Sunday, February 6, 2011

በምግብ መርከስ አለ?

ለክርስቲያኖች እንድንበላ የተፈቀደልን ምን አይነት ምግብ ነው? 
የፈለግነውን መብላት አለመብላት ያረክሳል ወይ (ሃጥያት ነው ወይ?)

2 comments:

  1. Thank You for posting this article Nafkotiye..As Kids,We are taught what to eat and what not to..Chances are,our grand parents learned from their ancestors and some are myths some are bahel and in the middle of it,we inherit what's far from truth..
    OK,what's Kosher,Hallal or what have you?As Christians are we to eat Hallal meat or shun from it?if we explore what's consider "Hallal" my understanding is the Animal is Slaughtered in the name of Mohamed or Allah..Keep the education going ye Negus lij again,thank you for the post..

    ReplyDelete
  2. የተዋህዶ ፋና

    በእረግጥ ጥሩ ጥያቄ ነው የጠየቅሽው። ብዙዎቻችን ሃይማኖታችንን በእምነት ደረጃ ሳይሆነ በባህል ደረጃ ነው ስናየው የኖርነው። ነገር ግን ሃይማኖትና ባህል በጣም የተለያዩ ነገሮች ናቸው። በእርግጥ ሁለቱም መከበር ያለባቸው ይመስለኛል ግን ሃይማኖትን ማክበር ግዴታችን ነው ባህልን ማክበር መብታችን ነው። እኔ እንደዚህ ነው የማየው። ብዙ ጊዜ ቤተሰቦቻቸን ባህልና ሃይማኖት አቀላቅለው ስለኖሩም ይመስለኛል እንደዚህ አለማው በክርስቲያኖች መካከል የበዛው። በእርግጥ ወንጌል በደንብ ስላልተሰበከላቸው ምንም ማድረግ አይቻልም በኦሪት የሚበሉ የማይበሉ የሚነኩ የማይነኩ የሚያረክሱ የሚቀድሱ እየተባሉ የእርግማኑን ዘመን ህግ አበክረው ስለተማሩት አልፈርድባቸውም ነገር ግን እኛ ከርስቲያኖች ከርስቲያን የተባልነው በክርስቶስ እንደመሆኑ መጠን ከርስቶስ ወደ ምድር መቶ ከዘላለማው ሞት ወደ ዘላለማዊ ሒወት እንዳሻገረን የደሙን ፍጹም አዳኝነት የመስቀሉን ስራ በአጠቃላይ ከመርገሙ ዘመን እንላቀቅበት ዘንድ አምላካችን በአንድ ልጁ የከፈለውን ያከናወነውን ካላመንን በእውነት እኛ እራሳችን ከሃዲ ወይም መናፍቃን ነን ማለት ነው።

    ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ባፈሰሰው ንጹህ ደሙ በጸጋ አለምን ሀሉ ስለጠራ ምድር ተባርካለች በውስጧም ያሉት ሀሉ ተቀድሰዋል የረከሳ የተረገመ የሚባል አንድም ነገር የለም። ከእንግዲህ ወዲህ ወደ አፍ የሚገባው ሳይሆን ሰውን የሚያረክሰው ከአፍ የሚወጣው ነው። ድነት በመብላት ባለመብላት ቢሆን ኖሮ ፍጹም የጌታ ደም በከንቱ ባለፈሰሰ ነበር። ስለዚህ ወደጥያቄሽ ልመለስና ሁሉን እንድንበላ ተፈቅዶልናል ግን ሁሉም አይጠቅመንም እኛ ኢትዮጵያውያን በባህልና በተለያዩ መንገዶች የማንበላቸው ከምንበላቸው ይበልጣሉ ግን በሃይማኖተ ምክንያት አይደለም በባህል እንጂ። ግን ማንም ሰው የሚመገበውን ነገር በጌታ ስም ወይም በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስመ ባርኮ ቢበላው ፍጹም ቅዱስ ነው። እንዳልሺው ሃላል ወይም ኮሸር ስጋ በሌላ እምነት ተባርኮ ስለመጣ እርኩስ ነው ብለን አንጥለውም እንደዛ ካልን ከሃጥያት ሀሉ በላይ ሃጥያት ጌታ የሰጠንን እርኩስ ብሎ መጥራት ነው እሱ ያከበረውን እኛ ማርከሳችን እርግማን ነው። እንደውም በስሙ የምናምንና የደናን ግን በታላቁ አባታቸን ስም ባርከን እንበላዋለን። ክርስቲያኖችን እንኳን የሚበላ ነገር ሊያረክሰን መርዝ እንኳን ቢሰጡን አምነን ባርከን ብንበላው ምንም አንሆንም ቃሉ ለሚያምን ሀሉ ይቻለዋል ነውና።

    ይልቁንስ እኛ በዚህ ዘመን ወንጌል እንደ ውሃ በሚፈስበት ዘመን ንግግራችንና ትምህርታችን ስለሚያረክስና ስለማያረክስ ስለሚበላና ስለማይበላ ሊሆን አይገባም ነበር ሰባኪያን ነን የሚሉት ተምረናል የሚሉት በስነ ስርዓት ለመንጋው ውንጌሉን ቢሰብኩለት ኖሮ እንዲህ አይነት አስተሳሰብ ከኛ ይርቅ ነበር። ነገር ግን አንዳንድ የሃይማኖቷን ቀሚስ ያጠለቁ መስለቀል የተሸከሙ አውቀናል ተምረናል የሚሉ ግን የተማሩት ያልገባቸው ወይም ያልተማሩ ጌታ አለመን በደሙ ካዳነ በኋላ ወደ ቀደመው የመርገም ሂወት የጌታን መንጋ ለመመለስ ዲያቢሎስ እነሱን እየተጠቀመ የጌታን ደም ሲያረክስ የመስቀሉን ፍቅር ሲያጣጥል እናየዋለን ልክ ያን ግዜ ጳውሎስን ሃሰተኛ ነብያቶች ከአባታቸው ከዲያቢሎስ እየተላኩ በሃሰት የክህደት ትምህርት ያስቸግሩት እንደነበረው ዛሬም ለቤተ ክርስቲኗ ተቆርቋሪ ተከራካሪ እየመሰሉ የቅድስቲቷን ቤተ ክርሰቲያን ልጆች በኑፋቄ መርዝ የሃሰት ስብከታቸው ይበክሉታል። ማንም ሆነ ማንም በመብላት፤ በመንካት፤ ልማድ በመጠበቅ ፤የረከሳ ፤የልረከሰ በማለት አይድንም።

    ትምህርታችን ወንጌላችን እንዲህ ይላል “ምድርኒ ትገብር ፋሲካ ተሃጺባ በደመ ክርስቶስ” ምድር ደስታን ታድርግ በክርስቶስ ደም ታጥባለች እና። ስለዚህ ደሙ ቀድሶናል ስሊዘህ ብላ አትብላ ንካ አትነካ ረክሳሃል አልረከስክም ተፈቅዷል አልተፈቀደም እያሉ የከርስቶስን ተከታዮች ከሚያወናብዱ የክህደት ትምህርቶችና ከሃዲ(መናፈቅ አስተማሪዎች መንጋው እራሱን ይጠብቅ) ስንት ሊቃውንት የፈሉባት ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያናችን ልዩ ልዩ ትምህርቶችን በልጆቿ አዘጋጅታልናለች። ለምሳሌ ወንጌል በዖሪት ላይ በሚለው ትምሀርት አባ ወ/ትንሣዔ አያልነህ ህይወት የሆነ ትምሀርት ለትውልድ የሚተርፍ ማንም ሃይማኖተኛ ነኝ የሚል ሀሉ ቀና ብሎ እንዳያያን አርገው አስተምረውናል ስለዚህ የተዋህዶ አምላክ እውነተኛ አባቶችን ይጠብቀልን።

    እንዲሁ ብዙ ሊቃውንት አሮጌውን ኪዳን ከአዲሱ ኪዳን ጋር አጣጥመው አስተምረውናል። አሁንም እያስተማሩ ይገኛሉ የሚሰማ ጆሮ የሚቀበል ህሊና የሚያከብር ልብ ካለ። በመብላት ባለመብላት መርከስ የለም የተፈቀደ ያለተፈቀደ የሚባል የለም ፋና ማንም ሰው የፈለገውን የፈቀደውን መብላት መብቱ ነው በእግዚአብሔር ስም ባርኮ እስከተመገበው ድረስ። “የፈለገንውን እንድንበላ ተፈቅዶልናል ግን ሀሉም አይጠቅመንም” በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም ባርከን እንብላ/እንመገብ?

    ይቆየን ናፍቆት ገበየሁ

    ReplyDelete