የገላትያ መልእክት ም 1፡1-10 (ክፍል ፩)
በመጀመሪያ የሚከተለውን ሙሉ ንባብ ያንቡ።
1-2 በኢየሱስ ክርስቶስ ከሙታንም ባነሣው በእግዚአብሔር አብ ሐዋርያ የሆነ እንጂ ከሰዎች ወይም በሰው ያልሆነ ጳውሎስ ከእኔም ጋር ያሉት ወንድሞች
ሁሉ፥ ወደ ገላትያ አብያተ ክርስቲያናት፤
3 ከእግዚአብሔር ከአባታችን ከጌታችንም ከኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋና ሰላም ለእናንተ ይሁን።
4 ክፉ ከሆነ ከአሁኑ ዓለም ያድነን ዘንድ እንደ አምላካችንና እንደደ አባታችን ፈቃድ ስለ ኃጢአታችን ራሱን ሰጠ።
5 ለአብ ከዘላለም እስከ ዘላለም ክብር ይሁን፤ አሜን።
6 በክርስቶስ ጸጋ እናንተን ከጠራችሁ ከእርሱ ወደ ልዩ ወንጌል እንዲህ ፈጥናችሁ እንዴት እንዳለፋችሁ እደነቃለሁ፤
7 እርሱ ግን ሌላ ወንጌል አይደለም፤ የሚያናውጡአችሁ የክርስቶስንም ወንጌል ሊያጣምሙ የሚወዱ አንዳንዶች አሉ እንጂ።
8 ነገር ግን እኛ ብንሆን ወይም ከሰማይ መልአክ፥ ከሰበክንላችሁ ወንጌል የሚለይ ወንጌልን ቢሰብክላችሁ፥ የተረገመ ይሁን።
9 አስቀድመን እንዳልን እንዲሁ አሁን ሁለተኛ እላለሁ፥ ከተቀበላችሁት የተለየውን ማንም ቢሰብክላችሁ የተረገመ ይሁን።
10 ሰውን ወይስ እግዚአብሔርን አሁን እሺ አሰኛለሁን? ወይም ሰውን ደስ ላሰኝ እፈልጋለሁን? አሁን ሰውን ደስ ባሰኝ የክርስቶስ ባሪያ ባልሆንሁም።
በክርስቶስ ኢየሱስ ከሙታንም ባስነሣው በእግዚአብሔር አብ ሐዋርያ የሆነ እንጂ ከሰዎች ወይም በሰው ያልሆነ (ቁ. 1-2)
ሐሰተኛ አስተማሪዎች ጳውሎስን ሐዋርያ አይደለም ኢየሱስንም አላየም የሚል ወሬ በገላትያ ቤ/ክር/ ሳይበትኑ አልቀረም። እንዲህ እያሉ የሚያስወሩትም
መጀመሪያ ጳውሎስ ለገላትያ ክርስቲያኖች ያስተማረውን ትክክለኛ ትምህርት እንዲጠራጠሩ ለማድረግ እና ወደ ራሳቸው ስሕተት ለመሳብ ነው። ከጌታ ጋር
አብረው የዋሉ እና ያደሩ ሐዋርያት እንደ ጳውሎስ አያስተምሩም የጳውሎስ ትምህርት ግን ከነርሱ የተለየ ነው የሚል ወሬ ይነዙ እንደነበር የጽሑፉ ይዘት
ይመሰክራል። በዚህ ምክንያት ጳውሎስ ሐዋርያት የሚሰብኩትን ወንጌል እርሱ ከሚስብከው ወንጌል ጋር ለማመሳከር ወደ ኢየሩሳሌም ወጥቶ ነበር።
ለዚህም እንዲህ ያላል።
ገላ 2፡1-6
ከዚያ ወዲያ ከአሥራ አራት ዓመት በኋላ ከበርናባስ ጋር ቲቶን ደግሞ ይዤ ወደ ኢየሩሳሌም ሁለተኛ ወጣሁ፤
እንደ ተገለጠልኝም ወጣሁ፤ ምናልባትም በከንቱ እንዳልሮጥ ወይም በከንቱ ሮጬ እንዳልሆን በአሕዛብ መካከል የምሰብከውን ወንጌል አስታወቅኋቸው፤
ዋኖች ግን መስለው ለሚታዩ ለብቻቸው አስታወቅኋቸው።
ነገር ግን ከእኔ ጋር የነበረ ቲቶ እንኳ የግሪክ ሰው ሲሆን ይገረዝ ዘንድ ግድ አላሉትም፤
ነገር ግን ባሪያዎች ሊያደርጉን በክርስቶስ ኢየሱስ ያለንን አርነታችንን ይሰልሉ ዘንድ ሾልከው በስውር ስለ ገቡ ስለ ሐሰተኞች ወንድሞች ነበረ።
የወንጌልም እውነት በእናንተ ዘንድ ጸንቶ እንዲኖር ለአንድ ሰዓት እንኳ ለቅቀን አልተገዛንላቸውም።
አለቆች የመሰሉት ግን፥ በፊት ማን እንደ ነበሩ አይገደኝም፤ እግዚአብሔር የሰውን ፊት አይቶ አያደላም፤ አለቆች የመሰሉት አንዳች እንኳ
አልጨመሩልኝምና፥
በአሕዛብ መካከል የምሰብከውን ወንጌል አስታወቅኋቸው የሚለው ቃል ክሱን ለማስተባበል ያደረገውን ትግል ያሳያል። ሐዋርያትም በጳውሎስ ትምሕርት
እና በነርሱ ትምህርት መካከል ምንም ልዩነት እንደሌለ በማረጋገጥ ለበርናባስና ለጳውሎስ ቀኝ እጃቸውን ሰጠዋል።ቁ 9
ስለዚህ የሐሰተኛ አስተማሪዎች ወሬ መሠረት የሌለው ነው። ጳውሎስ ሐዋርያነቱን ለማረጋገጥ በኢየሱስ ክርስቶስ እና በአብ የተመረጠ ምሆኑን አበክሮ
ይናገራል። ከሰዎች ወይም በሰው አልተመረጥሁም ይላል። ጳውሎስ እንዴት ሐዋርያ እንደሆነ በሐዋርያት ሥራ ም 9 ማንበብ ይችላል። ጳውሎስ ስሙ ገና
ሳውል ሳለ
- ፈሪሳዊ ምሑረ ኦሪት ነበር
- ለአባቶቹ ወግ ከመጠን ይልቅ ቀናተኛ ነበር ገላ 1፡14
- የአይሁድን ሥርዓት በመፈጸም ማንም አይወዳደረውም ነበር
- ሕግን በመጠበቅ በኩል ነቀፋ አልነበረበትም ፊልጵ 3፡6
- ቤተ ክርስቲያንን ያለ ልክ የሚያሳድድ የክርስቶስ ተቃዋሚ ነበር
- እስጢፋኖስ ሲገደል ዋና ተባባሪ ነበር። የሐዋ 7፡60።
አንድ ቀን በደማስቆ ክርስቲያኖች እንደበዙ ሲሰማ እንርሱን አሥሮ ወደ ኢየሩሳሌም ለማምጣት ከሊቀ ካህናቱ ባገኘው ሥልጣን ተማምኖ ሲሄድ ኢየሱስ
ክርስቶስ ተገለጠለት። ጳውሎስ በታላቅ መደነቅ የክርስቶስን ጌትነት እና አዳኝነት ተቀበለ እንዲያውም ምን ላደርግልህ ትወዳለህ? ሲል ለመታዘዝ ተዘጋጀ።
ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስለ ጳውሎስ ሲናገር ይህ በአሕዛብም በነገሥታትም በእሥራኤልም ልጆች ፊት ስሜን የሚሸከም ለእኔ የተመረጠ እቃ ነው። ይላል
የሐዋ 9፡15። ጳውሎስ በእርግጥም የጌታን ስም የተሸከመ ምርጥ እቃ ነው ሕይወቱ በሙሉ ወንጌል ነው በመልእክቶቹ የእግዚአብሔርን ምሥጢር
አብራራቶልናል።
በሐዋ 26፡15-18 ላይ
እኔም። ጌታ ሆይ፥ ማንነህ? አልሁ። እርሱም አለኝ። አንተ የምታሳድደኝ እኔ ኢየሱስ ነኝ።
ነገር ግን ተነሣና በእግርህ ቁም፤ ስለዚህ እኔን ባየህበት ነገር ለአንተም በምታይበት ነገር አገልጋይና ምስክር ትሆን ዘንድ ልሾምህ ታይቼልሃለሁና።
የኃጢአትንም ስርየት በእኔም በማመን በተቀደሱት መካከል ርስትን ያገኙ ዘንድ፥ ከጨለማ ወደ ብርሃን ከሰይጣንም ሥልጣን ወደ እግዚአብሔር ዘወር
እንዲሉ ዓይናቸውን ትከፍት ዘንድ፥ ከሕዝቡና ወደ እነርሱ ከምልክህ ከአሕዛብ አድንሃለሁ።
ይላል። በዚህ መሠረት ሐዋርያው ጳውሎስ ቀጥታ በየሱስ ክርስቶስ የተሾመ ሐዋርያ ነው። የሐሰተኛ አስተማሪዎች ክስም ዋጋ የሌለው ይሆናል።
ከእግዚአብሔር ከአባታችን ከጌታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ እና ሰላም ለእናንተ ይሁን (ቁ. 3) ( ... ይቀጥላል)
No comments:
Post a Comment