Thursday, January 27, 2011

እግዚአብሔር መቼ ነው የሚወደን መቼ ነው የሚጠላን? ናፈቆት ገበየሁ

ጌታ ሁሌም ይወደናል ጠልቶንም አያውቅም

በመጀመሪያ እግዚአብሔር መቼም ቢሆን አይጠላንም በተለይ በልጁ ደም ካጠበን ጀምሮ ለኛ ያለውን ፍቅር በግልጽ አሳይቶናል። ነገር ግን ብዙዎቻችን ጌታን እንደ ገዳይ እንደ ክፉ እንደ አረመኔ በማየት አገልግሎታችን ወይም ህይወታችን በፍርሃት የተለወሰ አምልኮ ነው የምናመልከው ነገር ግን የምናመልከው ጌታ ኢየሱስ ክረስቶስ እንዲሁ የወደደን ከባርነት ወደ ልጅነት ያሸጋገረን የለመንነውና የጠየቅነውን እንደሚያስፈልገን አድርጎ የሚሰጠን ስለወደድነው የማይወደን ወይም ስለጠላነው ያማይጠላን ልዩ ፍቅር ጌታ ነው።

ስለዚህ የምታመለኩትን አምላክ ለሌሎች ስበኩ የፍቅር ጌታ የሰላም ንጉስ ከምንም በላይ ልጆቹን የሚወድ ጌታ እንደሆነ ተናገሩ ድንቅ ስራውን መስክሩ እውነትን መስክሩ።  እግዚአብሔር ታላቅ ነው ሰው እስከ ሞት ሊወደን ይችላል እሱ ግን ፍቅሩ ከመቃብር ያልፋል ስለዚህ ምን ግዜም ከኛ የማይለየውን ንጹህ ውድ ፍቅር የሆነ አባት ለአለም ስበኩ ስለስሙ አትፈሩ የማያምኑትን በፍቅር አሳምኗቸው ያመናችሁ የሚመስላችሁም እምነታችሁን መርምራችሁ ጠንቅቃችሁ ተረዱ እምነትና ስርዓትን ለዩ ባህልንና ሃይማኖትን አንቀላቅል እውነተኛ የጌታ ልጆች እንሁን እርስ በዕርሳችን እንፋቀር ጌታ ከኛ የሚፈልገው እሱን ነውነና።

እሱ ሁሌም ይወደናል እኛ ግን ፍቅራችን ከጥቅም ጋር የተዛመደ ስለሆነ የምንፈልገው ነገር ሲሆን እናመሰግነዋልን ያላሰብነው ነገር ሲሆን ግን ስሙን መጥራት የስጠላናል እባካችሁ ፍቅራችን በጥቅም የተሸፈነ አይሁን ጌታ እንዲሁ ስለወደደን እነዲሁ እንውደደው መውደዳችንን ደሞ በስራ እንግለጸው ያን ግዜ የጌታ ልጆች እንባላለን።
ይቆየን

No comments:

Post a Comment