ የተመለከትን እንደሆነ እነሱ ብቻ አዋቂዎች፣ ብልጦች፣ የሚያስቡትንና የሚመክሩትን የላቀና የማይደረስበት ራሳቸውን ከሰው በላይ አድገው ሲወስዱና ሲቆጥሩ በአንጻሩ ደግሞ ሰፊውን ሕዝብ ምንም የማያውቅ የአብርሃም በግ አድርገው መፈረጃቸው ነው። ይሁንና ዛሬ ማለት ትናንት ሊሆን እንደማይችል ከሰው ልጅ በላይ ነፋሳት ምስክርነታቸው አሰምተዋል።
ዓባይ ተገድቦ ለኢትዮጵያ ምድርና ሕዝብ ረብ ይዋል ሲባል የሁላችን ሀገር ወዳድ ዜጎች የላቀ ደስታ ነው። በዚህ ግልጥ ባለ ሀሳብ ላይ አንዱ ከሻሽ ሌላው ተከሳሽ ወይንም ደግሞ አንዱ የጭዋ ሌላው ደግሞ የባርያዋ ልጅ ተብሎ ነገር አይኖርም። ጥያቄው ከሊቅ እስከ ደቂቅ የተቀጣጠለውን እሳት በውስጡ አምቆ ይዞ የማይበጀውና የማይፈልገውን ከትክሻው አሽንቀጥሮ ለመጣል ለለውጥ በለውጥ ትርክ ላይ ለመሮጥ በተጠንቀቅ በቆመበት ሰዓት (በቃ! ለማለት ነው) ዓባይ ዓባይ ማልትስ እኛም አውቀናል … አይስብልም ወይ ጉበዝ? አሁንስ እነዚህ ሰፈርተኞች በማን ደምና ነፍስ ዘመነ ሥልጣናቸውን ያራዝሙ?
እንግዲህ ምን እንላለን በድጥ ላይ የቆማችሁ ሞኞችና ቅሎች ሳላችሁ ተራ ተንኮልና ሴረኝነት እውቀትና ጥበብ ሆኖ ከተሰማችሁና ከመሰላችሁ ዓባይ በማለት የኢትዮጵያ ሕዝብ ልብ ለመስለብ፣ ከገባችሁበት ጉድጓድ ለመውጣት እንደ መሰላል ለመጠቀምና የላላችውን ፈትል ዳግም ለመለቀብ ከሆነ ዓባይ እንደ ባድመ ለተጨማሪ አስር ዓመታት በግርግር የሚያሰነብታችሁ ሳይሆን ስትበቅሉ ጀምሮ እስከ ዛሬው ዕለት የዘራችሁትን ዘር የሚያሳጭዳችሁ ማዕበል ለመሆኑ አትዘንጉ።
በመጨረሻ መንግሥታት ሕዝብን አንድ ሁለት ጊዜ ያታልሉ ይሆናል በሦስተኛው ግን ተራው የሕዝቡ ይሆንና አንድና ሁለት በሌለው ሁኔታ ጭራሽ ለዘልአለም እንደሚሽራቸውና እንደሚቀብራቸው ሳይታለም የተፈታና ፀሐይ ያሞቀው የአደባባይ ምሥጢር ከመሆኑ ባሻገር በተጨማሪ በአንድም በሌላም ምክንያት ያለ እውቀት ከጀርባው ሞት ባለበት አጀንዳ ለተሰለፍን ዜጎች የምለው ነገር ቢኖር እውነት የኢህአዴግ መንግሥት የኢትዮጵያ ሕዝብ ለመጥቀም ሳይሆን ከኢትዮጵያ ሕዝብ ፍርድ ለማምለጣና ጠፍተህ ለማጥፋት የጠነሰሰው ሴራ መሆኑ ተገንዝበን በምንም ዓይነት መልኩ ከጥቅሙ ይልቅ ኪሳራው በሚያመዝነው አጀንዳ ላይ ገብተን የታራክ ተወቃሾች ከመሆን ለመትረፍ ራሳችንን ማንኛውም ዓይነት ድጋፍ ከመስጠት በመቆጠብ ዜግነታዊ ግዴታችንን እንወጣ ዘንድ ጥሬን አቀርባለሁ።

ሀገር ነጻ ስትወጣ በግርግር ሳይሆን በሥራ የሀገራችን እና የሕዝባችን ታሪክ እንለውጣለን!!
ዲ/ን ሙሉጌታ ወልደገብርኤል

Wednesday, April 27, 2011

የምድሪቱ ጉዞና የማንቂያው ደወል ድምፅ(dejesemay)

የምድሪቱ  ጉዞና የማንቂያው ደወል ድምፅ
(ጌዲዮን)
 "ስለዚያች ቀንና ስለዚያች ሰዓት ግን ከአባት ብቻ በቀር የሰማይ መላዕክትም ቢሆኑ ልጅም ቢሆን የሚያውቅ የለም "(ማቴ 24፡ 36)
" በመሸ ጊዜ ሰማይ ቀልቷልና ብራ ይሆናል ትላላችሁ፡፡የሰማዩን ፊትማ መለየት ታውቃላችሁ የዘመኑንስ ምልክት መለየት አትችሉምን?" (ማቴ 16፡3)
"ምሳሌዋንም ከበለስ ተማሩ ጫፏ ሲለሰልስ ቅጠሏም ሲያቆጠቁጥ ያን ጊዜም በጋ እንደቀረበ ታውቃላችሁ፡፡" (ማቴ 24፣32)
የዘመንን ፊት ስለመለየት ወይም "ስለዚያች ቀንና ሰለዚያች ሰዓት" ሰለተባለው ድንገተኛ ክስተት ለማወቅ የተለየ ወርክ ሾፕ እና ሲምፖዚየም ማዘጋጀት በዘመናዊ ቴክኖሎጂ ቤተ ሙከራ ማካሄድ በብዙ ሚሊዮን ሰልፈኛ አደራጅቶ በአደባባይ አመፅ መቀስቀስ አልፎም የአርባ ቀን ጾም ፀሎት መያዝ ላይጠበቅብን ይችላል፡፡ የዘመኑን ፊት ማን እንዲህ በቀላሉ ይለያል? የሚገርመው ትውልድ እንዲህ በሰለጠነበት እና ዘመን እንዲህ በረቀቀበት የመሬታችን ጉዞ ውስጥ ለአንድ ጊዜ የሚሆን የሰው ልጅ ከተነገረላት በለስ ተምሮ የበጋን መቅረብ ከመገመትና ከመተንበይ ባለፈ ለበጋና ለክረምት መፈራረቅ ከመሬት ዑደትና ከተፈጥሮ ክስተት በቀር እግዚአብሔር ስለሚባለው የነገሮች ሁሉ መጀመሪያና መጨረሻ የክስተቶች ሁሉ ማጠንጠኛ ማሰብ ቆም ብሎም መጠየቅ አይፈልግም፡፡ ያመዋል ምን አልባትም ይህን የማድረግ የህይወት አቅጣጫው አሁን ካለበት ሁኔታ 360 ዲግሪ ዞሮ ህይወትን ሌላኛዋ መልክ እንዲያጠና ስለሚገደድ ይፈራል፡፡ የሚፈልገው በደመ ነፍስ መኖር ነው፡፡ በመብላት በመጠጣት ልዮ ፋሽን በማሳደድ ቪላ በመገንባት ቆንጆ ሴቶች (ወንዶች) በመምረጥ የተሻለ የስራ ቦታ በማመቻቸት ተሰሚነት በሚያስገኙ መድረኮች አስገራሚ ዲስኩሮችን በማሰማትና ምድሪቱን በአሸናፊነትና በለውጥ ማማ ላይ ማስቀመጥ ነው፡፡
እኛ እኮ ጉዶች ነን፡፡ እጅግ የበዛን የበዛብን ጉዶች ሁሌም የህይወትን አንድ መልክ ብቻ የምንመዝን፡፡ ለሰው ለትውልድ ለህዝብ ለም ዲሞክራሲን ስንሰጥ ዲሞክራሲን  ስንሰብክ በራሳችን ላይ የጨከንን አምባገነኖች ነን፡፡ ነፍሳችን በነፃነት እንዳታስብ ህሊናችን የሚያምንበትን እንዳናራምድ እውነትን በእውቀት የገደልን እና መልስ ለሚሹ የውስጥ ጩህትና ኡኡታችን የበዛን የበዛብን ቢሮክራቶች  እና እንዴት ለራሳችን ዴሞክራሲን እንስበክ ? ይልቁኑ "ይህ ልጃችን እንደሆነ እውርም ሆኖ እንደተወለደ እናውቃለን፡፡ዳሩ ግን አሁን እንዴት እንዳየ አናውቅም ወይንም ዓይኖቹን ማን እንደከፈተ እኛ አናውቅም ጠየቁት እርሱ ሙሉ ሰው ነው እርሱ ስለራሱ ይናገራል " ማለት ይቀለናል ቀላሉ የማምለጫ መንገድ ይሔ ነንውና ታዲያ ለነፍሳችን ምን ዲሞክራሲ ያስፈልጋታል? ምክንያቱም
"አይሁድን ስለፈሩ ይህን አሉ" ለምን ይህን አሉ? እነሱ ከዘመኑ ፊት ይልቅ ፍርሃታቸው የሰው ፊት ነበርና ይህን አሉ፡፡ ይህን በማለትም ማህበራዊ ኑሮን እድርና እቁብን ሰርግ መልስ ቅልቅልን ገናና ፋሲካን በፍቅር በህብር በፌሽታ ያሳልፋሉ፡፡ ይህ ባይሆን ደግሞ "እርሱ ክርስቶስ ነው ብሎ የሚመሰክር ቢኖር ከምኩራብ እንዲያወጡት አይሁድ ከዚህ በፊት ተስማምተው ነበርና" (ዮሐ 9፡18-23) ስለተባለ የክህደት አድማ በአዋጅ ተለፈፈ፡፡ ሰው ለነፃነትና ለዲሞክራሲ አደባባይ ይወጣል  ድምፁን ያሰማል እዚህ በተቃራኒው መንፈሳዊ ዲሞክራሲን መንፈሳዊ አርነትን ለመግደል ለክህደትና ለእውነት ሞትና ስቃይን ለመጋበዝ ትውልድ ባንድ ተስማምቶ ሰልፍ ይወጣል ፡፡ ታዲያ ይህ ወገን የሰማይን ፊት እንጂ የዘመኑን ፊት እንዴት ይለያል? የዘመኑን ፊት በጽድቅ  በንጽህና በታማኝነት በትጋት በእውቀት በጭምትነት ራስን በመግዛት ለህሊና በመታመን ለእውነት በመኖርና በመሞት ከሁሉ በላይ ደግሞ በእምነት በመኖር የሚገኝ ነው፡፡ የሚገለጥ ነው፡፡ አሁን ማን ይሙት(እንበልና እንደተራቾቻችን) የዚህን ዘመን ፈተናና ስቃይ  ልብ ብሎ ለሚመረምር "ያን ጊዜ በጋ እንደቀረበ ታውቃላችሁ" እንደተባለላት በለስ  ጌታችሁ በደጅ እንደቀረበ እወቁ፡፡ ማለትም ከግንዛቤ ማስወጣት ይኖርብን ይሆን ወይስ "ስምንተኛው ሺ ቀርቧል" እየተባለ የፌዝ ማጣፈጫ የሆነው የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ዳግም ምጻአት ለኛ ከቁም ነገር የሚጻፍ አልሆነብን ይሆን ? እኔ ግን የምድሪቷ ጉዞና የደውል ድምጽ በለሆሳስ እያስተጋባ እንደሆነ አስባለሁ፡፡ የሚያስደነግጠኝ ግን ነገሩ ሁሉ ልክ እንደ ኖህ እንደ ሎጥ ዘመን ታሪክ "የአስረሽ ምችው ዘመን ታሪክ" አንዳይደግም ነው፡፡               
"ሊበሉ ሊጠጡ ተቀመጡ ሊዘፈኑ ተነሱ" አይነት
ፍቅር ሲቀዘቅዝ፣ ወንድም ወንድሙን ሊያጠፋ ሲነሳ ስጋ ሁሉ ለራሱ ነፍስ ብቻ ሲጠበብና ሲጨነቅ፣ ወላጅ በአደባባይ ሲዋረድ፣ የቤተክርስቲያን ክብር በስጋዊያንና በአለማውያን ልክ የለሽ ምኞት ሲገሰስ፣ ጽድቅ፣ ቅድስና፣ ቅንነት፣ ታማኝነት፣ ራስን መግዛት፣ በጎነትና ንፁህ አምልኮ . . . . የሞኞች ስብከት ሆነው ሲተረኩ እንዴትስ የዘመኑ መልክ ለትውልዱ ጠፍቶታል፡፡ ለማለት እንገደድ ይሆን? ጭንቁ የሚጀምረውም እዚህ ላይ ነው፡፡ አልያም ደግሞ ግድ ከሆነብን እንደ ዓለም አቀፍ የመገናኛ ብዙሀን ወቅታዊ ክስተቶችን እየተከታተልን ለምዕመኖቻችን ማሳወቅ ግድ ሊለን ነው፡፡ ዕምነት ያልከፈተው አይን ጋዜጣና፣ ቴሌቭዥን ወይም የቴክኖሎጂው "በረከት" የዲሽ አገልግሎት በምድራችንና በዘመናችን መካከል ላይ የሚፈፀመውን ጉድ እቤታችን ድረስ ስበው ስለሚያመጡልን "ወይ ጉድ" እያልን እየተደመምን እጃችንን በአፋችን ላይ እያኖርን ቀኖቻችንን እንገፋለን፡፡ ንቁና ብልህ የዕምነት ሰው ግን ከመጽሐፍም ከዘመንም እየተማረ ለእግዚአብሔር እውነት ይገዛል፡፡ አሁንም ንቁና ብልህ ሰው ከዘመኑ ፊት እየተማረ ከዓለም ጋር ያለውን ቁርኝት አቋርጦ ከእግዚአብሔር ጋር ያለውን ጽኑ ህብረት ይበልጡኑ ያጠናክራል፡፡
ü ህዝብ በህዝብ ላይ ሲነሳ እያየን
ü የምድር መናወጥ የሬክታር መጠኑን እየለካን
ü ጎርፍና የነፋስ ጉልበትን እየመዘንን
ü የፍቅር መቀዝቀዝና የጥላቻ መጠንን መበርከቱን እየቃኘን
ü ጦርነትን ጦርንና የጦር ወሬን እያደመጥን
"ወይ ስምንተኛው ሺህ" እያልን እየተረትን እምናልፍ ከሆነ በዕርግጥም የእውነት መስመሩን ስተናልና ቆም ብለን እናስብ ለኛ የሚገርመን
ü የመካከለኛው ምስራቅ ነውጥና የህዝቦች አለመረጋጋት ነወይ?
ü የግብፅ ብጥብጥና የሆስኒ ሙባረክ ከስልጣን መልቀቅ ነወይ?
ü የሊቢያ ፈተናና የሙዐመድ ጋዳፊ ጭካኔ ነወይ?
ü የሱማሊያ መበታተንና የባህር ላይ ውንብድና ነወይ?
ü የሆሳማ ቢንላደን አመፅና የመስከረሙ 1 የአሜሪካ ህንፃ መጋየት ነው ወይ?
ü ወይንስ የሶቪየት ህብረት መበታተን የዩጎዝላቪያ መለያየት  የአይቮሪኮስታውያን አመጽ?
እኛ እኮ አውራቂስንም እናውቃለን ኖህና የሎጥ ታሪክንም እናውቃለን የእስራኤልና የፍልስጤምንም ሆነ የሮማውያንን ወረራ ከመፅሃፍ ተምረናል በምልክት የምንደነግጥና የምንቦርቅ ሳንሆን በተከፈቱ የዕምነት አይኖች የጌታችንን የኢየሱስ ክርስቶስን ዳግም ምፅዐት በእምነትና በተስፋ የምንጠባበቅ ነን፡፡ ስለዚህ የጌታ ምፅዐት የሚያስደነግጠን ሳይሆን በፍቅር የምንጠብቀው ነው የሚሆነው ለዚህ ደግሞ ዝግጁ እንድንሆን መፅሃፍ እንዲህ ይለናል ፡፡
 "ያን ግን እወቁ ባለቤት ከሌሊቱ በየትኛው ክፍል ሌባ እንዲመጣ ቢያውቅ ኖሮ በነቃ ቤቱም ሊቆፈር ባልተወም ነበር፡፡ ስለዚህ እናንተ ደግሞ ተዘጋጅታችሁ ኑሩ የሰው ልጅ በማይታሰብበት ሰዓት ይመጣልና ፡፡" (ማቴ 24 ፡43)
ይመጣልና በእግዚአብሔር ግንዛቤና እውቀት " ይመጣል " ነው አንዳችም ክፍተት አንዳችም ጥርጣሬ አንዳችም የምናልባታዊነት ድምፀት  የለውም፡፡ ጌታችን ኢየሱስ የምድርን ጫፍ ከዳር እስከዳር ሊረግጥ ያለአንዳች ጥርጥር በዘመኑ ፍፃሜ ወደእኛ ያመጣዋል፡፡የምድሪቱ ፍፃሜን የሚያበስረው የደውል ድምፅ ከትላንት ይልቅ ዛሬ ከዛሬም በላቀ ሁኔታ ነገና ከነገ በስቲያ በምድራችን በጉልህ መደመጡ የማይቀር እውነት ነው፡፡እና ጥንቃቄን ለእናንተ እናስታውሳለን፡፡ ትጋትን ለናንተ " እርስ በእርስ ተመካከሩ " በተባለው መንፈስ ውስጥ ሆነን እንመክራለን፡፡ የእግዚአብሔርን ቃል በጥንቃቄ በመመርመር ከቃሉ ውስጥ በሚገኝ የዘመኑን ፊት የመለየት ጥበብ ተክነን ከእግዚአብሔር ጋር ያልተቋረጠ ህብረትን  እንመሰርታለን፡፡ በምድር የምንኖረው የእርሱ እውነተኛ ወኪሎች ሆነን ነውና ውክልናችንን በትክክለኛው የተልዕኮ ፈፃሚነታችን  መስመር አስይዘን የምድር ጉዞአችንን ልናጠናቅቅ ተስፋ እናደርጋለን እናምናለንም ፡፡ የማንቂያው የደውል ድምፅ የሚነግረን ልዩ መልዕክት ቢኖር በትጋትና በዝግጁነት የጌታችንን የኢየሱስ ክርስቶስን መመለስ እንድንጠብቅ ነው፡፡ 

Monday, April 25, 2011

በጎውን ማን ያሳየናል የሚሉ ብዙ ናቸው== dejesemay

‹‹በጎውን ማን ያሳየናል የሚሉ
ብዙ ናቸው››
              (መዝ. 4፥6)፡፡
 
ስለ ዘመናችን ድንቅነት ብዙ ተነግሯል፡፡ የንግግሩ ምራቅ ሳይደርቅ ግን አሳዛኝነቱ ይተረካል፡፡ ዘመናችን ከተደነቀባቸው ነገሮች አንዱ የመረጃ ዘመን መሆኑ ነው፡፡ ሰዎች ስለ ራሳቸው ሳይሆን ስለ ሌሎች፣ ስለ ጎረቤታቸው ሳይሆን ስለ መካከለኛው ምሥራቅ ብዙ መረጃዎችን የሚሰሙበት ዘመን ነው፡፡ የመስማት አንዱ ዓላማ ለመመካከር፣ መራራው ወደ ጣፋጭ እንዲለወጥ ለመጸለይ ነው፡፡ የመረጃው ዘመን ግን ሰምቶ ማዳነቅ ብቻ ነው፡፡ ችግሮች ብዙ ናቸው፣ የመፍትሔ ድምፆች ግን አይሰሙም፡፡ ብዙ የመረጃ መረቦች የጭንቅ ወሬ ካጡ ይጨነቃሉ፡፡ የጦርነት፣ የተፈጥሮ አደጋ፣ የእርስ በርስ መተላለቅ ትልቅ ርእሳቸው ነው፡፡ በአገራችን በኢትዮጵያ በ1998 ዓ.ም በነበረው ግርግር አንድ የጋዜጣ አዘጋጅ ለጓደኛው ሲናገር፡- ‹‹ይህ ግርግር ሳይበርድ ለሦስት ወር ከቀጠለ የጀመርኩትን ቤት እጨርሳለሁ›› እንዳለ፣ ጭንቅ ባላለቀ እያሉ የሚሳሉ፣ እንደ ዕድር ጡሩንባ ነፊ ሞተ እንጂ ተነሣ የማይሉ፣ እንደ ጠመንጃ አፈ - ሙዝ ከአፋቸው ደህና የማይወጣ፣ ያልተባረኩ አንደበቶች በዝተዋል፡፡ ብዙ የቴሌቪዥን ጣቢያዎችን እንለዋውጣለን፡፡ ሁሉም የሚያመነዥጉት ያንን ክፉ ነው፡፡ አዋቂዎቹ የሚሰጡት ትንታኔ የሚመጣውን ቀውስ ጠቋሚ ነው፡፡ ስለዚህ የግለሰቦች ቀውስ እያለፈ ዓለም ራሷ እየቀወሰች መሆኗን እንረዳለን፡፡ ግለሰቦች ሲቃወሱ ምድር ችላቸው ብዙ ዘመን ኖረናል፡፡ ምድር ከቀወሰች ግን ማን ይችላታል@
ተበልቶ እንዳለቀ አጥንት ወይም የበቆሎ ቆረቆንዳ የቴሌቪዥን ጣቢያዎችን ብናገላብጣቸው ለጥጋብ የሚሆን አንድም ነገር የለባቸውም፡፡ ወደ ኢንተርኔት ጫካም ስንገባ ወሬ ከመንግሥታዊ ተቋማት ወደ ግለሰብ ተቋማት ዝቅ ብሎ፣ ‹‹ሐሜት ድሮ ቀረ በቃል ብቻ›› የሚሉ የጽሑፍ ሐሜተኞችን እናገኛለን፡፡ የሰውን ስም ቡና ላይ ከማንሣት ድረ - ገጽ ላይ ወደ ማንሣት ተሸጋግረናል፡፡ ብሔራዊ የነበረውን ኃጢአታችንን ዓለም አቀፋዊ አድርገነዋል፡፡ ጫካ ገብቶ በጥይት የመዋጋት ዘመን በኢንተርኔት ውስጥ መሽጎ በስም ማጥፋት አረር እንደ ተለወጠ እያየን ነው፡፡
ጉድ ያለበት የሰው ልጅ የሌላውን ጉድ ለማውራት በጀት የባጀተበት ዘመን መሆኑን እናያለን፡፡ ዘመኑና ሥልጣኔው መስተዋት ሳይሆን መነጽር መሆናቸውን እናስተውላለን፡፡ መስተዋት ራስን ያሳያል፣ መነጽር ሌላውን ያሳያል፡፡ በክፉ ወሬዎች በተከበበው ዘመን የብዙዎች ነፍስ ተጨንቃለች፡፡ በሩቅ ስላለው ሰው እያወቁ ራስን አለማወቅ፣ የሌሎችን ክፋት እየተረኩ የእግዚአብሔርን በጎነት መዘንጋት ለሰዎች ዕረፍትን አልሰጣቸውም፡፡ በእውነት፡- ‹‹በጎውን ማን ያሳየናል@ የሚሉ ብዙዎች ናቸው›› (መዝ 4፥6)፡፡
ስለ ሰዎች ክፋት አንድ ሰዓት ማውራት መቻል ስለ እግዚአብሔር በጎነት ዐሥር ደቂቃ መነጋገር አለ መቻል በጣም ያሳዝናል፡፡ የሰው ልጅ የትኛውም ማንነቱ አያሳርፍም፡፡ እንኳን ከድካሙ ከብርታቱም ጉድለት አለበት፡፡ ነቢዩ፡- ‹‹ጽድቃችንም ሁሉ እንደ መርገም ጨርቅ ነው›› ያለው ለዚህ ነው (ኢሳ. 64.6)፡፡ የሚያሳርፈው የመስቀሉ ሥራ ብቻ ነው፡፡ ስለ ክፉ አንድ መጽሐፍ መጻፍ ስለ መጽናናት ግን አንድ መስመር አለመጻፍ በእውነት ምስኪንነት፣ የሞትም አገልጋይ መሆን ነው፡፡ የሰዎችን መልካምነት በካባ እየሸፈኑ ትንሽ ስህተታቸውን በአጉሊ መነጽር ማየት በእውነት አለመታደል ነው፡፡ ዘመናዊነትን ስናየው የክፋት ማፍጠኛ እንጂ የመልካም ነገር ማፍጠኛ አለመሆኑ ያሳዝናል፡፡
ብዙ የዓለማችን ሕዝቦች ከመረጃ መረቦች ራሳቸውን እያገለሉ ነው፡፡ የራሳቸውን ችግር ሳይፈቱ ስለ ሰው ኃጢአት መነጋገር እየሰለቹ ነው፡፡ ልክ ያልሆኑ ነገሮችን ከሚያሰሙ ስብከቶች ልክ የሆነውን ወደሚያሳዩ አገልጋዮች ዘወር እያሉ ነው፡፡ የሰው አእምሮ በብዙ ጭንቀቶች በተወጠረበት በዚህ ዘመን፣ ብዙ አደንዛዥ ዕፆች በሚወሰዱበት በዛሬው ጊዜ የሚበጀው ሰላማዊ መልእክት ብቻ ነው፡፡ በራሳቸው መወደድ ያልቻሉ ሌላውን እያስጠሉ ለመወደድ የሚሹ ሰዎችን ብዙዎች እየራቁ ‹‹በጎውን ማን ያሳየናል@›› እያሉ ነው፡፡ እኔ ቆንጆ ነኝ ለማለት እገሌ አስቀያሚ ነው ማለት አስፈላጊ እንዳልሆነ ሕዝባችን እያስተዋለ ነው፡፡ እናንተን የምንቀበላችሁ በራሳችሁ ልክ ስትሆኑ እንጂ እነ እገሌ ስለ ተሳሳቱ አይደለም እያለ ነው፡፡ በእውነት ጠብን ሳይሆን ፍቅርን የሚዘሩ፣ ክርክርን ሳይሆን መግባባትን የሚያመጡ አገልጋዮች እየተፈለጉ ነው፡፡ 
ራሳችንን ስናየው ሬዲዮን በደንብ ሳንጠቀም ቴሌቪዥን የጀመርን፣ ታይፕን በደንብ ሳንጠቀም ኮምፒዩተርን የተከልን፣ አጠገባችን ካለው ሰው ጋር ሳንግባባ ዓለም አቀፍ መረጃ ውስጥ አሳብ የምንሰጥ፣ ከወንድማችን እየተጣላን ከዓለም አቀፍ ወጣቶች ጋር ማኅበርተኛ መሆን የምንፈልግ፣ በጾም ከበሮ መምታትን እየጠላን ወገናችንን በስድብ የምንደልቅ፣ ያጎረስነው ሰው እያነቀ በላይ በላዩ የምናጎርስ፣ ከሥልጣኔው ክፉውን የምንጠቀም ነን፡፡
በብዙ ውጣ ውረድ ያለፈው ሕዝባችን ዕረፍትን ፍለጋ ወደ ቤተ ክርስቲያን ሲመጣ በሁከት ድምፅ እያሸበርነው፣ ማንንም አትመን እያልን አውሬን እየሳልንለት፣ የሥጋ ቅንዓታችንን ሃይማኖታዊ ካባ አልብሰን እያስጨነቅነው ነው፡፡ ወጣትነቱን በትክክለኛ ጎዳና ለመምራት የመጣውን ወጣት ሃይማኖታዊ ጠብ እንዲጣላ፣ በዝማሬ በስብከት ካጽናኑት አገልጋዮች ጋር እንዲታኮስ እያደረግነው ነው፡፡ ከዓለም ሁከትን ሸሽቶ የመጣው ትውልድ፣ በቤተ ክርስቲያን የሁከትን ድምፅ ሲሰማ ‹‹በጎውን ማን ያሳየናል@›› እያለ እየተጨነቀ ነው፡፡ ያሉት አገልጋዮች ተቀንሰው አይደለም፣ በእጥፍ ተጨምረው እንኳ ሕዝቡን መድረስ አይቻልም፡፡ ከዚሁም ላይ ስም እየሰጠን እየቀነስን ቤተ ክርስቲያንን የወላድ መሐን ማድረጋችን፣ የመናፍቃኑን አዳራሽ አለመሙላት ከውስጥ መግፋታችን አሳዛኝ ነው፡፡ ብዙ የሳጥናኤል የውስጥ ካድሬዎች ከውስጥ ሆነው ሲገፉ ከደጅ ያሉት ደግሞ ይቀበላሉ፡፡ በዋጋ የተሰበሰበውን ሕዝብ ያለ ዋጋ መበተን፣ ፍቅር አጥቶ ከዓለም የመጣውን ሕዝብ ጠብና ክርክር ማስጠናት ተገቢ አይደለም፡፡ አንድ ሕገ መንግሥት (መጽሐፍ ቅዱስ) ይዘን መለያየት ለአረማውያን ሰይፍ ራሳችንን ማዘጋጀት ነው፡፡
ሕዝባችን የፍቅር ሰባኪዎች ሲፋቀሩ፣ የይቅርታ አዋጅ ነጋሪዎች ይቅር ሲባባሉ ማየት ይፈልጋል፡፡ የቃል ስብከታችንን ከተማው ጠግቦት በሕይወታችን ስንኖረው ማየት እየፈለገ ነው፡፡ በየአድባራቱ እየታየ ያለው የጠብ አዝመራ፣ ጭር ሲል የማይወዱት የጠብ ጫሪዎች፣ በሰው ሬሳ ለመኖር የሚያቅዱ የክርስቶስ ጠላቶች፣ ስሜታቸውን መግዛት ያቃታቸው የገምቦኞች ክተት ነው፡፡ ሕዝባችን የእግዚአብሔርን ቃል ዳኛ አድርጎ ማነው የሳተው? ማለት አለበት፡፡ ጋዜጣ ላይ የወጣ ሁሉ የመጨረሻው እውነት ሆኖ ሊታየው፣ በኢንተርኔት የተለቀቀ ሐሜት የሲኖዶስ ውሳኔ አድርጎ ሊቀበለው አይገባም፡፡ ሁሉን የሚበክሉ ሚዛን የለሾች፣ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያንን ከመልካም አገልጋዮች ብቻ ሳይሆን ከተሰቀለው ጌታ ሊለዩአት የተነሡ፣ ወንጌልን ከኦሪት፣ ክርስቶስን ከሙሴ፣ መጽሐፍን ከተረት መለየት ያልቻሉ፣ እውነት በሚመሰል ሐሰት፣ ቅንዓተ ቤተ ክርስቲያን በሚመስል ራስን መስበክ ሕዝቡን እያደናገሩት ይገኛሉ፡፡ ሕዝቡም የሚይዘውን የሚጨብጠውን አጥቶ ‹‹በጎውን ማን ያሳየናል@›› ይላል፡፡
ወገናችን ዕድሜውን በሙሉ ብዙ ጭንቆችን ያየ፣ ብዙ ጦርነቶችን ያሳለፈ፣ የኑሮ ጠባሳ መልኩን ያጠፋው፣ በብዙ ቀBስለትም የሚያቃስት ነው፡፡ በዚህች አገር ላይ የኖረ፣ ያለፉትን ዘመናት ሰቆቃ ያየ ወገን፣ ሕዝቡን እንደ ገና አያስጨንቅም፡፡ የሚያጽናናውን ወንጌል በመስበክ ያረጋጋ ነበር፡፡ ጭጋግና ደመናው ነገን አላሳይ ላለው ወገን፣ ዝናብ የሌላቸው ደመናዎች ላደከሙት ሕዝብ የወንጌልን ማዕድ የምናቀርብበት ዘመን አሁን ነው፡፡ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያንን መወከል የማይችሉ አጽራረ ወንጌሎች የአዋቂዎችን ልብ እየሰበሩት፣ ትውልዱ ያዳነውን ጌታ እንዳያይ የክርስቶስን ደም እያክፋፉበት መሆኑ ያሳዝናል፡፡ መሳሳት የማይደክማቸው፣ ከትላንት ጥፋት የማይማሩ በመሆናቸው ሊለቀስላቸው ይገባል፡፡ ሊሰበክ ሊታወቅ የሚገባው ማን ነው@ የቤተ ክርስቲያን መሠረትና ጉልላትስ ማን ነው? ኢየሱስ ክርስቶስ አይደለምን? ‹‹ሞኝ ባያፍር ዘመዱ ያፍራል›› እንዲሉ በእነዚህ ሰዎች እስከ መቼ እናፍራለን? በአይሁድ ምኩራብ ክርስቶስ በተስፋ ይሰበካል፣ አይታፈርበትም፡፡ በእስላም መስጊድ ዒሳ ተብሎ ይነሣል፡፡ በእነዚህ ሰዎች ዘንድ ግን ኢየሱስ ክርስቶስን የጠራ በውግረት ይሙት ተብሎ ይፈረድበታል፡፡ ጠላትነታቸው ከፍጡር ሳይሆን ከተሰቀለው ጌታ ጋር ነውና ንስሐ እንዲገቡ እንጋብዛለን፡፡ ነፍሳቸውም በሐዋርያት ውግዘት ውስጥ ነች፡- ‹‹ጌታን ኢየሱስ ክርስቶስን የማይወድ ቢኖር የተረገመ ይሁን›› (1ቆሮ. 16.22) በተባለው ቃል የታሠሩ ናቸው፡፡ 
ሕዝቡ በዕንባ የሚዘምረውን ዝማሬ ያንተ አይደለም ይሉታል፣ የራሱ ያልሆነ ነገር እንዴት ያስለቅሰዋል? ልቡን ያሳረፉለትን ሰባኪዎች መናፍቃን ናቸው ይሉታል፣ የተፈወሰበትን መጻሕፍት የባዕድ ናቸው ይሉታል፡፡ በዚህ ሁሉ ውስጥ ‹በጎውን ማን ያሳየናል? የሚሉ ብዙ ናቸው›› (መዝ 4፥6)፡፡
ሕዝባችንም አደባባዩን የያዙ እውነተኞች ናቸው ብሎ ማሰብ የለበትም፡፡ ቅንዓት በዲግሪም አይለቅምና አዋቂዎች ነን በሚሉ ፈሪሳውያን ግራ ሊጋባ አይገባውም፡፡ እውነት ምንድነው? ብሎ ሊጠይቅ፣ ክርስቶስን የማይወድ የተረገመ መሆኑን ሊገነዘብ ይገባዋል፡፡ ትላንት ያስተማሩት አገልጋዮች ዛሬ ጦርነት ሲታወጅባቸው የአንዱን ቀን ማጽናናታቸውን እንኳ አስቦ ለምን@ ሊል ይገባዋል፡፡ ባለቤቱ፡- ‹‹እኔ ኦርቶዶክሳዊ ነኝ›› እያለ አይደለህም ማን ይለዋል? እነዚህስ ስም አጥፊዎች ይህንን እንዲያደርጉ ፈቃድ የሰጣቸውና የወከላቸው አካል ማን ነው@ ማለት አለበት፡፡ መጽሐፍ ቅዱስን በመግለጥ ሁሉንም አገልጋዮች በቃሉ መመዘን ይገባል፡፡ አሊያ ያለፉት ዘመናት ስህተት ሳያንስ ሌላ ደም በእጃችን እንዳይገኝ መጠንቀቅ ይገባል፡፡