ከእለታት አንድ ቀን አንድ እግዚአብሔርን በጣም የሚወድና የሚያመለክ ሰው ነበረ። የዚህ ሰው አምልኮት ከሁሉም ሰው የበለጠና የሚገርም ነበር። ብዙ በሱ እምነት ስር ያሉ ችግረኞች ወደሱ በመጡ ጊዜ በደንብ ተቀብሎ አስተናግዶ የሚገባቸውን ሀሉ አድርጎ ይሸኛቸው ነበር። ከእምነቱ ጥንካሬ የተነሳ አንድ ነገር በፈለገ ጊዜም ሆነ በከፋው ጊዜ እግዚአብሄርን በግልጽ እስኪያናግረው ድረስ የበቃ ሰው ነበር።
ከዕለታት አንድ ቀን አንድ የ60 አመት አዛውንት መንገድ ላይ ይደክማቸው እና ወደእሱ ቤት ሄደው ለማረፍ ይጠይቁታል እሱም በጣም ከመደሰቱ የተነሳ እሱ ቤት እነዲያድሩ ይለምናቸውና ያለውን ሁሉ ያደርግላቸውና ቁጭ ብለው ይጨዋወታሉ በመጨረሻም እኩለ ሌሊት ላይ ለመተኛት ሲዘጋጁ ያሰው ለሰውየው መጽሃፍ ቅዱስ አምጥቶ ይሰጣቸዋል አንብበው እንዲተኙ። በዚያም ወቅት ያልጠበቀውና ሊያመነው ያልቻለው ነገር ተከሰተ ሽማግሌው እጅግ በመናደ የሰጣቸውን መጽሃፍ ቅዱስ ውረወሩበትና ደሞ ምን እንዳደርገው ነው የሄን የክርስቲያን መጽሀፍ የምትሰጠኝ አሉት። እሱም በጣም ከመበሳጨቱ የተነሳ በዛ በምሽት እኛን ሽማግሌ ሰውዬ ጎትቶ ከቤቱ አውጥቶ እመንገድ ላይ ጣላቸውና ሰደባቸው።
ወደቤቱም ገብቶ እግዚአብሔርን በማማረር ለምን የማያምን ሰው ቤቴ አመጣህብኝ ብሎ ጮሆ ጠየቀው። እግዚአብሔርም በነገሩ ፍጹም በመደነቅ እንዲህ ብሎ ጠየቀው ለመሆኑ ከቤትህ አውጥተህ መንገድ ላይ በዚህ በጨለማ የጣልካቸው ሽማግሌ ስንት አመታቸው ነው? ሰውየውም 60 ብሎ መለሰ። እግዚአብሔርም እንዲህ አለው እኔ እኚህን ሽማግሌ ለ60 አመት ተሸክሜአቸው ኖሬአለሁ አንተ ግን ለአንድ ቀን መሸከም አቃተህ አለውና በማዘን ተሰውሮት ሄደ።
ይቆየን
ናፍቆቴ በጣም ደስ የሚል ቃል ነው::
ReplyDeleteያስጀመረ አምላክ ፍጻሜህን ያሳምርልህ!!!