የገላትያ መልእክት ትርጉም
ገላትያ ማን ናት ?
ገላትያ የጥንት የሮማ ግዛት የክፍለ ሀገር ከተማ ነበረች አሁን የቱርክ ግዛት ሳትሆን አትቀርም። የደቡብ እስያ ሀገራት በሙሉ ገላትያ ይባሉ
ነበር። ለምሳሌ ጲስድያ ፤ አንጾኪያ ፤ ኢቆኒዮን ፤ ልስጥራን እና ደርቤን በገላትያ አውራጃ የሚገኙ ህገሮች ናቸው። ሐዋርያው ጳውሎስ
ለመጀመርያ ጊዜ ተጉዞ ወንጌልን የሰበከው በነዚህ አካባቢ እንደነበረ ይተረካል።
የሐዋ 16፡6 በእስያም ቃሉን እንዳይናገሩ መንፈስ ቅዱስ ስለከለከላቸው በፍርግያና በገላትያ አገር አለፉ የሚለው ቃል ገላትያ ከእስያ እና
ከቱርክ መካከል መሆኗን የሚጠቁም ነው።
ሐዋርያው ጳውሎስ በሦስተኛ ጉዞው ገላትያን እንደጎበኘ የሐዋ ሥራ ሲናገር፤- ወደ ቂሣርያም በደረሰ ጊዜ ወጥቶ ለቤተ ክርስቲያን ሰላምታ
ከሰጠ በኋላ ወደ አንጾኪያ ወረደ ጥቂት ቀንም ቆይቶ ወጣ ደቀ መዛሙርትንም ሁሉ እያጸና በገላትያ አገርና በፍርግያ በተራ አለፈ ይላል የሐዋ
18፡23።
ከገላትያ ጋር አብረው የተጠቀሱት ሀገራት ሁሉ ጳውሎስ በርናባስን አስከትሎ ለመጀመሪያ ጊዜ ወንጌልን የሰበከባቸው እና አብያተ
ክርስቲያናትን የተከለባቸው ሀገራት ናቸው።የሐዋ 13፡13-14። መልክቱ የተጻፈውም ከ49-60 ዓ.ም ባሉት አመታት እንደሆነ ይገመታል።
መልእክቱ የተጻፈበት ምክንያት
ሐሰተኛ አስተማሪዎች የገላትያን ቤተ ክርስቲያን በሐሰተኛ ወይም የይሁዲነት ወግ እና ልማድ ትምህርታቸው አናውጠዋት ስለነበር የገላትያ
ክርስቲያኖችን ወደ መጀመሪያ እምነታቸው ለመመለስ እና ሐሰተኞ አስተማሪዎችንም ለመቃወም ነበር። ጳውሎስ የሙሴን ሕግ እናስተምራለን
እያሉ የሚበጠብጡትን በሚከተሉት ቃላት ነው የሚጠራቸው፤-
- ሐሰተኛ ወንድሞች ገላ 2፡4
- ውሾች
- ክፉዎች ሠራተኞች ፊልጵ 3፡2። ይላቸዋል
ክርስቶስን ተቀበለው ክርስቲያን የሆኑ አይሁዶች የሙሴን ሕግ ካልፈጸማችሁ በክርስቶስ ብቻ አትድኑም እያሉ የገላትያን ምእመናንን
አውከው እንዲገረዙም አስገድደዋቸው ነበር። ነገር ግን እራሳቸው የግዝረት ሰባኪዎች ሕግን አይጠብቁም ነበር። በሥጋችሁ እንዲመኩ
ልትገረዙ ይወዳሉ እንጂ የተገረዙቱ ራሳቸው እንኳ ሕግን አይጠብቁም ሲል ጳውሎስ አጋልጧቸዋል።ገላ 6፡13።
ዋናው የሐሰተኞች ትምህርት
- እንደ ሙሴ ሥርዓት መገረዝ አለባችሁ
- የሙሴን ሕግም መጠበቅ አለባችሁ የሚል ነው።
የገላትያ ክርስቲያኖች ግን በክርስቶስ ጸጋ የተጠሩ ከጣኦት ከርኩሰት ከተለያዩ የአጋንንት እሥራቶች በወንጌል ብርሃን ነጻ የወጡ እንጂ
ስለሙሴ ሕግ የሚያውቁት ነገር አልነበረም። በኋላ ግን ከአይሁድ ክርስቲያኖች በተማሩት የስሕተት ትምህርት ምክንያት የክርስቶስን ጸጋ
ጥለው ወደ ሙሴ ሕግ ዘወር ስላሉ የገላትያ መልእክት ተጻፈችላቸው። ጳውሎስን ያስደነቀውም የእግዚአብሔርን ጸጋ ጥለው ወደ ልዩ ወንጌል
ማለት ወደማያድነው የሙሴ ሕግ ፈጥነው ዘወር ማለታቸው ነበር። በክርስቶስ ጸጋ እናንተን ከጠራችሁ ከእርሱ ወደ ልዩ ወንጌል እንዲህ
ፈጥናችሁ እንዴት እንዳለፋችሁ እደነቃለሁ ይላል ገላ 1፡6።
ጳውሎስ በአንድ ወቅት እነዚህ የአይሁዳዊነት አስተማሪዎችን በመጀመሪያው የኢየሩሳሌሙ ጉባኤ በተደረገው ክርክር አሸንፏቸው ነበር የሐዋ
15፡1-29። በሐዋርያት ጉባኤ ሲሸነፉ ወደ ገላትያ ሾልከው በመግባት የስሕተት ትምህርታቸውን ቀጠሉ ለዚህ ነው በገላ 2፡5 በክርስቶስ ያለንን
አርነታችንን ይሰልሉ ዘንድ በስውር ሾልከው የገቡ ሲል የሚገልጣቸው።
በኢየሩሳሌሙ ጉባኤ የተደረገው ክርክርከና ውሳኔ የሚከተለው ነበር
ጳውሎስ እና በርናባስ ወንጌልን ለአሕዛብ ሰብከው ከተመለሱ በኋላ በአንጾኪያ ለነበሩ ደቀ መዛሙርት የአሕዛብን መዳን አወሩላቸው የሐዋ
14፡24-27። አንዳድ ከኢየሩሳሌም የመጡ ክርስቲያኖች ግን “እንደ ሙሴ ሥርዓት ካልተገረዛችሁ ትድኑ ዘንድ አትችሉም ብለው ወንድሞችን
ያስተምትሩ ነበር። በእነርሱ እና በጳውሎስ በበርናባስም መካከል ብዙ ጥልና ክርክር በሆነ ጊዜ ስለዚህ ክርክር ጳውሎስና በርናባስ ከእነርሱም
አንዳንዶች ሌሎች ሰዎች ወደ ሐዋርያት ወደ ቀሳውስትም ወደ ኢየሩሳሌም ይሄዱ ዘንድ ተወሰነ። የሐዋ 15፡1-2
ክርክሩ ቀላል አልነበረም የአሮጌው ኪዳን አስተማሪዎች ሐዲስ ኪዳንን በሙሉ ልባቸው ካልተቀበሉ የክርስቶስ ሙሉ አዳኝነት ይጋረድባቸዋል።
የክርስቶስ አዳኝነት ደግሞ ፍጹም የእግዚአብሔር ስጦታ እንጂ አይሁድ ወይም ኃጢአተኛ የሚባሉት አሕዛብ አንዳች የጨመሩት ነገር የለም።
በመዳን እና መንፈስ ቅዱስን በመቀበል በኩል በአይሁድም ሆነ በአሕዛብ መካከል ምንም ልዩነት አልተደረገም እግዚአብሔር ሁሉንም
በክርስቶስ ለመጠቅለል ስላሰበ ኤፌ 1፡10። የማዳን ሥራውን ያደረገው በራሱ ፍቅር እንጂ በማንም ሕግ ላይ ተመስርቶ አይደለም።
ሰለዚህ የአይሁድ ክርክር እግዚአብሔርን መፈታተን እንደሆነ በቅ/ ጴጥሮስ ተገልጾላቸዋል።
”ሐዋርያትና ቀሳውስትም ስለዚህ ነገር ለመመካከር ተሰበሰቡ ከብዙ ክርክርም በኋላ ጴጥሮስ ተነሥቶ እንዲህ አላቸው ወንድሞች ሆይ አሕዛብ
ከአፌ የወንጌልን ቃል ሰምተው ያምኑ ዘንድ እግዚአብሔር በመጀመሪያው ዘመን ከእናንተ እኔን እንደ ጠራኝ እናንተ ታውቃላችሁ ልብንም
የሚያውቅ አምላክ ለእኛ ደግሞ እንደሰጠን መንፈስ ቅዱስን በመስጠት መሠከረላቸው ልባቸውንም በእምነት ሲያነጻ በእኛ እና በነርሱ
መካከል አንዳች አለየም። እንግዲህ አባቶቻችን እና እኛ ልንሸከመው ያልቻልነውን ቀንበር በደቀ መዛሙርት ጫንቃ ላይ በመጫን
የሚያውቅ አምላክ ለእኛ ደግሞ እንደሰጠን መንፈስ ቅዱስን በመስጠት መሠከረላቸው ልባቸውንም በእምነት ሲያነጻ በእኛ እና በነርሱ
መካከል አንዳች አለየም። እንግዲህ አባቶቻችን እና እኛ ልንሸከመው ያልቻልነውን ቀንበር በደቀ መዛሙርት ጫንቃ ላይ በመጫን
እግዚአብሔርን አሁን ስለ ምን ትፈታተናላችሁ? ነገር ግን በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ እንደ እነርሱ ደግሞ እንድን ዘንድ እናምናለን” ቁ 6-11
የሚለውን ምሥክርነት ተናገሯል።
ያዕቆብም የሚከተለውን መሥክሯል “ ... ስለዚህ ከአሕዛብ ወደ እግዚአብሔር የዞሩትን እንዳናስቸግራቸው ነገር ግን ከጣዖት ርኩሰት እና
ከዝሙት ከታነቀም ከደምም ይርቁ ዘንድ እንድንጽፍላቸው እቆርጣለሁ” ቁ 19-20
ደብዳቤውም እንዲህ የሚል ነበር “ያላዘዝናቸው ሰዎች ከእኛ ወጥተው ትገረዙ ዘንድ እና ሕግን ትጠብቁ ዘንድ ይገባችኋል ብለው ልባችሁን
እያወኩ በቃል እንዳናወጧችሁ ስለ ሰማን ስለ ጌታችን ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ ስም ነፍሳቸውን ከሰጡት ከምንወዳቸው ከበርናባስና ከጳውሎስ
ጋር የተመረጡትን ሰዎች ወደ እናንተ እንልክ ዘንድ በአንድ ልብ ሆነን ፈቀድን ... ልጣዖት ከተሰዋ ከደምም ከታነቀም ከዝሙትም ትርቁ ዘንድ
ከዚህ ከሚያስፈልገው በቀር ሌላ ሸክም እንዳንጭንባችሁ እኛ እና መንፈስ ቅዱስ ፈቅደናልና ከዚህም ሁሉ ራሳችሁን ብትጠብቁ በመልካም
ትኖራላችሁ ጤና ይስጣችሁ” ቁ 23-29። ይህ የመጀምሪያው ጉባኤ ለቤተ ክርስቲያን ጉዞ እስከ አሁን ድረስ ትልቅ አስተዋጽኦ እያደርገ ነው።
መዳን በእግዚአብሔር ጸጋ እንጂ በሙሴ ሕግ እንዳልሆነ የተረጋገጠበት ፤ የቤተ ክርስቲያንን አቅጣጫ የወሰነ ፤ ከተደበላለቀ ትምህርት
ያጸዳ አስፈላጊ ጉባኤ ነበር።
ጴጥሮስ “በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ እንደ እነርሱ ደግሞ እንድን ዘንድ እናምናለን” ሲል አይሁድ እንኳ የሚድኑት በሕጋቸው አለመሆኑን
ለማስረዳት ነው።
እንግዲህ የገላትያ መልክትም ይህን እውነታ የሚያብራራ ነው መልካም ጥናት ይሁንልን
አከፋፈሉ
- ም 1-2 የወንጌልን ከስሕተት ትምህርት ለመከላከል የተጻፈ ነው
- ም 3-4 የወንጌልን ጸጋነት የሚያብራራበት ክፍል ሲሆን
- ም 5-6 የወንጌልን ጸጋ ተግባራዊነት የሚያረጋግጥ ነው።
ገላትያ ምዕራፍ ፩
ቁ፡1-10 ( ... ይቀጥላል)
No comments:
Post a Comment