Wednesday, February 16, 2011

ሰውን የምንወደው ለጥቅም ነው።(King Nafkote)



በዚህ ምድር ላይ የሰው ልጅ ከሰው ልጅ ጋር ተስማምቶና ተዋዶ መኖሩ ሰብዕናው የቸረው ግዴታው ነው ሆኖም አመላችን እንደመልካችን ዝንጉርጉር ስለሆነ አንዱ አንዱን የሚወደው ከጥቅሙ አንጻር እንጂ እንዲሁ ከመሬት ተነስቶ አይደለም።

ብዙዎቻችን እስከ ዛሬ የኖርንበትን ሕይወት ወደኋላ ዘወር ብለን ብንመለከት ፍጹም ልንደነቅ እንችላለን።  ማናችንም ብንሆነ በዚህ ምድር ላይ የምንኖር ሰዎች በሕይወታችን ወደናቸው ያለፍናቸውን ሰዎች ወይም ዛርም ድረስ የምንወዳቸውን ሰዎች ብንመረምር ከነሱ በምናገኝ ጥቅም ወደድናቸው እንጂ እንዲሁ ዝምብለን አልወደድናቸውም።  በዚህ ዓለም እንዲሁ የሚወደን ወይም የወደደን አንድ ጌታ ብቻ ነው። በዚህ ዓለም የወለደችን እናታችን እንኳ አለአንዳች ጥቅም አትወደንም እንዲሁም የወለድናቸው ልጆቻችን አለጥቅም አይወዱንም ስለዚህ በዚህም ምድር ላይ በቀጥተኛም ሆነ በተዘዋዋሪ መንገድ ሰዎችን የምንወደው ከምናገኘው ጥቅም የተነሳ ነው። ብዙዎቻችሁ ምን ማለቱ ነው? እኔ ሰውን የምወድው ለጥቅም ነው ማለት ነው? ሌላውስ ይሁን እናቴን? እንዴት የወለድኩት ልጄ ለጥቅም ብሎ ይወደኛል? ምንድነው ይሚያወራው እንደምትሉ አልጠራጠርም ምክንያቱም ስለዚህ ነገር ስመረምር እኔም ከራሴ ጋር ተኳርፌ ነበርና ሁላችሁም የምለውን ነግረ በጥሞናና ጽፈፌነዕ በመረዳት መንፈስ ካነበባችሁት የምናገረው ወይም ማለት የፈለኩትን በስነሥርዓት መረዳት ትችላላችሁ ማለት ነው መልካም ንባብ።

እስቲ እራሳችሁን መርምሩ ለምሳሌ እናቶች ወይም አባቶች ልጆቻችሁን ከነሱ ከምታገኙት ጥቅም የተነሳ ነው። የምተወዱት ያልኩበትን ላስረዳችሁ ለምሳሌ ገና ለገና በመውለዳችሁ ለመከበር ፈልጋችሁ፣ ልጆቻችን አድገው አንድ ነገር አየደርጉልናል ብላችሁ፣ ጧሪ ቀባሪ አለን ብላችሁ፣ ቢቸግራን ከጎናችን አይርቁም በመከራ ቀን ከአጠገባችን ይሆናሉ ብላችሁ፣ ዘራችሁ በምድር ላይ ጠፍቶ እንዳይቀር በነሱ ምክንያት የመኖራችሁ ተስፋ በመሆናቸው፣ ሲያገቡ ሲመረቁ ሲወልዱ የነሱ ደስታ የናንተ ደስታ ስለሆነ እንዲሁም በህይወት መኖራቸው ስለሚስደስታችሁና ውስጣችሁ ከዛ ደስታ የተነሳ ስለሚጠቀም የመኖራቸውም ምስጢር ትቅም ነው ማለት ነው።  እነዚህ ሁሉ ለቤተሰቦች ልጆቻቸውን ለመውደድ እንደምክንያት አርገን ልንጠቀምባቸው እንችላልን። 

እንዲሁም ልጆች ቤተሰቦቻቸውን የሚወዱበት የተለያየ ምክንያት አለ ከነዛም ውስጥ ወልደው ስላሳደጓቸው ስለሚንከባከቧቸው በችግር በመከራ ጊዜ ከጎናቸው ስለማይለዩ በጨንቃቸው ቢጠባቸው የሚፈልጉትን ነገር ከማንም በበለጠ ሁኔታ ከነሱ ማግኘት ስለሚችሉ ጠዋት ማታ ስለሚጨነቁላቸውና በዚህ ምድር ያለው ጥሩ ነገር ሀሉ የነሱ እንዲሆን ስለሚጥሩላቸው የፍላጎታቸው መሟላት ሲበዛ መውደዳቸው ይበዛል በተጨማሪም ምንም እንካን ባያደርጉላቸው በህይወት ከጎናቸው መኖራቸው ለነሱ ብርታት ነውና ያንን ብርታት በነሱ ስላገኙ ተጠቀሙ ማለት ነው አሁንም ወውደዳቸው በጥቅም ላይ የተመሰረተ ነው ማለት ነው። ብዙ መጻፍ ይቻላል ከብዙ በጥቂቱ ይሄንን ይመስላል።

ባል ለሚስ ሚስት ለባል ያለው ፍቅርስ በምን መንገድ በጥቅም ላይ የተመሰረተ ይሆናል? እሱም ልክ እንደ ሌላው በጥቅም ዙሪያ ነው።  ለምሳሌ ሚስት ባሏን የወደደችእው ከሱ በምታገኘው የተለያዩ አይነት ጥቅሞች ሊሆን ይችላል እንደሂም ባል ሚስቱን እሷን የፈለጋት ለተለያዩ አይነት ጥቅሞች ይሆናል።  እንደው መጀመሪያ እንካን ሲተዋወቁ በመተያየት ብቻ ተዋደው ነው ከተባለ እሱ እሷን በማየት እሷ እሱን በማየት ተደስተዋል ስለዚህ ሁለቱም ውስጣቸው ተጠቅሟል ማለት ነው። ስለዚህ ከመተያየት አንስቶ እስከ አብሮ መኖር ኪዚያም ወውለድ ማርጀት መሞት ደርስ ወደድንም ጠላንም ህይወታችን በተለያዩ መንገዶች በጥቀም ላይ የተመሰረተ ይሆናል ማለት ነው።

የጓደኛማቾች ፍቅር ልክ እንደሌሎቹ በጥቅሙ ዙሪያ ተጀምሮ በጥቅም ዙሪያ የሚያልቅ ነው።  አንዱ አንዱን የሚወደው ሲያደርገልት ወይም ሲያስደስተው እንደመሆኑ መጠን በጣም የምንወዳቸው የምንላቸውን ጓደኞቻችንን በምን ምክንያት በጣም እንደወደድናቸው እንመርምር በእርግጥ በግልጽ በሚያደርጉልን ነገር ብቻ ላይሆን ይችልላል ለኛ ባላቸው ጥሩ አስተሳሰብ ሊሆን ይችላል ክፉ ባለመሆናቸው ሊሆን ይችላል።  ምንም ሆነ ምንም አንዱን ከአንዱ አብልጠን ይምናይበት የጥቅም ሚዛን አለ በዛ በጥቅም ሚዛን ላይ መዝነናቸው ሚዛናቸው የደፉተን በጣም የምንወዳቸውንና የምናቀርባቸው አርገን እንናገራለን ነገር ግን እንደዛ የወደድናቸው አለጥቅም እንዳልሆነ እራሳችንን ባሀሰት ለማሳምን እንሞክራልን ምንክንያቱም ወስጣችን እውነቱን መቀበል ስለማይፈልግ ብቻ ነው። 

ስለዚህ በዚህ ምድር ላይ እንዲሁ የወደደን የሚወደን ጌታ አንድ አምላክ ብቻ ነው።  ከዚያ ውጪ ማንም ሆነ ማንም እንዲሁ አይወደንም እኛም አንወድም።  እራሳችሁን መርምሩ ስንት ቀን የኔ ያላችሁት ሰው አንድ ቀን ሲበድላችሁ በደሉ ከተሰማችሁ ፍጹማን አይደላችሁም ማለት ነው ሰዎች ናችሁ ስሜታችሁ ሊያዝን ይችላል ደሞም ያዝናል ነገር ግን እግዚአብሄርን እዩት እየገደልነው አፈቀረን እየጠላነው ወደደን እየሸሸነው ቀረበን። ከፍቅር በላይ ፍቅር ለዛውም እውነተኛ ዘላለማዊ ፍቅር ማለት ይሄ ነው unconditional love ማለት ከጌታ የምናገኘው ብቻ ነው።  ነገር ግን ያፍቅር ለኛ አልሰጠንም ማለት አልችልም አልተጠቀምንበትም ለማለት እንጂ።  መክንያቱም ጌታ እነደራሱ አርጎ ከሰራን ያንንም ይዘን ነው የተፈጠርነው ማለት ነው ነገር ግን የተሰጠንን ስጦታ በጥቅም ስለለወጥነው እውነተኛ ፍቅር ዘወትር ስንራብና ስንጠማ እንኖራለን ማለት ነው።  በዚህም ምክንያት ተወለደን አድገን ገልምሰን አርጅተን እስክንሞት ድረስ በጥቅም ፍቅር ሕይወታችን ያልፋል ማለት ነው።  እንዲሂሁም ከሞትን በኋላ ዓለም የሚያስታውሰን ስለማንነታችን ነው ያ ማንነታችን ደሞ በህየወት እያለን የነበረው ማንነታችን ነው። በሱም በአንድ ወቅተ በቀጥተኛም ሆነ በተዘዋዋሪ መንገድ እነዛን ሰዎች ጠቅመናቸው ነበር ማለት ነወ።

ይቆየን King Nafkote2/16/11

No comments:

Post a Comment