ነጻነት (ካለፈው የቀጠለ ቁ፫)
ኃጢአተኛ በእግዚአብሔር ፊት ሲታይ
የሰው ሁለንተና በኃጢአት የተበከለ ነው። ይህ ማለት አእምሮው ፤ ስሜቱ እና ፈቃዱ ተበከለዋል ማለት ነው። ሰው በሰው
ፊት ሲታይ መልካም የሠራ ፤ ጻድቅ እንከን የለሽ ይመስላል። ሰውን ጻድቅ እና ኃጥእ ፤ በጣም የጸደቀ በጣም የተኮነነ
እያልን በሁለት ጎራ ልንመድብ እንችላለን። ነገር ግን ሰው ፊትን ያያል እግዚአብሔር ግን ልብን ያያል 1ሳሙ16፡7 ተብሎ
እንደተጻፈ የእኛ አመዳደብ ፍጹም የተሳሳተ ነው።
መጽሐፍ ቅዱስ የእኛን አመዳደብ በመሰረዝ አንድም ጻድቅ የለም በማለት ይደመድማል ሮሜ 3፡11። ሰው በመልካምነቱ
ጻድቅ ቢባልም ኃጢአት የሌለበት ነው ማለት ግን አይደለም። ለዚህ ነው ጻድቃን ራሳቸው ጽድቃችን የመርገም ጨርቅ
ነው። እንሆ በአመፃ ተጸነሥሁ እናቴም በኃጢአት ወለደችኝ ያሉት ኢሳ 64፡6 መዝ 51፡5።
ኃጢአተኛ በእግዚአብሔር ፊት የሚከተሉትን ይመስላል።
ኃጢአተኛ የተኮነነ ነው። “ኃጢአትን የምትሠራ ነፍስ እርሷ ትሞታለች” ሕዝ 18፡20። ልብ አናድርግ ነፍስን የሚገድላት
ኃጢአት እንጂ እግዚአብሔር አይደለም። እግዚአብሔር ከኃጢአት ለማዳን ቆሞ ይጠብቃል።
ኃጢአተኛ በቍጣ ሥር የሚገኝ ጠላት ነው። አመንዝሮች ሆይ ዓለምን መውደድ ለእግዚአብሔር ጥል እንዲሆን
አታውቁምን? የዓለም ወዳጅ ሊሆን የሚወድ ሁሉ የእግዚአብሔር ጠላት ሆኗል። ጠላት ማለት በተቃርኖ የቆመ ማለት
ስለሆነ ኃጢተኛም ከእግዚአብሔር ፈቃድ ውጭ የሆነ አቋም ያለው ማለት ነው። ጳውሎስ በሮሜ 5፡9-10 ላይ በክርስቶስ
ሞት ከእግዚአብሔር ጋር የታረቁ ጠላቶች ከእግዚአብሔር ቁጣ የመዳን ዋስትና እንዳላቸው ይናገራል።
የተበከለ ወይም የተበላሸ ነው። ምድርም በእግዚአብሔር ፊት ተበላሸች ምድርም ግፍን ተሞላች። እግዚአብሔርም
ምድርን አየ እነሆም ተበላሸች ሥጋን የለበሰ ሁሉ በምድር ላይ መንገዱን አበላሽቶ ነበርና ዘፍ 6፡11። ይላል።
ኃጢአተኝነት ማለት አደገኛ ብልሽት ማለት ነው።
በሕግ በኩል ሲታይ ደካማ ነው። የእግዚአብሔር ሕግ በሰው ውድቀት አልተለወጠም። ዛሬም የእግዚአብሔር ፈቃድ ሕጉን
ሰው በሙሉ እንዲታዘዘው ነው። ነገር ግን ሰው ከተበከለ ማንነቱ የተነሣ ሕጉን መታዘዝ አይችልም። በሥጋ የሚኖሩትም
እግዚአብሔርን ማስደሰት አይችሉም ተብሎ ተጽፏል ሮሜእ 8፡7። ሕግ ኃጢተኛ መሆናችንን ይነግረናል እንጂ
ከኃጢአታችን አያድነንም። እግዚአብሔር በሰጠው ሕግ በኩል ሲመለከተን ከሕግ በታች ወይም ከፍርድ በታች
እንገኛለን። አፍም ሁሉ ይዘጋ ዘንድ ዓለምም ሁሉ ከእግዚአብሔር ፍርድ በታች ይሆን ዘንድ ሕግ የሚናገረው ሁሉ ከሕግ
በታች ላሉት እንዲናገር እናውቃለን ይህም የሕግን ሥራ በመሥራት ሥጋ የለበሰ ሁሉ በእርሱ ፊት ስለማይጸድቅ ነው።
ኃጢአት በሕግ ይታወቃልና ይላል ሮሜ 3፡19-20።
ኃጢተኛ በእግዚአብሔር ዘንድ የሞተ ነው። በቅዱስ መጽሐፍ ውስጥ ሕይወት ማለት ከእግዚአብሔር ጋር በሕብረት መኖር
የእግዚአብሔርን ሕይወት መካፈል ማለት ሲሆን ሞት ማለት ደግሞ ከዚህ ሕብረት መለየት ወይም የእግዚአብሔርን
ሕይወት ማጣት ማለት ነው። ቅ/ጳውሎስ በበደላችሁና በኃጢታችሁ ሙታን ነበራችሁ ይላል ኤፌ 2፡1።
ታዲያ የኃጢተኞች መጨረሻ ምን ይሆን? የኃጢአተኞች መጨረሻ ወደ ገሃነም መጣል ነው ሉቃ 12፡5። ይህ እውነት
ላይመስልዎት ይችላል ነገሩ እውነት ነው። ሰው በሥጋ ከንፍሱ ከተለየ በኋላ ወደ መቃብር መውረዱ እውነት እንደሆነ ሁሉ
በሕይወቱ የሞተ ሰውም ወደ ገሃነም መውረዱ የማይቀር ነው። መጽሐፍ ቅዱስ አትሳቱ እግዚአብሔር አይዘበትበትም ሰው
የሚዘራውን ያንኑ ደግሞ ያጭዳልና በገዛ ሥጋው የሚዘራ ከሥጋ መበስበስን ያጭዳልና በመንፈስ ግን የሚዘራ ከመንፈስ
የዘለዓለም ሕይወትን ያጭዳል ይላል ገላ 6፡7።
ከኃጢአት እና ከዘለዓለም ፍርድ ነጻ መውጣት ትፈልጋለ/ሽ/ ??
ኃጢአተኛ ነህ ፤ ኃጢአተኛ መሆንህን እወቅ ኩነኔ የለም በሚል የተሳሳተ ግምት ራስህን አታታልል፤ የኃጢአት ሸክምህ
በእንዲህ አይነቱ ግምት አይቀልልህምም፤ ተጠንቀቅ፤
ከዘለዓለሙ የኃጢአት ፍርድ ማን ነጻ ያወጣኛል. . .? ? ? ይቀጣላል..
No comments:
Post a Comment