Thursday, January 27, 2011
KING ( ከእምነትና ከስራ ማን ይበልጣል?) ናፍቆት ገበየሁ
እንደኔ እንደኔ እምነት ቀዳሚ ነው። እውነተኛ አማኝ በስራው ይታወቃል። አምናለሁ የሚለን ሁሉ ግን አማኛ አይደለም። እውነተኛ ስራን ለመስራት ማመን ይኖርብናል ለምሳላሌ አንድ ፈረስና ጋሪ ቢኖሩ ቀዳሚው ፈረሱ ነው ፈረሱ ግን ጋሪውን ይዞት ይሄዳል ጋሪው ዞሮ ፈረሱን እየጎተተ አይሄድም እንደ ስርዐቱ ፈረሱ ከቀደመ ስራም ይሰራል ማለት ነው። ስለዚህ እምነት በፈረሱ ይመሰላል ስራ ደሞ በጋሪው ማለት ነው እውነተኛ እምነት ያለው ሰው ቅዱስ ስራ እየሰራ የጌታ መክበሪያ ሆኖ ይኖራል። ነገር ግን እምነት በአፉ ብቻ የሆነ ስው እምነቱ ባዶ ነውና ስራውም ባዶ ይሆናል ከሁለቱም ሳይሆን ባዶውን ይቀራል ስለዚእህ እውነት የሚያምን ሰው ሁል ግዜ እውነተኛ ስራ በእምነቱ ስር ይኖራል ማለት ነው ስለዚህ እምነት ከስራ ይበልጣል ማለት ነው። ሌላ ደሞ ስራ ሰርተን ከፍተኛ ቦታ ለመድረስ ወይም በስራችን መጠቀምና ከፍ ማለት ከፈለግን መጀመሪያ ህሊናችን በስራው ላይ (በነገሩ ላይ) ማመን መቻል አለበት ሰውነታችን ስራውን ለመስራት ትዕዛዝ የሚያገኘው እኛ ስናምን ብቻ ነው ማለት ነው። ለምሳሌ አንድ የታወቀ ሯጭ ከመሮጡ በፊት ማሸነፉን አምኖ ለዕግሩ ይነግረዋል ያመነበትን ያስረዳዋል ማለት ነው ያንን የተረዳው ልብና እግር ደሞ እምነቱን ከግብ ለማድረስ ስራ ይ ሰራሉ ማለት ነው በመጨረሻም በስራው ምክንያት እምነት ከግብ ደረሰ ማለት ነው ስለዚህ ምን ግዜም ቢሆን እምነት ዋና ነው እውነተኛ ስራ በዕምነት ስር የሚኖር የእምነት ውጤት ነው ( ስራ የምለው እውነተኛ ስራ ማለቴ ነው ከ እውነተኛ አማኞች የሚገኝ እውነተኛ የጽድቅ ስራ)። ነገር ግን በስራችን መብዛት ወይም ማነስ አይደለም የምንጸድቀው ወይም የምንድነው በእምነት ነው እንጂ ምክንያቱም በእውነተኛ እምነት ወስጥ እውነተኛ ስራ እንዳል እናውቃለን እና።
Subscribe to:
Post Comments (Atom)
No comments:
Post a Comment