Thursday, January 27, 2011

KING (ነጻነት ክፍል2 መምህር ተከስተ ጫኔ)

ነጻነት(ካለፈው የቀጠለ)
ከኃጢአት ነጻ መውጣት
ኃጢእት ምንድን ነው?
የኃጢአትን ምንነት ለማወቅ ከኃጢአት ነጻ ለመውጣት የምናደርገውን ፍላጎት ይጨምርናል ። ስለ ኃጢአት ካላወቅን
የእግዚአብሔርን ጸጋ ፍቅሩን ፤ ድኅነትን ፤ የወንጌልን መልእክት ሁሉ መረዳት አንችልም።
ኃጢአት ስሕተት ፤ ኢላማን መሳት ፤ ድንበርን መተላለፍ ፤ ፍትሕን ወይም ጽድቅን መጣስ ፤ ግፍ ፤ ብልሽት የሚሉትን
ትርጉሞች ይሰጣል።
በጎ ለማድረግ አውቆ የማይሰራውም ኃጢአት ነው። ያዕ 4፡17። እንደተባለው ፤ ኃጢአት የሚገባንን አለመፈጸምም
እንደሆነ እንረዳለን። በዚህ መሠረት ኃጢአት በያንዳዱ ሰው የሚገኝ ርኩሰት ነው።
የሰው ልብ በእግዚአብሔር ዓይን ሲታይ እጅግ ክፉ ነው።
እግዚአብሔርም የሰው ክፋት በምድር ላይ እንደ በዛ ፤ የልቡ ሐሳብ ምኞትም ሁልጊዜ ፈጽሞ ክፉ እንደሆነ አየ ይላል ዘፍ 6፡
5።
የሰው ልብ ከሁሉ ይልቅ ተንኮለኛ እጅግም ክፉ ነው ማንስ ያውቀዋል?ይላል ኤር 17፡9።
እንዲሁም ሁሉም ኃጢአትን ሠርተዋልና የግዚአብሔር ክብር ጎድሏቸዋል
ተብሎ ተጽፎአል። ሮሜ 3፡23።
ከሁሉም የከፋው ኃጢአት ግን በኢየሱስ ክርስቶስ አለማመን ነው።
እርሱም መጥቶ ስለ ኃጢአት ስለጽድቅም ስለፍርድም ዓለምን ይወቅሳል፤ ስለኃጢአት በእኔ ስለማያምኑ ነው ፤ ስለጽድቅም
ወደ አብ ስለምሄድ ነው ፤ ስለፍርድም የዚህ ዓለም ግዢ ስለተፈረደበት ነው። ይላል ዮሐ 16፡8-9። ምክንያቱም ኃጢአተኞች
በኢየሱስ ክርስቶስ ቢያምኑ ይድናሉ ፤ ነገር ግን ኃጢአተኞች ሆነው ሣለ ሊያድናቸው በሚችለው በክርስቶስ አለማመናቸው
ደግሞ እጥፍ ኃጢአት ነው።
የኃጢአት ውጤት
1 ኃጢአት በእግዚአብሔርና በሰው መካከል ያለውን ግንኙነት ያበላሻል።
በመጀመሪያ በሰውና በእግዚአብሔር መካከል ያለውን መለካም ግንኙነት ያበላሸው ኃጢአት ነበር ዘፍ 3፡8። ሰው በኃጢአት
እየኖረ ከእግዚአብሔር ጋር መኖር አይችልም። የእግዚአብሔርን ክብርና ሞገስም አያገኝም። ሰላም ፤ ደስታ እና እርካታም
ሁሉ ይርቁታል።
2 ኃጢአት በሰውና በሰው መካከል ያለውን ግንኙነትም ያበላሻል ዘፍ 2፡25።
ሰዎች በኃጢአት የሚኖሩ ከሆነ እርስ በርሳቸው መተማመን አይችሉም ፤ ፍቅር ፤ መተሳሰብ ፤ አይኖራቸውም ፤ ንሥሐ
በሌለው ሕይወት እራስ ወዳድነት ጎልቶ ይታያል። እርስ በእርስ መካሰስ የሚመጣውም በኃጢአት ምክንያት ነው ዘፍ 3፡13።
3 ኃጢአት የእግዚአብሔርን ፍርድ ያስከትላል።
እግዚአብሔር በባሕርዩ ቅዱስ ስለሆነ በኃጢአት ላይ መፍረድ አለበት። በዚህ ምክንያት በኃጢአተኛው ፈንታ
የእግዚአብሔርን ፍርድ የሚሸከም ምትክ ካልተገኘ ኃጢተኛው ፍርዱን ይሸከማል። ዘፍ 3፡14-19 6፡13።
4 ኃጢአት የዘለዓለም ጥፋት አለበት
የኃጢአት ደሞዝ ሞት ነው እንደተባለ ሮሜ 6፡23። በኃጢአታችን ተናዘን ንስሐ ባንገባ ግን የዘለዓለም ሞት ይጠብቀናል ዳሩ
ግን የሚፈሩ እና የማያምኑ የርኩሳንም የነፍሰ ገዳዮችም የሴሰኛዎችም የአስማተኞችም ሁሉ ዕዳላቸው በዲን እና በእሳት
በሚቃጠልም ባሕር ነው ይኸውም ሁለተኛው ሞት ነው ራእ 21፡8።
ታዲያ ከኃጢአትና ከዘላለም ጥፋት ማን ያድነን ይሆን? . . . . . . ይቀጥላል

No comments:

Post a Comment