Wednesday, June 8, 2011

በማኅበረ ቅዱሳን ላይ ከየአቅጣጫው ተቃውሞዎች እየተሰነዘሩ ነው== dejesemay.org

  • የቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ ተማሪዎች ታሪካዊ የተባለ የአቋም መግለጫ በማኅበረ ቅዱሳን ላይ አወጡ፤ ለቅዱስ ፓትርያርኩም አቀረቡ
  • ማኅበረ ቅዱሳን ከነጥሎ መምታት ወደ ጅምላ የስም ማጥፋት ስልት መሸጋገሩ ያስከተላቸው መዘዞች
  • በሐዋሳው ጉዳይ ላይ ቋሚ ሲኖዶስ ማኅበረ ቅዱሳንን አንገት ያስደፋ ውሳኔዎችን አሳለፈ 
ማኅበረ ቅዱሳን በለኮሰው እሳት መለብለብ መጀመሩን ከየአቅጣጫው እየተነሡ ያሉ ፀረ ማኅበረ ቅዱሳን እንቅስቃሴዎች እያረጋገጡ መሆኑን ምንጮቻችን ገለጹ፡፡ ማኅበሩ የስም ማጥፋት ዘመቻ ከከፈተባቸው መንፈሳውያን ኮሌጆቻችን መካከል አንዱ የሆነው የቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ ተማሪዎች በ5/8/2003 ዓ.ም. በማኅበረ ቅዱሳን ላይ የተቃውሞ ሰልፍ በማድረግ ወደመንበረ ፓትያርክ ጽ/ቤት ቀርበው የአቋም መግለጫቸውን ለብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ አቅርበዋል፡፡ የወንድሞች ከሳሽ የሆነውና ጥቂት ዘመን እንደቀረው ዐውቆ በታላቅ ቁጣ እንደ ወጣው እንደ ግብር አባቱ እንደ ዲያብሎስ፣ ማኅበረ ቅዱሳንም ዘመኑ እንደ ተፈጸመና ጥቂት እንደቀረው ተረድቶ በቤተ ክርስቲያን ልጆች ላይ የስም ማጥፋት ዘመቻውን አጠናክሮ በቀጠለበት በዚህ የዐቢይ ጾም ወቅት፣ የመንፈሳዊ ተቋማትን (የኮሌጆችን) ተማሪዎች ነጥሎ ከመምታት ስልቱ ወደጅምላ የስም ማጥፋት ዘመቻ መሸጋገሩ የኮሌጁን ተማሪዎች በእጅጉ እንዳስቆጣና ለተቃውሞ ሰልፍ እንዳንቀሳቀሳቸው ምንጮቻችን ጠቅሰው፣ በማኅበሩ ላይ ከኮሌጁ ተማሪዎች በኩል እንዲህ ያለና የአንድ እጅ ጣት የማይሞሉ ጥቂት የማኅበረ ቅዱሳን ደጋፊ ተማሪዎች ሲቀሩ፣ አብዛኛው ተማሪ ቀፎው እንደ ተነካ ንብ አንድ ሆኖ ለተቃውሞ መውጣቱ በኮሌጁ ታሪክ የመጀመሪያ መሆኑ ይነገራል፡፡
“የቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ ተማሪዎች ወቅታዊ በሆኑ የቤተ ክርስቲያቱ ችግሮች ዙሪያ የተሰጠ የዐቋም መግለጫ” በሚል ርእስ የወጣው የዐቋም መግለጫ 6 ነጥቦች ያሉት ሲሆን፣ በቅድሚያ ማኅበረ ቅዱሳን እየሠራ ያለውን መሠሪ ተግባር በዝርዝር አስቀምጧል፡፡ በዚሁ መሠረት ማኅበረ ቅዱሳን፡-
  • ቤተ ክርስቲያኒቱ አምናባቸው የከፈተቻቸውንና የምትቆጣጠራቸውን፣ ለቤተ ክርስቲያኒቱም ከፍተኛ አገልግሎት እያበረከቱ ያሉትን ኮሌጆች የሃይማኖት ችግር አለባቸው የሚል የስም ማጥፋት ዘመቻ መክፈቱ፤
  • የቤተ ክርስቲያኒቱን የአስተዳደር መዋቅር በመናቅና እንደሌለ በመቁጠር ከቤተ ክርስቲያን ዕውቅና ውጪ በየሆቴሉ በየአዳራሹ ስብሰባ በመጥራት በፈጠራ ወሬና አሉባልታ፣ የቤተ ክርስቲያን አባቶችንንና ምእመናንን ግራ የማጋባትና ረብሻና ብጥብጥ ሰፍኖ ቤተ ክርስቲያቱ ብሎም አገሪቱ በብጥብጥ የምትተራመስበትን መንገድ መቀየሱ፣
  • በቅዱስ ፓትርያርኩ ዘመነ ፕትርክና ቤተ ክርስቲያናችን በዓለም አብያተ ክርስቲያናት ያገኘችውን ስፍራ በማጣጣልና ለዚህ ከፍተኛ ጥረት ያደረጉትን የቅዱስ ፓትርያርኩን ስም በየሚዲያው ሲያጠፋና ሲያስጠፋ የኖረ መሆኑና አሁን ግን የፕሬስ ሕጉ ሕገወጦችን ተጠያቂ የሚያደርግበት ሁኔታ ስለተፈጠረ፣ ሌላውን ካልወነጀለ፣ ካልተሳደበና ስም ካላጠፋ የሠራ የማይመስለው ማኅበረ ቅዱሳን “ደጀ ሰላም” የተባለ የወሬ ድረ ገጽ ከፍቶ በዓለም አቀፍ ደረጃ የስድብ አፉን ማላቀቅ ከጀመረ ውሎ ማደሩ ተመልክቷል፡፡ የሚከተለው ስልትም “መንጋውን ለመበተን እረኛውን መምታት” የሚል ነው ይላል መግለጫው፡፡ ስልቱ ፓትርያርኩን በማስወገድ ቤተ ክርስቲያቱን መቆጣጠር የሚል አንድምታ ያለው ሲሆን፣ እርሳቸውን አስወግዶ እርሱ የቀረጸውን ፖለቲካዊ የሃይማኖት ሥርዐት ማስፈን የመጨረሻ ግቡ መሆኑም የአደባባይ ምስጢር ነው፡፡
6 ነጥቦች ያሉት የቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ ተማሪዎች ያወጡት የአቋም መግለጫ የሚከተለው ነው፡፡
1- “የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ለዘመናት ዶግማዋን፣ ቀኖናዋንና ትውፊቷን ጠብቃ የኖረችው ባላት ጠንካራ አስተዳደራዊ መዋቅርና በመንፈስ ቅዱስ የሚመራ ቅዱስ ሲኖዶስ ያላት ያለ ምንም እንከን የኖረች ስለሆነች፣ አሁንም ይህ ሥርዐቷንና የቅዱስ ሲኖዶስ መመሪያ ተጠብቆ በተገቢው የቤተ ክርስቲያን አስተዳደራዊ ሰንሰለት የቅዱስ ሲኖዶስ ክብርና ሥልጣን እንዲጠበቅ፣
2- “ማኅበረ ቅዱሳን የሚባለው ማኅበር አሁን የቤተ ክርስቲያናችንን የአስተዳደራዊ መዋቅር እና የቅዱስ ሲኖዶስ አመራርን ወደ ጎን በመተውና በመናቅ የቤተ ክርስቲያኒቱን አባቶች ከምእመናን፣ ከመንፈሳዊ ኮሌጆች የሚወጡ ደቀ መዛሙርትን ከአባቶችና ከምእመናን ጋር በማጋጨት የኮሌጆቹን ስም በማጥፋት እያደረጉት ካለው ሕገወጥ ተግባር ቅዱስ አባታችን እና ጉዳዩ የሚመለከታቸው የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት በዚህ ማኅበር እንቅስቃሴ ላይ አስተዳደራዊ እርምጃ እንዲወስዱ እንጠይቃለን፡፡
3- “ይህን የስም ማጥፋት ዘመቻ በማስፋፋት ላይ ያለውና የፈጠራ ወሬውን የፈጠረው አቶ ያረጋል አበጋዝ የሚባል በማኅበረ ቅዱሳን የሐመር መጽሔት ዝግጅት ክፍል ምክትል ኀላፊ እና አባል ግለሰቡም ፍጹም የሆነ ሃይማኖታዊና ቤተ ክርስቲያናዊ ዐላማን የማያራምድ ሲሆን፣ በተቃራኒው ሽብርና ሁከትን በቤተ ክርስቲያኒቱ ብሎም በአገር ለመፍጠር በጥናታዊ ጽሑፍ መልክ በመላው ሀገሪቱ በመዘዋወር የቤተ ክርስቲያቱን መንፈሳዊ ኮሌጆችን የተሐድሶ እና የመናፍቃን መፍለቂያ ወይም መፈልፈያ ናቸው በማለት ችግር እየፈጠረ ያለ በመሆኑ፣ ይህ ሁኔታ የቤተ ክርስቲያኒቱንም ሆነ የሀገሪቱን ሰላም የሚያናጋ  በመሆኑ ግለሰቡ በቤተ ክርስቲያኗ የበላይ አመራር እና ኀላፊዎች ተጣርቶ ከዚህ ተግባር እንዲቆጠብና ከዚህ ቀደም ላደረጋቸው ድርጊቶች ሕጋዊ እርምጃ እንዲወሰድበት እንጠይቃለን፡፡
4- “የዚህ የስም ማጥፋት ዘመቻ ተባባሪ የሆኑ በቤተክርስቲያን መዋቅር ውስጥ የመሸጉ ለዚህ መሠረተ ቢስ ውንጀላ እና ሽብር የተሳሳተ መረጃ አቀባይ እና የተሰጣቸውን ኀላፊነት ወደ ጎን በመተው ቤተ ክርስቲያንን ማገልገል ሲገባቸው፣ ለዚህ እኩይ ተግባር ተባባሪ በመሆን ለማኅበሩ ፈቃድ የሰጠውን የቅዱስ ሲኖዶስን ስም በማጥፋት ራሳቸውን የዚህ ማኅበር አባል ያደረጉ በኮሌጆቻችን እና በጠቅላይ ቤተ ክህነት በየመምሪያው ያሉ የቤተ ክርስቲያኗ አገልጋዮች ከዚህ ሥራ እንዲቆጠቡና ሁኔታው ተጣርቶ አስፈላጊው አስተዳደራዊ እርምጃ እንዲወሰድባቸው በጥብቅ እንጠይቃለን፡፡
5- “ባለቤትነቱ ለጊዜው ያልጠረጋገጠ ነገር ግን በጽሕፈቱ ሐሳብ ደረጃ ማንነቱ የሚታወቅ ማኅበር በቅዱስነትዎ እና በብፁዓን አባቶች ላይ እንዲሁም በመምሪያ ኀላፊዎች በመንፈሳዊ ኮሌጅ ደቀ መዛሙርት ላይ የስም ማጥፋት ዘመቻ በደጀ ሰላም ብሎግ (በደጀሰላም ዌብ ሳይት) እየተደረገ ያለውን፣ ቤተ ክርስቲያናችንን የማይወክልና በቅዱስ ሲኖዶስ የማይታወቅ ድርጊት በመሆኑ፣ ለምእመናን እና ለቤተ ክርስቲያን አገልጋዮች እንዲሁም ለመንግሥት በማሳወቅ ጉዳዩን የሚያከናውኑ ግለሰቦችም ሆኑ ማኅበሩ ላይ እርምጃ እንዲወሰድ ስንል አቋማችንን እንገልጻለን፡፡
6- “በመጨረሻም ለዚህ ስም የማጥፋት ዘመቻ እንደ ምሽግ የሚጠቀሙበት የቤተ ክርስቲያኒቱ ዐውደ ምሕረት ነው፡፡ ነገር ግን ቅዱስ አባታችን ደጋግመው እንደሚያዙትና ቤተ ክርስቲያኗም እንደምታምንበት የዐውደ ምሕረት ጉባኤ በተማረው ክፍል ወይም ቤተ ክርስቲያኒቱ መምህራን ብላ በመንፈሳዊ ኮሌጆች በአብነት ትምህርት ቤቶች በምታስመርቃቸው መምህራን እንዲሆን ከዚህ በፊት የተጻፈ ቢሆንም፣ ተፈጻሚ እንዲሆን በአጽንኦት ከከፍተኛ መንፈሳዊ ኮሌጆች እንዲሁም ከሚታወቁ የአብነት ትምህርት ቤቶች መምህራን ውጪ በቤተ ክርስቲያን ዐውደ ምሕረት ማስተማር የማይቻል መሆኑ ተገልጾ ለእየአህጉረ ስብከትና ለወረዳ ቤተ ክህነቶች እንዲሁም ለእያንዳንዱ አጥቢያ ቤተ ክርስቲያን ሰርኩላር በድጋሚ እንዲተላለፍልን እና ለመምህራኑም ሕጋዊ የሆነ የሚታደስ መታወቂያ እንዲሰጣቸው በጥብቅ እንጠይቃለን፡፡”
ከዚህ የአቋም መግለጫ በመነሳት እናንተም ሆናችሁ ሌሎቹ ሁላችሁም ልጆቼ ናችሁ በማለት ንግግራቸውን የጀመሩት ቅዱስ ፓትርያርኩ መቼም ሳትበደሉ ገፍታችሁ እንዲህ በቁጭት አትመጡም‹‹ውሸት ሲደጋገም እውነት ስለሚመስል›› ያለውን ችግር ለሚመለከተው አካል ለማሳወቅ መነሳታችሁ ‹‹ለእኔም ሆነ ለብፁዓን አባቶቼ ትልቅ የቤት ሥራ ነው›› ብለዋል፡፡ ‹‹ያገለገልነው ሕዝብ ድንጋይ እንዲወረውርብን በገዛ ቤታችን የባይተዋርነት ስሜት እንዲያድርብን እየተገደድን ነው›› ላሉት የደቀ መዛሙርቱ ተወካይ ቅዱስነታቸው አክለው ሲመልሱ ‹‹የሠራ ሁሉ ይነቀፋል ሥራ ስለ ሰራችሁ አገልግሎታችሁ ትርጉም ስላለው ነው የተነቀፋችሁት፤ ሕይወት ስለሌላቸው በድኖች ማን ምን ይላል? አይዟችሁ ስለ ሰሙ ነቀፋን መሸከም የደጋጎቹ አባቶቻችሁ መንገድ ነው በርቱ!  እኛ ይኼ ነው ብለን ዛሬ ምንም ባንላችሁም አሁን እናንተ ባነሳችኋቸው ጉዳዮች ዙሪያ እየሰራን ስለ ሆነ በቅርቡ ተግባራዊ ምላሽ ታገኛላችሁ፡፡ ቤተ ክርስቲያንን እንዲያገለግሉ አደራ ተጥሎባቸው መንፈሳዊ ተቋሙን ለጥፋት እያዘጋጁት ያሉት የኮሌጁም አስተዳዳሪዎች ለእውነትና ለቅድስት ቤተ ክርስቲያን እንደሰሩ መደረጉ የማይቀር ነው በማለት የዕርምት እርምጃ እንደሚወሰድ ተገልጾላቸዋል የሚል ምላሽ መሰጠቱን ምንጮቻችን አክለው ገልጸዋል፡፡
አስገራሚው ነገር የፈጠራው “ጥናታዊ ጽሑፍ” ደራሲ አቶ ያረጋል በአንድ በኩል ኮሌጁን የመናፍቃን መፈልፈያ እያለ ሲሳደብ፣ እርሱ ለስም ማጥፋት ዘመቻው በተገኘባቸው አዳራሾች የመድረክ መሪዎች የነበሩት የማኅበሩ አባላት ሲያስተዋውቁት ስሙን “የቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ ደቀ መዝሙር” ከሚል ቅጽል ጋር መጥራታቸው፣ የሌላውን በግ ለመውስድ ከጅሎ ባለቤቱን የተሸከምኸው ውሻ ነው እያለ ለማስጣል የሞከረውን ቀሳጢ ታሪክ ያስታውሳል ሲሉ ምንጮቻችን ትዝብታቸውን ያስቀምጣሉ፡፡ 
በመግቢያው ላይ እንደተገለጸው ማኅበረ ቅዱሳን፣ ወደ ጅምላ የስም ማጥፋት ዘመቻ ከመሸጋገሩ በፊት የቀደመው ስልቱ ነጥሎ መምታት የነበረ መሆኑን ብዙዎች ይናገራሉ፡፡ አንበሳ ከዱር እንስሳት መንጋ መካከል ለመንጠቅ ሲፈልግ፣ በአንዱ ላይ አተኩሮ እስኪይዘው ድረስ እንደሚያሳድደው ሁሉ፣ የሚውጠውን ፈልጎ እንደሚያገሣ አንበሳ በዙሪያችሁ ይዞራል ለተባለው ባላጋራችን ዲያብሎስ፣ የግብር ልጆች የሆኑት ማኅበረ ቅዱሳንም በቅጥረኞቹ በኩል ነጥሎ በመምታት ስልቱ ብዙዎችን ግዳይ እየጣለ መሆኑ የማይረሳ ሲሆን፣ አሁንም እንደ አስፈላጊነቱ ይህን ስልት እየተጠቀመበት ቢሆንም፣ ለመብቱ የሚታገልና ማኅበረ ቅዱሳን በቤተ ክርስቲያናችን ዕድል ፈንታ እንዳይኖረው የሚቃወም ትውልድ እየተነሣ መሆኑ ስልቱን ጊዜ ያለፈበት (Out dated) እያደረገው መጥቷል፡፡ በዚህ በኩል በመምህር አሰግድ ሣህሉ ላይ የከፈተው ነጥሎ የመምታት ስልቱ እንዳልያዘለትና ነውራችሁን ይፋ አደርጋለሁ እያለ ያሻውን የሚያስፈጽማቸውን ቅጥረኛ ጳጳሳቱን ሁሉ በሕግ ፊት እያዋረዳቸው መምጣቱ ተመልክቷል፡፡ ማኅበረ ቅዱሳን በመምህር አሰግድ ሣህሉ ላይ የሸረበውና እስከ ኮሌጁ ዲን አቡነ ጢሞቲዎስ ድረስ ባደራጃቸው ጀሌዎቹ በኩል የሞከረው ነጥሎ የመምታት ስልቱ በሕግ ፊት ጭምር መክሸፉን የሚገልጽ ዘገባ በቀጣይ እንደምናስነብብ ከወዲሁ መግለጽ እንወዳለን፡፡
ይህ በእንዲህ እንዳለ የቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ ተማሪዎች ያሰሙትን ተቃውሞና በማኅበረ ቅዱሳን ላይ ያወጡትን ጠንካራ የአቋም መግለጫ በማግሥቱ የወጡ የግል ጋዜጦች አለመዘገባቸው የጋዜጦቹን ማንነት ያጋለጠ ተግባር ነው ሲሉ አንዳንድ የቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ ተማሪዎች መናገራቸውን ምንጮቻችን ገልጸዋል፡፡ ተማሪዎቹ ለአብነት የሚጠቅሱት በየሳምንቱ ዐርብ የሚታተመውንና “ፍትሕ” የተባለውን አፍቃሬ ማኅበረ ቅዱሳን የሆነውን ጋዜጣ ነው፡፡ ጋዜጣው በሚያዝያ 7 ዕትሙ በፊት ገጹ “የሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ ተማሪዎች ቅሬታቸውን ለፓትርያርኩ አቀረቡ” በሚል ርእሰ ዜና የሠራ ቢሆንም፣ በዜናው ሐተታ ውስጥ ግን ተማሪዎቹ በዋናነት የአቋም መግለጫ ያወጡበት የማኅበረ ቅዱሳን ጉዳይ ፈጽሞ ሳይጠቀስና ከዚህ ቀደም የተቃውሞ ድምፅ ያሰሙባቸውን የከረሙ ጉዳዮች ፈጽሞ ባልተነሡበት ሁኔታ እንዳዲስ በማቅረብ ዋናውን ጉዳይ አቅጣጫ ለማስለወጥ ሆነ ብሎ የተዘጋጀ አስመስሎታል፡፡ ከምንም በላይ ደግሞ ጋዜጠኛው ሳይጋደል አክሊለ ሰማዕትን ለመቀዳጀት የከጀለ ይመስል፣ የዘራውን ማጨዱን “እንግልት” አድርጎ መዘብዘቡ ትልቅ ትዝብት ላይ እንደጣለውና “ፍትሕ ጋዜጣ ሆይ! ከማን ወገን ነህ?” የሚል ጥያቄ እንዳሰነዘረበት ተጠቁሟል፡፡ ጋዜጠኛው “ምንጮቻችን” ያላቸውና “ፓትርያርኩም የተማሪዎቹን ቅሬታ አድምጠው ‘ይህ በአስቸኳይ ትእዛዝ የማስተላልፍበት ጉዳይ ነው’” ሲሉ ምላሽ እንደሰጡ የነገሩት ክፍሎች፣ የመግለጫውን ፍሬ ነገር ለምን ቀየሩት? ወይስ ጋዜጠኛው ይሆን የለወጠው? ሲሉ ታዛቢዎች ይጠይቃሉ፡፡ በብዙዎቹ የግል ጋዜጦች ውስጥ በአንድም በሌላም መንገድ የማኅበረ ቅዱሳን እጅ መኖሩን የሚናገሩት እነዚሁ ምንጮች፣ ጋዜጦቹ ማኅበረ ቅዱሳን የሚፈልጋቸውን ጉዳዮች ብቻ እያነፈነፉ ለማኅበረ ቅዱሳን ወግነው ከመዘገብ ውጪና የማኅበሩን “በጎ ገጽታ” ከመገንባት በቀር አንድም ጊዜ እንኳ የእርሱን ድክመትና መሠሪነት ሲዘግቡ እንደማይስተዋሉ ይናገራሉ፡፡ ይህም ጋዜጦቹ የቆሙት የማኅበረ ቅዱሳንን ፖለቲካዊ አጀንዳ ለማስፈጸም እንጂ፣ በገለልተኛነትና በነጻነት የሁሉንም ሐሳብ ሚዛናዊ ሆነው ለማስተናገድ አለመሆኑን የሚጠቁም ምስክር ነው፡፡    
ይህ በእንዲህ እንዳለ የተማሪዎቹ የአቋም መግለጫ በቀረበበት በዚሁ ዕለት፣ ቋሚ ሲኖዶሱ በሐዋሳ ለግጭቶች መንሥኤ የሆነውን በማኅበረ ቅዱሳንና ሐዋሳ ላይ በሚገኘው የማኅበረ ተስፋ ኪዳነ ምሕረት መካከል የተፈጠረውን ችግር ለመፍታት ባደረገው ስብሰባ በግጭቶቹ ዙሪያ ውሳኔዎችን አሳልፏል፡፡ በዚሁ መሠረት፡-
1.      አዲስ ተሹመው በሀገረ ስብከቱ የተመደቡትና ለማኅበረ ቅዱሳን ሽፋን ሲሰጡ የነበሩት ሊቀጳጳስ አቡነ ገብርኤል እስከ ግንቦቱ የሲኖዶስ ስብሰባ ወደ ሀገረ ስብከቱ እንዳይሄዱና ለጊዜው ሀገረ ስብከቱን ቅዱስ ፓትርያርኩ በሞግዚትነት እንዲያስተዳድሩ፣
2.     ማኅበረ ቅዱሳንና ማኅበረ ተስፋ ኪዳነ ምሕረት በሀገረ ስብከቱ ውስጥ በሚከናወኑ ማናቸውም የቤተ ክርስቲያኒቱ ጉዳዮች ውስጥ ምንም ዐይነት ጣልቃ ገብነት እንዳያካሂዱ፣
3.     በማኅበረ ቅዱሳን ኀይለኛ ውንጀላ በሐዋሳ ከተማ የሚገኙ የገብርኤል፣ የሥላሴ፣ የጊዮርጊስና የተክለ ሃይማኖት አድባራት አስተዳዳሪዎች የማኅበረ ተስፋ ኪዳነ ምሕረት ደጋፊዎች ናቸው የሚለውን ክስ ቋሚ ሲኖዶሱ ውድቅ በማድረግ በየተመደቡበት ቦታ አገልግሎታቸውን እንዲቀጥሉ ውሳኔዎችን አሳልፏል፡፡
ውሳኔው ማኅበረ ቅዱሳንን አንገት ያስደፋና ተሰሚነቱና ጫና መፍጠሩ እየተሸረሸረ መምጣቱን የሚያሳይ መሆኑን ምንጮቻችን ይገልጻሉ፡፡
ይህ በእንዲህ እያለ የቅዱስ ሲኖዶሱን ውሳኔ ተከትሎ በአንዳንድ የሀገራችን ክፍሎች የተቀሰቀሰው አንባጓሮ ማኅበሩ ለእግዚአብሔር፣ ለቅድስት ቤተክርስቲያንና ለመንግሥት አስተዳደር ስፍራ በሌላቸው ጨካኞች የሚመራ በለስ ቢቀናው ማንንም አጋድሞ ከማረድ የማይመለስ ቡድን መሆኑን የማያሳይ ሆኗል፡፡ በተለይም በሆሳዕና በአል ዋዜማ ቅዳሜ በ8/8/2003 ዓ.ም ቅዱስ ሲኖዶስ ባሉበት እንዲቆዩ ከወሰነላቸው አስተዳዳሪዎች መካከል የቅዱስ ገብርኤልን  ቤተ ክርስቲያን አስተዳዳሪ የማህበሩ መናጆ የሆኑ ሁለት መሪጌቶች በጋቢ አፍነው ለመግደል ሲታገሉ ድንገት በደረሰች አንዲት የሰንበት ተማሪ ጩኸት አስተዳዳሪው ከሞት ተርፈዋል፡፡ የወጠኑት ያልሆነላቸው መሪጌቶች በደመነፍስ ባነሱት ቆንጨራ ጩኸቱን ሰምተውና ተሯሩጠው ከመጡ የሰ/ት/ቤቱ አገልጋዮች መካከል አለማየሁ የተባለውን የሰንበት ት/ቤት አገልጋይ እጁን ሲዘነጥሉ፤ አሸናፊ የተባለውን የሰንበት ት/ቤቱን ምክትል ሊቀመንበር ደግሞ በያዙት ቆንጨራ አናቱ ላይ የከፋ ጉዳት አድርሰዋል፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘ አቶ ዘለቀ ሶርሳ የሚባለው ግለሰብ በመኪና ጭኖ ባቀረበው ድንጋይ ልጅ አዋቂ ሳይለይ በተፈፀመው ጥቃት ደግሞ ወ/ሮ እናኑ መኩሪያ የተባሉ እናት ቀኝ እጃቸው ከመሰበሩም ሌላ በቅጥቀጣው ሰውነታቸው ክፉኛ ተጎድቷል፡፡ እኒህን እናት ጨምሮ በርካታ ሰዎች ላይ ከፍተኛ ጉዳት ያደረሰው የማኅበረ ቅዱሳን ወጀብ ፈጥኖ በደረሰው የሰላም አስከባሪ ተኩስ ባይገታ ኖሮ ሊደርስ የሚችለው እልቂት ከዚህ ይከፋ እንደነበር በስፍራው የነበሩ የዐይን እማኞች መስክረዋል፡፡
የመቀደሻ አልባሳት መገበሪያና ጧፍ የሌላቸው ገዳማትን ለመርዳት እያለ በተዘጉ አብያተ ክርስቲያናት ስም ገንዘብ ሲያካብት የኖረው ማኅበረ ቅዱሳን፤  ባከማቸው ገንዘብ ለወንጌል የተከፈቱ ደጆችን ለማዘጋት መትጋቱ፣ ከሀይማኖት ውጪ ለሆነ አላማው ስኬት አብረውት ያልተሰለፉትን መጉዳቱ፣ በተለይም አበይት በዓላትን አስታኮ የሚለኩሰው እሳትና የሚያደርሰው ጥፋት በየትኛውም መመዘኛ ኦርቶዶክሳዊ ወይም ክርስቲያናዊ ባልሆነ ሸፍጥ ውስጥ እንዳለ ጠቋሚ ነው፡፡ በተለይ ለተከታታይ አመታት አብይ ጾምን ተከትሎ በሚፈጥረው ውዥንብር የበረከቱን ወቅት የመርገምና የመከራ እንዳደረገው የታዘቡ አንድ አረጋዊ ዓብይ ጾም ለማኅበረ ቅዱሳን ‹‹ረመዳኑ ነው እንዴ?›› ብለው መጠየቃቸው ተሰምቷል፡፡ የያዛቸው አባዜ እስከዚያ አያደርሳቸውም እንጂ ለከርሞ አብሮን ከዘለቁ የከዚ በፊቱን ልብ ብሎ ያላየ የዚህ ጽሑፍ አንባቢ መጪውን የ2004 ዓብይ ጾም ‹‹ረመዳን›› አርገውት በሌላ በከፋ መከራና ሀዘን እንደሚያያቸው ስንጠቁም ‹‹አንባቢው ያስተውል›› የሚለውን የመጽሐፍ ቃል እንዲያስታውሰው በማስገንዘብ ነው፡፡
በሌላ በኩል ደግሞ የማኅበረ ቅዱሳን አባል በመምሰል ሙሴ ነኝ በማለት ለብፁዕ አቡነ ገብርኤል ስልክ ደውለው የነበሩ የገፈቱ ቀማሽ ወጣቶች ሲናገሩ፤ አቡነ ገብርኤል ‹‹አይዟችሁ በርቱ የወያኔ ካድሬ የሆኑት ፓትርያርክ ትንሽ እንቅፋት ሆነውብኛል፡፡ እናንተ በርቱ ምንም የሚመጣ የለም፤ እኛ እናሸንፋለን ›› ሲሉ የማበረታቻ ቃል መናገራቸውን  በሞባይል ከተቀረጸው ድምፃቸው ማረጋገጥ ችለናል፡፡
በሌላም በኩል  መንፈሳዊ ተቋም ነኝ ካለው ማኅበር በእጅጉ ተሽለው የተገኙት የጥበቃ ሰራተኞችና፣ የክልሉ ባለስልጣናት እንደከዚህ ቀደሙ የቤተ ክርስቲያኑ በር እንዳይዘጋ ‹‹ነገ ህፃን አዛውንቱ የዘንባባ ዝንጣፊ ይዞ የሚያከብረው የሆሳዕና በዓል ነው፤ ደጁ መቆለፍ የለበትም፤›› በማለት ሀዘኑ እጥፍ ድርብ እንዳይሆንና ዝንት ዓለም የሆሳዕና በዓል በመጣ ቁጥር የሚታወስ ጠባሳ እንዳይኖር ስለ አደረጉት ማስተዋል የተመላበት ውሳኔ በቅድስት ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን እንዲሁም የቤተ ክርስቲያን ራስ በሆነው መድኃኔ ዓለም ኢየሱስ ክርስቶስ ስም ሳናመሰግንናቸው አናልፍም፡፡ ይህንንም ተከትሎ የሆሳዕና በዓል የከተማው ወጣቶች ለጥምቀት በዓል በገዙት ምንጣፍ ግቢው አጊጦ ሀዘኑን በሚያስረሳ ድምቀት ‹‹ሆሳዕና ለዳዊት ልጅ ሆሳዕና አቤቱ አድን አቤቱ አቅና›› በሚሉ ዝማሬዎች ደምቆ ተከብሯል፡፡
EBS የቴሌቪዥን መንፈሳዊ አገልግሎት እየተጠናከረ መሄዱ ተመለከተ
በዐረብ ሳት እየተላለፈ ባለው EBS የቴሌቪዥን መርሐ ግብር ላይ በመጋቤ ሐዲስ በጋሻው ደሳለኝ፣ በመምህር በሪሁን ወንድወሰን፣ በመምህር ያሬድ አደመ እና በዘማሪ ዲያቆን ትዝታው ሳሙኤል የተጀመረው በየሳምንቱ እሑድ ከ4፡30-5፡00 ሰዓት የሚተላለፈው የግማሽ ሰዓት የቴሌቪዥን መንፈሳዊ አገልግሎት፣ ወቅታዊ በሆነ የቤተ ክርስቲያን ጉዳይ ላይ መልእክት አስተላለፈ፡፡
ለመልካም ነገር ባልታደሉ አሉባልተኞች ብዙ ሲነቀፉ የነበሩት የየEBS መንፈሳዊ አገልግሎት ጀማሪ አገልጋዮች የሆኑት እነመጋቤ ሐዲስ በጋሻው፥‹‹
ይሁን እንጂ ለግብር አባታቸው ለዲያብሎስ እንጂ ለቅድስት ቤተ ክርስቲያንም ሆነ የእናት ቤተ ክርስቲያንን ጉዳት ማየትም ሆነ መስማት ለሚሰቃቸው የቤተ ክርስቲያን ልጆች ቦታ በሌላቸው የማቅ ቅጥረኞች ጉዳዩ ለጠላት ደስታ ለምዕመናንና ምዕመናት የልብ ስብራት መሆኑን ያስተዋሉ፣ ‹‹እነሱ በክፋት እናንተ ደግሞ ለበጎ በሆነ ቅንዓት ብትገለጡ ምናለ? ለምን ዝም አላችሁ? የእናንተ ዝምታ ለእነርሱ የልብልብ ሰጥቷቸዋል፡፡ ጉዳዩን ዓለም በተዛባ ሁኔታ እየሰማው ነው፣›› የሚል ግፊት በማሣደራቸው፤ ጉዳዩን ይፋ ለማድረግ የተገደዱት የስርጭቱ ባለቤቶች በውሸት ግራ ለተጋባው ሕዝብ እረፍት፣ ጉዳዩን በዚህ መልኩ ላላየው ፣ማስተዋል፣ ለቤተ ክርስቲያን ልጆች ተስፋ ሰጪ የሆነ መልዕክትን አስተላልፈዋል፡፡ እንደ ቀድሞ ማህበረ ቅዱሳን በምላሱ የነደፋቸው የሚመረዙበት እርሱ ቤታችሁ አይደለም ያላቸው ሁሉ ልባቸው እያወቀ እንደርሱ በሀይልና በተንኮል መገዳደር ስላልቻሉ እያለቀሱ ከቤታቸው እየወጡ በማያምኑበት መስመር ለመጓዝ የተገደዱበት ዘመን አብቅቷል፡፡ ዛሬ ከቤቱ ንቅንቅ የሚል አይኖርም ያሉት የፕሮግራሙ መሪዎች ሕዝቡም ቢሆን እንደአለፈው ዘመን እነሱ ጣት በቀሰሩበት ላይ ድንጋይ ለመወርወር ሆን ብሎ እንደማይነሳ ከዓለምና ከሞት ማጀት ጎትቶ ያወጣን የእነዚህ ተነቃፊዎች ዝማሬና ስብከት አይደለም እንዴ? እያለ ከነሱ ውንጃላ ይልቅ ተነቃፊቹ የሰበኩለት ወንጌል እንዳተረፋቸው መናገራቸውን ጠቆም አድ
በተለይም በተለያየ ጊዜ የሚነሳበትን የፓለቲካ ጥያቄ የትኩረት አቅጣጫ ለማስቀየር የአባይን ወንዝ ጉዳይ እያቀነቀነ ሕዝቡን በሚፈልገው መንገድ ሲነዳ እንደነበረው የግብጽ አስተዳደርዛሬም ሕዝባችን ለቅዱሳን ያለውን ከንጹህ ልብ የሚወጣ ፍቅር በመረዳት በቅዱሳን በተለይም አምላክን በወለደች በእመቤታችን የሚመጣበትን እንደማይወድ በመረዳት የጠሉዋቸውን ለማስጠላት በተሐድሶና በሌላ ውንጀል ማኅበሩ አገልጋዩን ከተገልጋዩ ለማጋጨት የሚያደርገው ጥረት እንዳለፈው ዘመን እንደማይሳካለት አስገንዝበዋል፡፡
አገልግሎቱ የቤተክርስቲያንን በጎ ነገር በሚናፍቁ በቅንነት በገባቸው መንገድ ያለውን እድልና ቴክኖሎጂ ለሰይጣን ውርደት፣ ለሕዝብ ጥቅምና ለእግዚአብሔር ክብር ለማዋል አቅምና እድሜያቸው ከሚፈቅደው አልፈው እየሰሩ ያሉትን ያደለው ‹‹እጁን ለበጎ በማበርታት በገንዘብ፣ በዕውቀት(በሀሳብ) በጉልበትና በልዩ ልዩ አስተዋጽኦ ሲደግፍ ያልታደሉት ደግሞ አለመተባበራቸው አንድም በጎ አስተዋፅኦ አለማድረጋቸው ሲያስገርም እንደ እነ ጦቢያና ሰንባላጥ ዳር ቆመው ‹‹ቤተክርስቲያን የማታውቀው›› እያሉ የአለማውያን መጽሔት ማጣፈጫ መሆናቸው አይ ቤተ ክርስቲያን ስንቱን ተሸክመሻል አሰኝቷል፡፡
እንደ እነ ነህምያ እንደ አንድ ልብ መካሪ እንደ አንድ ቃል ተናጋሪ በመሆን ‹‹የሰማዩ አምላክ ያከናውንልናል እኛም ባሪያዎቹ ተነስተን እንሰራለን›› ያሉት አገልጋዮች ከየኪሳቸው በማውጣት ለ4ት የጀመሩት አገልግሎት ሰምሮላቸው አገልግሎታቸውን የሚያስፋፉበት ድጋፍ በቅርብ ከሚያውቋቸውና ትጋትና ድካማቸውን በመልካም ከተረዱላቸው ጥቂት ሰዎች በተደረገላቸው ድጋፍ አገልግሎቱን ከ30 ደቂቃ ወደ አንድ ሰዓት ለማሳደግ ቆርጠው ተነስተዋል፡፡
ይህ በእንዲህ እንዳለ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ፓትርያርክ ሰሞኑን (በ2003 ዓ.ም) ባከበርነው የትንሳኤ በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት በመላው ዓለም ለሚተላለፈው ታኦሎጎስ የEBS ፕሮግራም ቡራኬና ቃለ ምዕዳን ሰጥተዋል፡፡ የአገልግሎቱን በረከት ለቴክኖሎጂው ቅርብ በሆነ ማስተዋል ከሌሎች ቀድመው የሚገነዘቡት ቅዱስ ፓትሪያርኩ ‹‹አይዟችሁ በርቱ! እደጉ! ልጆቼ›› ከሚለው የዘወትር ተስፋና ማበረታቻ ባሻገር በመንበረ ፓትርያርክ የስብከተ ወንጌል አደራሽ ተገኝተው ለ EBS ፕሮግራም አዘጋጆችና አቅራቢዎች እንዲሁም በመላው ዓለም ለሚገኙ ሕዝበ ክርስቲያን ባስተላለፉት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት፥ ‹‹የክርስትና አስኳሉ ፍቅር ነውና በሩቅም በቅርብም ያለን ሁላችን በፍቅር እንኑር›› በማለት አባታዊ ምክርና መመሪያ አስተላልፈዋል፡፡ ይህን ቡራኬና የፍቅር መልዕክት በEBS ሲተላላፍ ያዩና የሰሙ ፕሮግራሙ ወይንም ስለEBS አገልግሎት ከዚህ በኋላ ምን ይሉ ይሆን? እነርሱ የሚሉትን ባያጡም እኛም ያምንለውን ብለናል፡፡ አምላክ በነገር ሁሉ ማስተዋልን ይስጥልን፡፡
ወግ ማዕርግ ለሆናችሁን በቃለ ወንጌልና በጥኡም ዝማሬ የቅድስት ቤተክርስቲያን ፈርጥ የሆናችሁን የEBS አዘጋጆችንም ብዙ፤ እልፍ አዕላፍም ሁኑልን፡፡ ዘወትር በመልካም እንድናያችሁ አምላክ ከናንተ ጋር ይሁን እንላለን፡፡

‹‹የባርነት ልጆች››(ገላ. 4፥21-31) "DejeSemay.org

የገላትያ መልእክት ዐቢይ ዓላማ በክርስቶስ አምነው ከጸጋው ቃል ወደ ኋላ በመመለስ እውነትን ይቃወሙ ለነበሩ ምዕመናን የተጻፈ ነው፡፡ ሐዋርያው በዚህ መልእክት ላይ የተለያዩ ምሳሌዎችን በመጠቀም እንዲሁም በቀደመው ኪዳን ስለበነሩ ነገሮች በመጥቀስ የገላትያ ምዕመናን አስቀድሞ ከተሰበከላቸው የክርስቶስ ወንጌል የተለየ ወንጌልን የሚሰብክ ሰውም ይሁን መልአክ የተረገመ ይሁን!›› በማለት በሐዋርያዊ ሥልጣኑ ይገዝታል (ገላ. 18)፡፡
በገበሬ እርሻ ላይ ምርጥ ዘር ከተዘራ በኋላ ዘሩ መብቀል ሲጀምር ቀድሞ ያልነበረ ነገር መታየቱ አይቀርም፡፡ ይህም የሚሆነው መልካም ነገር ሁሉ ተቃዋሚ ስላለበት ነው፡፡ ከዚህም የተነሣ መልካም ነገር ኃላፊነት ነው፡፡ ጥበቃና እንክብካቤም ይፈልጋል፡፡ ያለበለዚያ ለፍሬ አይበቃም፡፡ ጌታም በእርሻው ላይ ስለተዘራው መልካም ዘር ከተናገረ በኋላ ሰዎቹ ሲተኙ ጠላት መጥቶ እንክርዳድ እንደዘራና እንደሄደ ለደቀ መዛሙርቱ ሲናገር እናያለን፡፡ (ማቴ. 1324-30)
በዚህ ዘመንም በእውነተኛው የወንጌል አገልግሎት ላይ እንክርዳድ ለመዝራት የተሠማሩ፣ ሕዝብ የክርስቶስን ወንጌል እንዳይሰማ በተረትና በወግ እንዲሁም የራሳቸውን የጥቅም ፍላጎት ለማሳካት በሚያመች ሁኔታ ተብትበው ሕዝብን ለባርነት የሚወልዱ ብዙ ናቸው፡፡
እነዚህ ወገኖች ቀድሞውንም የጽድቅ አገልጋዮች አይደሉም፡፡ መቼም ሰው ሁሉ ባለበት መንፈሳዊ ደረጃና ኑሮ ከታመነ፣ ይህ ሰው ለእግዚአብሔር መንግሥት ቅርብ ነው፡፡ ነገር ግን መንፈሳዊውን አገልግሎት አንድ የትርፍ መንገድ አድርጐ መያዝና ለማይኖሩበት እውነት መሟገትን የመሰለ የድፍረት ኃጢአት የለም፡፡
የክርስቶስ ወንጌልን የሚሰብኩትን ስም እየሰጡ እንዳያገለግሉ በማድረግ፣ ለክርስቶስ ክብር የሚቀርበውን የምሥጋና መሥዋዕት /ዝማሬ/ ሁሉ የሚያወግዙ፣ ይህ የእኛ አይደለም በሚል ፈሊጥ የሁሉም ነገር ጀማሪዎች እኛ እንደሆንን እንድናስብና ከእውነተኛው አምላክ እንድንለይ የሚያደርጉ፣ የክርስቶስ ስም የተጠራበት ዝማሬም ሆነ ስብከት የማይጥማቸው እነዚህ የመስቀሉ እንቅፋትና የባርነት ልጆች ናቸው፡፡
ወገኖቼ ! በወንጌል አምነናል እያልን ክርስቶስን የሚስጠላ ማንነት ካለን ስሙ ሲጠራም የምንደነግጥ ከሆንን ራሳችንን መፈተሽ ይኖርብናል፡፡ የማን ስም ይሰበክ? የማን ማዳን ይነገር? የማንስ ስም ይመስገን? በስሙ እየተጠራን እርሱን ከመቃወም ያድነን!
ሳይማሩ አውቃለሁ እንደማለት ያለ ድንቁርና የለም፡፡ የብዙዎች ችግር ይህ ነው፡፡ የሚማር መንፈስ የሌላቸውና ለመቃወም ብቻ የሚኖሩ፣ ግመል እየዋጡ ትንኝ የሚያጠሩ፣ ተረፈ ፈሪሳውያን ዛሬም ሞልተዋል፡፡ እነዚህ ወገኖች በገበያ ግርግር ተንጠላጥለው የቤተ-ክርስቲያንን ዓውደ ምሕረትና ልዩ ልዩ የአገልግሎት ሥፍራ የተቆጣጠሩ ሲሆን የጽዋ ማኅበራቸው አባል ያልሆነ ‹‹ኦርቶዶክሳዊ አይደለም›› በማለት ሰውን ሁሉ የአሳባቸው አገልጋይ (ባሪያ) ለማድረግ የሚተጉ ናቸው፡፡
እንደሚታወቀው የሽሽግር ወቅት /Transition Period / ተብሎ የሚጠራው ጊዜ ሲከሰት ይልቁንም የመንግሥት ለውጥ ሲደረግ የሚሞቱና ትንሣኤ የሚያገኙ ወገኖች ይኖራሉ፡፡ አንዳንዶች ወደ ድህነት ቀጠና ይወርዳሉ፡፡ ሌሎች በግርግሩ ዘርፈው ከባለጠጎች ጎራ ይቀላቀላሉ፣ አንዳንዶችም ሕይወታቸውን በማጣት ወደሞት ይሻገራሉ፡፡ በአንድም በሌላም የመጣው ለውጥ ብዙ ለውጦችን ይወልዳል፡፡
በአገራችን ታሪክም የደርግ መንግሥት ሲወድቅና አሁን በሥልጣን ላይ ያለው መንግሥት ሲተካ ይህ ሁኔታ ታይቷል፡፡ ራሱን ‹‹የቅዱሳን ማኅበር›› እያለ የሚጠራው ይህ የጽዋ ማኅበር ዛሬ ለደረሰበት ደረጃ የበቃው በዚህ ግርግር ነው፡፡ እየቆየ ሲሄድ ግን ራሱን እንደ አንድ ‹‹ሲኖዶስ›› መቍጠር ጀመረ፡፡ ብዙዎችም ለባርነት ወለደ፡፡ የመጣበትን ስለረሳው የሚሄድበት ቢጠፋው አያስደንቅም፡፡ ይሁን እንጂ ዛሬም በንስሓ ለመመለስ በሩ ክፍት ነው፡፡
የእግዚአብሔር ቃል፡- ‹‹በነጻነት ልንኖር ክርስቶስ ነጻነት አወጣን›› (ገላ. 5፥1) ይላል፡፡ ነጻነት ሁለንተናዊ ነው፡፡ ሰው ለተገዛለት ለዚያ ባሪያ እንደሆነም መጽሐፍ ቅዱስ ይነግረናል፡፡ ሰው ነጻ ግዛት ባለመሆኑ ለአንድ ጌታ መገዛቱ የግድ ነው፡፡ በክርስቶስ ያገኘነው መዳንም ከብዙ ባርነት ነጻ የወጣንበት ሲሆን ክርስትናም ራሳችንን ለዚህ ጌታ ባሪያ አድርገን የሰጠንበት የፍቅር ግዛት ነው፡፡ ቀድሞ የማይገዛንና በእኛ ላይ ያልሠለጠነ አልነበረም፡፡ ከመዳን በፊት የነበረን መታወቂያ ሁሉ የሚያሳፍር ታሪክ መዝገብ ነው፡፡ ኢየሱስ ክርስቶስ ግን የጽድቅ ባሪያዎች አድርጐናል፡፡
ወገኖቼ! አገልግሎታችንን መፈተሽ ይገባል፡፡ ሆዳችን አምላካችን ሆኖ ዛሬም ጥቅም የሚገዛንና በመንፈሳዊ አገልግሎት ስም የራሳችንን ፍላጎት ለማሳካት የቆምን ከሆንን የባርነት ልጆች መገለጫ ይህ ነው፡፡ መንፈሳዊ አገልግሎት የጸጋና የጥሪ ጉዳይ እንጂ የትምህርት ማስረጃ (የዲፕሎምና የዲግሪ ወዘተ…) ጉዳይ አይደለም፡፡ እውቀት እንጀራ ለመብላት ይጠቅም ይሆናል፡፡ ለመንፈሳዊ አገልግሎት ግን ጥሪና ጸጋ ያስፈልጋል፡፡ ሰዎችን ከተለያዩ የትምህርት ተቋማት በመመልመል የቤተ-ክርስቲያን አገልጋዮች ለማድረግ ማቀድና በዚህም ቤተ ክርስቲያንን ሙሉ በሙሉ ለመቆጣጠር ማሰብ፣ በገንዘብ ኃይል በመደራጀትም ተከታይ ለማብዛት ማቀድ፣ ለጊዜው አሸናፊ ሊያስመስል ይችላል፡፡ ኢየሱስ ክርስቶስ ግን በትንሣኤው ሞትን ሳይቀር የረታ በመሆኑ የወንጌሉን የምሥራች የሚገታው የለም፡፡ የወንጌል አገልጋዮችንም በማሳደድ እውነትን ማስቀረት አይቻልም፡፡
የአብርሃም ልጆች ብዙ ቢሆኑም በዋነኛነት ግን የሚታወቁት ሁለቱ እስማኤልና ይስሐቅ ናቸው፡፡ እነዚህ ሁለት ልጆች የአብርሃም ልጆች ቢሆኑም የተለያየ ማንነት አላቸው፡፡ እስማኤል ከእግዚአብሔር የተስፋ ቃል ውጪ የተወለደና በሥጋ ልደት የተገኘ ነው፡፡ ይስሐቅ ደግሞ አስቀድሞ የተስፋ ቃል የተነገረለትና በእግዚአብሔር የተስፋ ቃል የተወለደ እውነተኛ የአብርሃም ወራሽና የተስፋው ቃል ፍጻሜ ነው፡፡
በእነዚህ ሁለት ልጆች መካከል ትልቅ ልዩነት አለ፡፡ ይኸውም የእግዚአብሔር የተስፋ ቃል የሚፈጸመው እንደ ቃሉ በተወለደው በኩል በመሆኑ እንደ ሥጋ ፈቃድ የተወለደው እስማኤል ይስሐቅን የሚጠላና የሚያሳድድ እንደነበር ተገልጧል፡፡ ‹‹ነገር ግን እንደ ሥጋ የተወለደው እንደ መንፈስ የተወለደውን በዚያን ጊዜ እንዳሳደደው ዛሬም እንዲሁ ነው›› (ገላ. 429)፡፡
እንደ ሥጋ የተወለደ በማለት የገለጠው እስማኤልን ነው፡፡ ይኸውም እስማኤል የተወለደው አብርሃም መውለድ በሚችልበት ወቅት በአብርሃምና በሣራ ምክር ከባሪያይቱ ከአጋር ነው፡፡
በዚህ አሳብና ምክር እንዲሁም ሥራ ውስጥ እግዚአብሔር የለም፡፡ እስማኤል ቢወለድም የጠብና የሁከት ምክንያት እንጂ የቤቱ ደስታ አልሆነም፡፡ ዛሬም በእግዚአብሔር ቤት ውስጥ እንደ እስማኤል የተወለዱ አሉ፡፡ እነዚህ ወገኖች በእግዚአብሔር ቃል የተወለዱ ሳይሆኑ በሥጋዊ እውቀትና በራስ ችሎታ እንዲሁም በሥጋ ምክር የልጅነት እውቅና የተሰጣቸው ናቸው፡፡ ሌላው ቀርቶ ብዙዎቹ የአገልግሎት መሥፈርትን እንኳ ሳያሟሉ የአገልግሎት ሥፍራዎችን የተቆጣጠሩ ጨዋዎች ናቸው፡፡ (ጨዋ የሚለው ቃል በቤተ ክርስቲያን ቋንቋ ያልተማረ ማለት ነው)፡፡
እንደ እነዚህ ያሉ በመወለዳቸው ዛሬ ቤተ-ክርስቲያን ትታመሳለች፡፡ ሌላው ቀርቶ ገደባቸውን እንኳ ባለማወቃቸው ‹‹ቅዱስ ሲኖዶስ›› እያለ ተክተው ለመሥራት የሚያስቡና የሚያወግዙ እንዲሁም የራሳቸውን አሳብ ለማስፈጸም የሚሯሯጡ ናቸው፡፡ እስማኤል ይስሐቅን እንደ ጠላው፣ አጋርም ሣራን እንደናቀች እነዚህም ወገኖች ከእነርሱ ውጪ ያለውን እንዲሁ የሚመለከቱ ናቸው፡፡ እንደ መንፈስ ፈቃድ የተወለደው ይስሐቅ ነው፡፡ ይስሐቅ የተወለደው በእግዚአብሔር ፈቃድና ችሎታ ነው፡፡ አብርሃምም ሣራም ምንም ማድረግ በማይችሉበት ወራት የተወለደ የእግዚአብሔር ስጦታ ነው፡፡ ይህም የእግዚአብሔር ልጆች ተብለን ለመጠራት የሚያበቃን ከእርሱ የሆነልን ነገር ብቻ መሆኑን ይገልጣል፡፡ ክርስትና የዘር ውርስ አይደለም፡፡ ከእግዚአብሔር ቃል ጋር በመስማማት የተሰጠን የመዳን ጸጋ ነው፡፡ ቃሉም እንዲህ ይላል ‹‹ጸጋው በእምነት አድኖአችኋልና፤ ይህም የእግዚአብሔር ስጦታ ነው እንጂ ከእናንተ አይደለም፤ ማንም እንዳይመካ ከሥራ አይደለም›› (ኤፌ. 2፥8)፡፡ እንግዲህ በልጅነት ለመጠራት፣ ለማገልገልና ለመውረስ የእግዚአብሔር ጸጋ ያስፈልጋል፡፡ ቃሉም ‹‹የእግዚአብሔር ስጦታ ነው እንጂ ከእናንተ አይደለም›› ይላልና፡፡
ሐዋርያው እነዚህን ሁለት ልጆች በምሳሌነት ያነሣው ‹‹ዛሬም እንዲሁ ነው›› የሚለውን ለመግለጥ ነው፡፡ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክሳዊት ቤተክርስቲያንም ያለውን ሁኔታ ስንመለከት ዛሬም እስማኤላውያን እንደ ተስፋ ቃሉ የተወለዱትን ሲቃወሙና ሲያሳድዱ እናያለን፡፡ ከየዓውደ ምሕረቱ፣ ከየአድባራቱ፣ ከየገዳማቱ ወዘተ፡፡ በእርግጥም እውነተኛ ኦርቶዶክሳውያን የቤተ-ክርስቲያን ልጆች ዛሬም እንደሚሰደዱ ቃሉ ያረጋግጣል፡፡ ይሁን እንጂ እንደ ተስፋ ቃሉ ወራሾች እነርሱ ናቸው፡፡ ቃሉም እንዲህ ይላል፡- ‹‹የባሪያይቱ ልጅ ከጨዋይቱ ልጅ ጋር አይወርስም ባሪያይቱን ከልጅዋ ጋር አውጣት፤ ስለዚህ ወንድሞች ሆይ የጨዋይቱ ልጆች ነን እንጂ የባሪያይቱ አይደለንም›› (ገላ. 430-31)፡፡
ከላይ እንደተገለጠውና ‹‹ባሪያይቱን ከልጅዋ ጋር አውጣት›› እንደተባለ ዛሬም የእግዚአብሔር ፍርድ ሲገለጥ አሳዳጆች ይወጣሉ፡፡ ልጆች ይወርሳሉ፡፡ ለውርስ የሚያበቃው ከጨዋይቱ መወለድ ነው፡፡ የሚሰደዱ እንጂ የሚያሳድዱ የክርስቶስ አይደሉም፡፡
ወስብሐት ለእግዚአብሔር !