Friday, January 28, 2011

KING ( የሰው ክፋት)( ዘማሪ ናፍቆት ገበየሁ)

ከዕለታት አንድ ቀን
ሰው፡ እባብ፡ አይጥ፡ እና ዝንጀሮ ተያይዘው መንገድ ይሄዳሉ።  ካሰቡበትም ሳይደርሱ ይመሽባቸዋል ከዚያም ወደ አንድ ሰውዬ ቤት ይሄዱና ተራ በተራ እንዲያሳድራቸው ይጠይቁታል በመጀማሪያ ሰውየው ሄዶ እንዲህ አለው እባካችሁ እዚህ ቤት የመሸበት የማታ እንግዳ ማደሪያ ፈልጌ ነበር ሲል ባለቤቱ ብቅ ብሎ ውይ ምን ችግር  አለ ደሞ ለሰው ብሎ አቅፎ ስሞ አስገባውና ማደሪያ ሰጠው።  በመቀጠልም ዝንጀሮ ወደ ሰውየው ቤት ሄዶ ሰውየው እንዲያሳድረው ጠየቀ ሰውየውም ዝንጀሮውን እህሉን እንዳይነካበት በማስጠንቀቅ ማደሪያ ቦታ ሰጠው። ከዚያም አይጥም በተራዋ ሄደች ለሷም እንደ አቅሟ ትንሽዬ ቦታ እበሩ አጠገብ ተሰጣትና ከዛ ቦታ እንዳትንቀሳቀስ ማስጠንቀቂያ ተነገራት። በመጨረሻም የፈረደበት እባብ እንደሌሎቹ እሱም ባቅሙ ማደሪያ ሲጠይቅ ሰውየው በቁጣ አንተ ክፉ ደሞ አንተን እቤቴ ላሳድር ብሎ ሰደበው እባብ ግን አይ ብከፋ ብከፋ ከሰው አልከፋ በማለት ማደር ስላልተፈቀደለት በሃዘን እዛው ውጪ በሩላይ እየበረደው አደረ።  በነጋታው ሁሉም ከእንቅልፋቸው ተነስተው መንገዳቸውን ቀጠሉ።  እንዲሁ በአንጻሩ አንድ ቀን ይሄ እነዚህን ሁሉ የተቀበለና ሁሉንም እንደ ስሜቱ ያስተናገደ ሰው ሃብቱ ሁሉ ጠፍቶበት ደህይቶ የሚበላው አቶ ተቸግሮ መንገድ ላይ ሲሄድ ያን ጊዜ የተቀበላትን አይጥ አገኛት እና እንዲህ አላት አይጥ እንደምን አለሽ? አስታወሺኝ? እሷም በመመለስ አዎ አስታወስኩህ ሰው እንደምን አለህ ምነው በሰላም ነው አለችው እሱም ይደረሰበትን ሁሉ ከነገራት በሃላ በነገሩ በጣም በማዘኗ መርዳት ስለፈለገች ቆይ እዚህ ጋር ጠብቀኝ ብላ ሄዳ ከሰው ቤት ወርቃ ወርቅ ሰብስባ አምጥታ ያሄንን ሸጠህ ሰው ሁን ብላ ሰጠችውና ተሰናብታው ሄደች። አይጥ ብድሯን በምትችለው መንገድ ከፍላ እነደሄደች ያን ግዜ በቤቱ የተቀበለውን ሰው አገኘው እሱም ያንን ሰው አስታወስከኝ ብሎ ጠየቀው ያ ውለታ የተዋለለት ሰው ግን ውለታ የዋለለትን ሰው አላስታወሰውም ከብዙ ንግግር በሃላ አስታወሰው እሱም የደረሰበትን ችግር ሀሉ ነገረው እሱም በል መንም የለኝም ልረዳህም አልችልም ነገር ግን እሱን የያዝከውን ወርቅ የምትሸጥበት ቦታ ልውሰድህ ይለውና ወርቁን ተቀብሎ ይይዝለትና አብረው ይሄዳሉ ብዙ ከተጋዙ በሃላ ያን ምሲኪን ሰው ወደ ገደል ገፍትሮ ከቶ ወርቁን ይዞበት ይሮጣል።
ያ ምስኪን ሰው ተገለባብጦ ገደል ወስጥ ይወደቃል በድንገትም ያን ግዜ ውለታ የዋለለትን ዝንጀሮ ያገኘዋል ሰው ያደረገውን ከሰማ በሃላ በጣም በማዘን ዝንጀሮ ምንም ሊረዳው ስላልቻለ እንደምንም ብሎ ከጉድጋድ ውስጥ ያወጣውና በሃዘን ይሸኘዋል ያው ዝንጀሮም በሚችለው መጠን ብድሩን መለሰ።  ከብዙ መንገድ በሃላ ያሰው እባብን ያገኘውና እነዲህ ይለዋል እባብ እንምን አለህ? አስታወስከኝ ሲለው እባብ በፍጥነት አዎ አስታወስኩህ አንተ ያን ጊዜ ክፉ ብለኸኝ ውጪ ያሳደርከኝ ሰው ነህ አይደል ብሎ ጠየቀው።  ሰውየውም አዎ ብሎ መለሰለትና ሰው የደረገውን እና ሌሎቹ የከፈሉትን ውለታውን ሲነግረው እባብ በማዘን ያን ግዜ ብከፋ ብከፋ ከሰው አልከፋም አላለኩህም አለውና በል እኔ ምንም የለኝም ግን በአንድ ነገር እረዳሃለሁ እዛ ማዶ ጋራ ያለ አንድ ሃብታም ሰው አንድ የሚወዳትን ለጁን ነገ ይድራል እኔ ላንተ መርዜን እሰጥህና ሄጄ እሷን እነድፋታለሁ ከዚያም አንተ መርዙን ይዘህ መተህ እሷን ታድናታልህ አባቷም ደስ ይለዋል ይለውና በነጋታው መርዙን ሰቶት ይሄድና ልጅቷን ይነድፋታል ከዚያም አባቷ ልጄ ልትሞትብኝ ነው ብሎ ሲጨነቅ ልጁን ያድነለታል ከዚያም አባትየው በደስታ የሃብቱን እኩሌታ በእባብ ምክንያት ይሰጠዋል ስለዚህ የተናቀውና የተጠላው እባብ ታላቁን ቁም ነገር ላልተዋለለት ውለታ መለሰ።  የተከበረው የሰው ልጅ ግን የተዋለለትን ውለታ በክፋት ለውጦ እራሱን አዋረደ።
ማስተዋልን ይስጠን እግዚአብሔርን እንፍራ

ይቆየን

2 comments:

  1. ፋና አንዳንድ አባቶች ሰውን ማመን ቀብሮ እላዩላየ 10 ድንጋይ ጭኖ ነው ሲሉ በጣም ይገርመኝና ያስቀኝ ነበር ነገር ግን ሳስበው እውነታቸውን ነው። ግን አንድ በጣም የሚደንቀኝ ነገር ቢኖር ለሰው ጌጡ ሰው ነው። በዚህ ምድር ላይ ምንም የሁሉ ነገር መሪ ብንሆን ሃብታችንን መጣያ ብናጣ እውቀታችን የላቀ ቢሆን ሰው ከሌለ እኛም የለንም ማለት ነው ለሰው ዉበቱ ሰው ነው እና እንደ እኔ አባባል ሰው ከሰው ጋር ወይም ሰው አለሰው መኖር ከባድ ነው ማለት ነው። ሰው ሰውን አምኖ አምላኩን ግን ተማምኖ/አምልኮ ቢኖር ከሰው የሚደርስበት በደል ብዙም አይሰማውም ነበር።

    ReplyDelete