ነጻነት (ካለፈው የቀጠለ) ክፍል ፮
ባልፈው ሳምንት ንባባችን እግዚአብሔርም የሁላችንን በደል በእርሱ ላይ አኖረ የሚለውን ቃል ከጠቅስን በኋላ ነበር
ያቆምነው ። እግዚአብሔርም የሁላችንን በደል በእርሱ ላይ አኖረ የሚለውን ቃል ለመረዳት ትምህርተ ድህነትን መማር
አለብን
ትምህርተ ድኅነት:-
በልጁ የሚያምን የዘለዓለም ሕይወት አለው በልጁ የማያምን ግን የእግዚአብሔር ቁጣ በእርሱ ላይ ይኖራል እንጂ ሕይወትን
አያይም (ዮሐ 3፡36)
መዳን:- መዳን የሚለውን ቃል በሁለት ትርጉም ልናየው እንችላለን
1 መትረፍ ማለት ነው። ሊሞት ሲጠበቅ የነበረ በሽተኛ ሳይሞት ቢቀር ተረፈ ይባላል ዳነ ለማለት ነው
2 ማምለጥ ማለት ነው በጠላት ተከቦ ወይም በአደጋ ውስጥ የነበረ ሰው ከዚህ ሁኔታ ሲወጣ አመለጠ ይባላል።
ስለዚህ መዳን ማለት መትረፍ እና ማምለጥ የሚል ትርጉም አለው። በዚህ መሠረት ከላይ ያየነውን ጥቅስ መነሻ በማድረግ
የመዳንን ትምህርት እንማራለን። በዚህ ቃል ውስጥ
1 የዘለዓለም ሕይወት አለው[ይድናል]
2 የእግዚአብሔር ቁጣ በእርሱ ላይ ይኖራል [ይፈረድበታል]የሚሉትን እንመለከታለን።
የእግዚአብሔር ቁጣ:- የሰው ዘር እግዚአብሔር የተቆጣው ዘር ነው። እንደሌሎቹም ደግሞ ከፍጥረታችን የቁጣ ልጆች ነበርን
ይላል። (ኤፌ 2፡3)
ፍጥርታችን:- ፍጥርታችን የተባለው አዳም ነው የመጀመሪያው ዘር እርሱ ነበርና። ኃጢአት ወደዚህ የመጀመሪያው ዘር
በመግባቱ እግዚአብሔር ተቆጣው። በዚህ ምክንያት ከአዳም የተወለደ ሁሉ ተፈጥሮዉን እንደወረሰ ሁሉ ኃጢአቱንና
ፍርዱንም ወርሷል። ስለዚህ ምክንያት ኃጢአት በአንድ ሰው ወደ ዓለም ገባ በኃጢአትም ሞት ፤ እንደዚሁም ሁሉ
ኃጢአትን ስለአደረጉ ሞት ለሰው ሁሉ ደረሰ ይላል። (ሮሜ 5፡15)
የኃጢአት አገባብ:- ኃጢአት ወደ ፍጥረታችን እንዴት እንደገባ ከማየታችን በፊት ሰው [ፍጥረታችን] ከእግዚአብሔር ጋር
የነበረውን ግንኙነት እንመልከት ፤
እግዚአብሔር አምላክም ሰውን ወስዶ ያበጃት ዘንድ ይጠብቃትም ዘንድ በኤድን ገነት አኖረው። እግዚአብሔር አምላክም
ሰውን እንዲህ ብሎ አዘዘው ፤ ከገነት ዛፍ ሁሉ ትበላለህ ፤ ነገር ግን መልካምንና ክፉን ከሚያስታውቀው ዛፍ አትብላ ፤
ከእርሱ በበላህ ቀን ሞትን ትሞታለህ (ዘፍ 2፡15-16)።
በዚህ ቃል ውስጥ በእግዚአብሔርና በሰው መካከል ያለውን ቃል ኪዳን እናስተውላለን ሆሴ 6፡7
ቃል ኪዳኑ ዘፍ 2፡28-30 ያለው ነው። አዳም የፍጥረት ገዢ ሲሆን እግዚአብሔር ደግሞ የአዳም ገዢ ነበር። ዛፉ በሁለቱ
መካከል ላለው ቃል ኪዳን ምልክት ነው። አዳም እና ሄዋን በገነት ውስጥ ሲኖሩ ማንኛዉንም ዛፍ መብላት ይችላሉ። አንዱን
ዛፍ ሲያዩ ግን የእግዚአብሔርን ክብር ፤ ገዢነቱን ያያሉ በዚህ ጊዜ አምልኮ ፤ ምሥጋና ፤ ስግደት ፤ ያቀርባሉ። ዛፉን
ሲበሉ ግን የእግዚአብሔርን ክብር ማቃለላቸው ነበር።
ኃጢአት እንዴት ገባ?
ኃጢአት የገባው በሐሳብ ነው። የህ ሐሳብ የመጣው በዕባብ ተሰውሮ በመጣው በሰይጣን ነው። እባብም ለሴቲቱ አላት ፤
ሞትን አትሞቱም ከእርሷ በበላችሁ ቀን ዓይኖቻችሁ እንዲከፈቱ እንደ እግዚአብሔርም መልካም እና ክፉን የምታውቁ
እንድትሆኑ እግዚአብሔር ስለሚያውቅ ነው እንጂ (ዘፍ 3፡4-5) ።
በዚህ ቃል ውስጥ
- ሐሰት
- ጥርጣሬ
- ክህደት[እግዚአብሔርን አለማመን]
- ትእቢት
- ምኞት ወዘተ...
የመሳሰሉት የኃጢአት ሐሳቦች ወደ ሄዋን ገቡ። ሄዋን ሐስትን በማመኗ ዛፉን ስትመለከተው ፤ የእግዚአብሔርን ክብር
ማየት አልቻለችም። በዚህ ፈንታ ስሥትና መጎምጀት አእምሮዋን ተቆጣጠራት። ከዛፉም በላች ለባሏም አበላችው። በዚህ
ጊዜ የእግዚአብሔር ሐሳብ ሳይሆን የሰይጣን ሐሳብ አእምሮቸውን ስለገዛው ከዚህ ጊዜ ጀምሮ የእግዚአብሔር ክብር
ጊዜ የእግዚአብሔር ሐሳብ ሳይሆን የሰይጣን ሐሳብ አእምሮቸውን ስለገዛው ከዚህ ጊዜ ጀምሮ የእግዚአብሔር ክብር
ተወሰደባቸው።
እግዚአብሔር ተቆጣ:- አዳም ቃል ኪዳኑን በማፍረሱ በእርሱና በዘሩ ላይ እንዲሁም አዳም በሚገዛው ፍጥረት ላይ ተቆጣ
እርሱንም ከገነት አስወጣው። እግዚአብሔር አዳምን ከገነት ያስወጣው ስለተቆጣ ነው። አዳም ከገነት ከወጣ በኋላ ልጆች
ቢወልድም ወደ ገነት ምግባት ግን አይችሉም ነበር። ምክንያቱም የቁጣ ልጆች ስለነበሩ ነው (ኤፌ 2፡3)። ስለዚህ እኛም
ከፍጥርታችን የቁጣ ልጆች ነበርን።
የቁጣው ቃል:- በሦስቱም ማለት በእባቡ ፤ በሴቲቱ እና በወንዱ ድርጊት ምክንያት የፍርድ ቃል ተነግሯል።
ለምሳሌ ፤ በአንተና በሴቲቱ በዘርህና በዘርዋ መካከል ጠላትን አደርጋለሁ እርሱ ራስህን ይቀጠቅጣል ፡ አንተም ሰኮናዉን
ትቀጠቅጣለህ። ሰኮናን መቀጥቀጥ የፍርድ ቃል ነው። የሴቲቱን ቃል ሰምተሃልና ምድር ካንተ የተነሳ የተረገመች ትሁን (ዘፍ
3፡15 ፡17)። የሚለውና ሌሎችም የርግማን ቃላት ናቸው።
ኃጢአት በእግዚአብሔር ፊት እንዴት ይታያል?
ኃጢአት በእግዚአብሔር ፊት ሲታይ የእግዚአብሔርን ክብር እና ቅድስና የሚነካ ወንጀል ነው። ኃጢአት የሚባለው ደግሞ
ድርጊት ብቻ አይደለም ሐሳብም ኃጢአት ነው። እግዚአብሔር የሚመለከተው የልብን ሁኔታ ነውና።
የሰው ልብ በእግዚአብሔር ፊት ምን ይመስላል?
ሰው የሰይጣንን ሐሳብ እና ፈቃድ ካደረገ በኋላ ሐሳቡ [ልቡ]ተባላሽቷል። እግዚአብሔር ሲመለከተውም ይህን ይመስላል ፤
-እግዚአብሔርም የሰው ክፋት በምድር ላይ እንደ በዛ የልቡ ሐሳብ ምኞትም ሁልጊዜ ፈጽሞ ክፉ እንደሆነ አየ (ዘፍ 6፡5)
- የሰው ክፋት
- የልቡ ሐሳብ ምኞትም
- ሁልጊዜ
- ፈጽሞ
- ክፉ እንደሆነ አየ
የሚሉትን ቃላት በጸትታ አስተውል።
ምድርም በእግዚአብሔር ፊት ተበላሸች ምድርም ግፍን ተሞላች። እግዚአብሔርም ምድርን አየ። እነሆም ተበላሸች ፤
ሥጋን የለበሰ ሁሉ በምድር ላይ መንገዱን አበላሽቶ ነበርና። (ዘፍ 6፡11)
በዚህ ቃል ውስጥ ድግሞ
- በእግዚአብሔር ፊት
- ተበላሸች
- ግፍን ተሞላች
- ሥጋን የለበሰ ሁሉ
- መንገዱን አበላሽቶ ነበር
የሚሉትን ቃላትም አስተዉል።
የሰው ልብ ከሁሉ ይልቅ ተንኮለኛ እጅግም ክፉ ነው ማንስ ያውቀዋል? እኔ እግዚአብሔር ለሰው ሁሉ እንደ መንገዱ ፤ እንደ
ሥራው ፍሬ እሰጥ ዘንድ ልብን እመረምራለሁ ኩላሊትንም እፈትናለሁ (ኤር 17፡9-10)።
በዚህ ቃል ውስጥ
- የሰው ልብ
- ከሁሉ ይልቅ ተንኮለኛ
- እጅግም ክፉ ነው
- ልብን እመረምራለሁ
የሚሉትን ቃላት አስተውል
የሰው ልብ በእግዚአብሔር እይታ መሠረት ሰውን በሚያረክስ ነገር የተሞላ ነው። አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ በልብ
ውስጥ ያሉትን ነገሮች እንዲህ ዘርዝሯቸዋል።
ከውስጥ ከሰው ልብ የሚወጣ ክፉ ሐሳብ ፤ ዝሙት ፤ መስረቅ ፤ መግደል ፤ ምንዝርና ፤ መጎምጀት ፤ ክፋት ፤ ተንኮል
፤ መዳራት ፤ ምቀኝነት ፤ ስድብ ፤ ትእቢት ፤ ስንፍና ናቸው። ይህ ክፉው ሁሉ ከውስጥ ይወጣል ሰውንም ያረክሰዋል
(ማር 7፡20-23)። በዚህ ምክንያት የእግዚአብሔር ቁጣ በአመጸኛው የሰው ዘር ላይ ተገልጧል (ዘፍ 7፡1-24)።
የሰው ጽድቅ በእግዚአብሔር ፊት ሲታይ:- ጽድቅ ማለት በእግዚአብሔር ፊት ተቀባይነት ማግኘት ወይም እግዚአብሔር ደስ
የሚሰኝበት ኑሮ ማለት ሲሆን ጻድቅ ማለት ደግሞ በእግዚአብሔር ሕግ ፊት ምንም ነውር የሌለበት ማለት ነው።
ሰዎች ምንም እንኳ ትክክለኛውን ሥራ ቢሠሩም ልባቸው ክፉ በመሆኑ ጽድቃቸው እንደመርገም ጨርቅ ይቆጠራል (ኢሳ
64፡6)። ስለዚህ በእግዚአብሔር ፊት ነውር የሌለበት ጻድቅ አልተገኘም። የሚከተሉትን ጥቅሶች አናስተውል ፤
ሰዎች ምንም እንኳ ትክክለኛውን ሥራ ቢሠሩም ልባቸው ክፉ በመሆኑ ጽድቃቸው እንደመርገም ጨርቅ ይቆጠራል (ኢሳ
64፡6)። ስለዚህ በእግዚአብሔር ፊት ነውር የሌለበት ጻድቅ አልተገኘም። የሚከተሉትን ጥቅሶች አናስተውል ፤
* ጻድቅ የለም አንድስ እንኳ አስተዋይም የለም እግዚአብሔርን የሚፈልግ የለም ፤ ሁሉ ተሳስተዋል ፤ በአንድነትም
የማይጠቅሙ ሆነዋል ፤ ቸርነት የሚያደርግ የለም ፤ አንድስኳ የለም (ሮሜ 3፡11-12)
- አንድስንኳ የለም
- ሁሉ ተሳስተዋል
የሚሉትን ቃላት በማስተዋል ተመልከት
* ንጹሕ ይሆን ዘንድ ሰው ምንድር ነው? ጻድቅስ ይሆን ዘንድ ከሴት የተወለደ ምንድር ነው? እነሆ ፤ በቅዱሳኑስ እንኳ
አይታመንም ፤ ሰማያትም በፊቱ ንጹሐን አይደሉም ፤ ይልቁንስ አጸያፊና የረከሰ ፤ ኃጢአትንም እንደ ውሃ የሚጠጣ ሰው
ምንኛ ያንስ? (ኢዮ 15፡14-16)።
* ልዩነት የለምና ሁሉ ኃጢአትን ሠርተዋልና የእግዚአብሔር ክብር ጎድሏቸዋል (ሮሜ 3፡23)።
ታዲያ ሰው እንዴት ሊድን ይችላል?
ሰው ሊድን የሚችለው ነውር ባልተገኘበት በኢየሱስ ክርስቶስ ሥራ ነው። እግዚአሔር ይህን የድኅነት መንገድ አስቀድሞ
ተናግሯል እንዲህ ሲል እርሱ ራስህን ይቀጠቅጣል (ዘፍ 3፡15)። ለአብርሃምም እንዲህ ሲል የምሥራቹን ተናግሮ ነበር ፤
የምድር አሕዛብ ሁሉ በዘርህ ይባረካሉ (ዘፍ 12፡3፤22፡18)።
No comments:
Post a Comment